Get Mystery Box with random crypto!

'አቡ ዘር ጁንዱብ ኢብኑ ጁናዳህ (رضي الله عنه) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡- 'የአላህ | ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️

"አቡ ዘር ጁንዱብ ኢብኑ ጁናዳህ (رضي الله عنه) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከተግባራት ሁሉ በላጩ የትኛው ነው?" በማለት መልዕክተኛውን (ﷺ )ጠየቅኳቸው፡፡

"በአላህ ማመንና በርሱ መንገድ መታገል" ሲሉ መለሱልኝ፡፡ "የትኛውን የባሪያ አይነት ነፃ ማውጣት ነው ብልጫያለው?" አልኳቸው፡፡ "ከባለቤቷ ዘንድ በጣም ተወዳጅና ውድ ዋጋ የምታወጣውን" የሚል ምላሽ ሰጡኝ። "ይህን ማድረግ ባልችልስ?" ስልም ጠየቅኳቸው። "የሚሰራን ወይም መስራት የማይቺልን ሰው አግዝ" አሉኝ። "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጥቂት ስራዎችን እንኩዋን ማከናወን ከተሳነኝስ?"በማለት ጠየቅኳቸው። "ሰዎችን ከመተናኮል ተቆጠብ። ይህቺ አንተው ለአንተው ለራስህ የመፀወትካት #ሶደቃ ናት።" ሲሉ መለሱልኝ።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================