Get Mystery Box with random crypto!

የማይናማሯ የቀድሞ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር የ 3 ዓመት ፍርድ ተፈረደባቸዉ፡፡ ➯ይ | Abel Birhanu የወይኗ ልጅ

የማይናማሯ የቀድሞ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር የ 3 ዓመት ፍርድ ተፈረደባቸዉ፡፡

➯ይህ የ 3ዓመት ፍርድ ከዚህ በፊት በወታደራዊዉ የማይናማር መንግስት በተፈረደባቸዉ 17 ዓመት የእስር ጊዜ ላይ የሚጨመር ነዉ፡፡

➯ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር ወንጀል የ3 ዓመቱ ፍርድ ከከባድ የስራ ጫና ጋር የተፈረደባቸዉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በተለያዩ ወንጀሎች ከተፈረደባቸዉ የ 17 ዓመት እስር ላይ የሚጨመር መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

➯ሳንሱኪ በ2020 ህዳር ወር ላይ በተደረገዉ ምርጫ ላይ ፓርቲያቸዉ በከፍተኛ የበላይነት አሸንፏል በማለት ምርጫ አጭበርብረዋል ነዉ የተባለዉ ፡፡

➯በዚህ ወንጀል የተነሳ በተፈረደባቸዉ ፍርድ ሳንሱኪ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከፖለቲካዉ ርቀዉ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን፣ ወታደራዊዉ መንግስት በሳንሱኪ ዙሪያ ከዚህ በኋላ የሚከሰዉ እና ለፍርድ የሚያቀርባቸዉ ብዙ ወንጀሎች አሉት ነዉ የተባለዉ፡፡

➯የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ እና የማይናማር ተቃዋሚ ፓርቲ ቀንደኛ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ ባለፈዉ ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መዉረዳቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

➯ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ 2ሺህ 200 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ፣ ከ 15ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ፡፡

#Ethio Fm