Get Mystery Box with random crypto!

ከእለታት አንድ ቀን ሁለት ሰሀቦች ወደ ረሱል (ﷺ) ተወዳጅ ሚስት አኢሻ (ረድየሏሁ ዐንሀ) መጡ | ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️

ከእለታት አንድ ቀን

ሁለት ሰሀቦች ወደ ረሱል (ﷺ) ተወዳጅ ሚስት አኢሻ (ረድየሏሁ ዐንሀ) መጡና ጥያቄ ጠየቁ አኢሻ ሆይ!

እስኪ ረሱል (ﷺ) ላይ ያየሽውንና በጣም ያስገረመሽን ነገር ንገሪን አሏት

አኢሻ (ረድየሏሁ አንሀ ) እንባዋ ቀደማት አለቀሰች ከዛም እንዲህ አለች አንድ ቀን ማታ ረሱል (ﷺ) ከኔ ጋር ነበሩ አኢሻ ሆይ! ይችን ለሊት ፍቀጂልኝ ከጌታዬ ጋር ላሳልፈው አሉኝ"

እርስዎን የሚያስደስቶት ነገር ከሆነ እኔም ደስተኛ ነኝ ስላቸው ተነሱና ተጣጥበው መስገድ ጀመሩ ከዛም ጉንጫቸው እስኪርስ ድረስ አለቀሱ አሁንም ጉልበታቸው በእንባ እስኪርስ ድረስ አለቀሱ አሁንም መሬቱ በእንባቸው እስኪታጠብ ድረስ ማልቀሳቸውን ቀጠሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቢላል (ረድየሏሁ ዐንሁ) ለሰላት ሊጠራቸው መጣ እያለቀሱም አገኛቸው ከዛም እንዲህ አለ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ያለፈውንም የሚመጣውን ወንጀል ተምሮሎት እንዲህ ይሆናሉ ? ታዲያ አመስጋኝ ባሪያ መሆን የለብኝም እንዴ የሳቸው መልስ ነበር::

ከዛም የሚከተለውን ንግግር ተናገሩ:-…
ዛሬ ለሊት የተወሰኑ አንቀጾች ወርደውብኛል እነሱን አንብቦ ያላስተነተነ ሰው ወየውለት አሉና"

ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺧَﻠْﻖِ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺍﺧْﺘِﻠَﺎﻑِ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﻭَﺍﻟْﻔُﻠْﻚِ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﺗَﺠْﺮِﻱ ﻓِﻲ
ﺍﻟْﺒَﺤْﺮِ ﺑِﻤَﺎ ﻳَﻨﻔَﻊُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱَ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧﺰَﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻣِﻦ ﻣَّﺎﺀٍ ﻓَﺄَﺣْﻴَﺎ ﺑِﻪِ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﺑَﻌْﺪَ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ
ﻭَﺑَﺚَّ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻣِﻦ ﻛُﻞِّ ﺩَﺍﺑَّﺔٍ ﻭَﺗَﺼْﺮِﻳﻒِ ﺍﻟﺮِّﻳَﺎﺡِ ﻭَﺍﻟﺴَّﺤَﺎﺏِ ﺍﻟْﻤُﺴَﺨَّﺮِ ﺑَﻴْﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ
ﻟَﺂﻳَﺎﺕٍ ﻟِّﻘَﻮْﻡٍ ﻳَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ


ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትንና ቀንንም በማተካካት፣ በዚያቸም ሰዎችን በሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ በምትንሻለለው ታንኳ፣ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ በርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፣ ነፋሶችንም (በየአግጣጫው) በማገለባበጥ፣ በሰማይና በምድር መካከል በሚነዳውም ደመና ለሚያውቁ
ሕዝቦች እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡


«ሱረቱል አል-በቀራህ164» አነበቡ።

እኚህ ናቸው የኛ ነቢይ (ﷺ) ያለፈውንም የሚመጣውንም ወንጀል ተምሮላቸዋል ግን ሙሉ ለሊት እያለቀሱ ያድራሉ እኛስ እራሳችንን እንመልከት ቤተሰብ፤ የምንወዳቸው ጓደኞቻችን፤ ልጆቻችን ሞተው አልቅሰን ይሆናል ወይም የዱንያ ማጣት አስለቅሶን ይሆናል ወይም የማትሪክ የዩንቨርስቲ ፈተና ፈርተን ለሊት ቆይተን ይሆናል ግን ማናችን ነን ነገ አላህ ፊት እንደምንቆም አስበን ወንጀላችን ለሊት የቀሰቀሰን የተነሳን እራሳችንን እንፈትሽ ፡፡

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================