Get Mystery Box with random crypto!

ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል አሉ ➯በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መስከረም 11 አንድ ግለሰ | Abel Birhanu የወይኗ ልጅ

ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል አሉ

➯በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መስከረም 11 አንድ ግለሰብ ከሚስቱ እጅ ሞባይል መንትፎ ሲሮጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

➯ጉዳዩ እንዲህ ነው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለመጠበቅ የተሰማሩ አካላት (ሮንድ ጠባቂዎች) በምሽት አንድ ግለሰብ ከተበዳይ እጅ ሞባይል መንትፎ ሲሮጥ ተመልክተው ግለሰቡን ተከታትለው በቁጥጥር ስር በማዋል ለፖሊስ ያስረክባሉ።

➯በዚህን ግዜ ታዲያ ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ አበው ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ሞባይሉን የዘረፈው ከራሱ ሚስት ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።