Get Mystery Box with random crypto!

የታክሲ ሹፌር የፍቅር ደብዳቤ •=•=•=•=•=•=• ነብሷ አማን ነሽ ? ...እኔ ከባሉ | አቤ እና ከቤ

የታክሲ ሹፌር የፍቅር ደብዳቤ
•=•=•=•=•=•=•
ነብሷ አማን ነሽ ? ...እኔ ከባሉካው ጭቅጭቅና ከቤንዚን ዋጋ ሰማይ መሆን በስተቀር የመጨረሻ ሀፒ ነኝ። ብቻ ግን አንቺ እንደ ቶፓዝ ምላጭ ጣል ጣል አረግሽኝ የኔ TAXI የመጬ ናፍቀሽኛል ታውቂያለሽ?? ፎንቃሽ ሌላ መስመር እንዳልወርክ ገትሮ ይዞኛል። ከአራት ኪሎ መገናኛ መጫን የጀመርኩት እኮ አንቺን ለመከለም እንዲያመቸኝ ብዬ ነበር። አሁን አሁንማ በታክሲው ስፖኪዮ ፍሉካሽ እየተከሰተ ስንቴ ተጋጨሁ መሰለሽ። ትዝ ይልሻል ደሞ ባለፈው ሳምንት ወራጅ አለ ብለሽ ዱብ ስትይ እንዴት እንደሸከከኝ?? .... ትርንጎ ትሙት.... አሞራው ራሱ ሸኬ ብሎ
የመጨረሻ ሙድ ጋማ አለብኝ። ባክሽን ፍቅሬ ልብሽ እንደ ትራፊክ ጨካኝ አይሁን። እንደ ሁሌው ጋቢናው ላንቺ ሪዘርቭድ ነው ..... ከጎኔ ዱቅ ብለሽ ሚሪንዳሽን እየሸረብሽ ከለገሀር... ሳሪስ... ከፒያስ... ሽሮሜዳ... ከቀበና... ኮተቤ እየጫንን ከተማዋን ቀውጢ የምናደርግበት ቀን ሁሌም ናፍቂያታለሁ። የ 10 ብር ዝርዝር እየፈለኩ ነው። ይመችሽ ነብሴ

Join us➥
@abeenakebec