Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለኩራተኞቺ ! ምስጋና ለዓለማት ጌታ አላህ የተገባ ነው፡፡ በሱ ፈቃድ መልካም ነገሮቺ ሁ | ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️

ይድረስ ለኩራተኞቺ !

ምስጋና ለዓለማት ጌታ አላህ የተገባ ነው፡፡ በሱ ፈቃድ መልካም ነገሮቺ ሁሉ ይሞላሉ ፡፡ አላህን በብቸኝነት በማምለክ የዱንያም ሆነ የአኬራ ስኬት ይገኛል ፡፡

ሶላትና ሰላም በአዛኙ ነብይ፡የሰው ልጆቺ ሁሉ ምርጥና የመልካምነት ተምሳሌት በሆኑት በኛ ነብይና ፈለጋቸውን በተከተሉ ሶሀባቺ ላይ ይሁን፤ አሚን !
===========================

ኩራተኞቺ

አንድ አንድ ሰዎቺ እውቀት አለኝ, አሊም ነኝ, ትንሽ ተዋቂ ,ነኝ በሚል ሰበብ

ሰው ከማናገር፡በጥሩ ሲጠየቁ ከመመለስ ,እንዲሁም በመልካም ስራ ትብብር ላይ ቺላ ሲሉና በኩራትም ሲምቦጣረሩ ታያለህ ፡፡


ነገር ግን

የተኛውንም የሚያክል እውቀት ይኑርህ ጥቂትን እንጂ አለማወቅህን እወቅ፡ አለም ላይ ያለውን ተወውና ራስህ ላይ ያለውን አካል ክፍሎቺ እንኳን በቅጡ ሳይገባህ ለመንቦጣረር አትሞክር! ሁሉንም በስርአቱ አናግር በመልካም ተግባር ላይ ተረዳዳ፡ ለሰዎቺ እዘን ፡ግዴታ የኔ ካልሆነ ብቻ አትበል፡፡

በሀብትህ ሰበብ ሰዎ ከማናገር ከኮራህ፡በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ካገደህ እወቀው አንተ እጂጉን ደሀ ነህ ፡፡

ምድር ላይ ካለው ንብረት እጂግ ጥቂት እንጂ አልተሰጠህምና ካንተ ደሀ መስሎ በሚታይህ ሰው ላይ አትኮፈስ ፡፡ በኩራት ምንም ነገር ከመስራት ተቆጠብ ፡ አሏህ ኩራተኞቺን አይወድምና ፡፡


አሏሁ ሰብሀነሁ ወተአላ አንዲህ ይለናል


وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ

«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡

እነሆ ኩራት የሸይጧን ባህሪነውና እጂጉን ራቀው ፡፡ ሸይጣን በኩራቱ የዘላለም ክህደት ወስጥ አንደገባ ታውቃለህ ፡፡


وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ

ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡


የሚገርመቺሁ የትኛውንም ሰበብ አድርገው ለሚኮሩ ሰዎቺ ያለኝ ንቀት የላቀ ነው፡፡ ደረጃቸወም ይወርድብኛል!!!

ለምን የሰው ልጆቺ ሁሉ ምርጥ የሆኑት ነብያቺን ﷺ እንኳ ኩራተኛ አልነበሩም በል እንደውም ከሁሉም ጋር ያላቸው ግንኙነት በፍቅር የተሞላ ነበር ፡፡

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================