2022-07-31 17:48:51
የሱሩሪዮች ሴራ በሰለፍያ ላይ
በሀገራችን የሱሩሪያ መሪ የሆነው ዶክተር ጀይላን ከመዲና ወደ ሀገራችን በመጣበት ጊዜ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ ወጣቱን ለመቆጣጠር በሰለፍያ ስም እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር ። በዚህም ከዳር እስከዳር ወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ስሙ ገኖ እንቅስቃሴ ጀመረ ። አየር ጤና ያለው መርከዝ ገንብቶ ወጣቱን በደርስ ተቆጣጠረው ። በወቅቱ ምላሱ ከሰለፍያ ውጪ አያውቅም ወይ ያሰኝ ነበር ። ምስኪኑ ወጣት ዶክተሩ የሚፈልገው ሰለፍያ አይነትና ምንነት አያውቅም ስራው ዶክተር ጀይላን ማለት ብቻ ነው ። በዚህ ሁኔታ አያለ የነ ጀማል ያሲን ፊትና ሲመጣ ሱሩርይነቱ ታወቀ ። የዚህ ጊዜ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት ከመጀመሪያው በተቃራኒ ከዳር እስከ ዳር በሱ ላይ ረድ ተጀመረ ። ዶክተሩም የሚዘው የሚጨብጠው አጥቶ በሰለፍዮች ላይ ረድ ጀመረ ። በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ስለ ሸይኽ ረቢዕ እያነሳ እሱ ነው ይህን ፊትና ያመጣብን ማለት ስራው አድረጎ ያዘው ። ሙሪዶቹ ሰለፍዮችን መድኸልይ የሚል ስም ሰጥተው ሰውን ከሰለፍዮች የማራቅ ስራ መስራት የሙጥኝ አሉ ።
ዶክተሩ ይህ ቀጥተኛ ጦርነት ውጤቱ አመርቂ እንደማይሆን ለማወቅ ጊዜ አልወሰደበትም ። ስልቱን ቀይሮ ቀስ በቀስ ከሙሪዶቹ ቱጉህ ሰራተኞችን መልምሎ የሰለፍያ ጃኬት አልብሶ ወደ ሰለፍዮች ውስጥ በመላክ ሰለፍያን መቦርቦር ጀመረ ።
የመጀመሪያ ታርጌቱ የነበረው የወቅቱ የሰለፍዮች መርከዝ የነበረው የናጂያ ማህበር ነበር ። ተልእኮ በተሰጣቸው ሙሪዶቹ አማካይነት ወጣቱን የማረጋጋት ስራ ሰራ ። በወቅቱ የተሳካ ስራ የመስራቱ ምልክት ናጂያ የሚባለው ማህበር በነበረ ጊዜ ኮርስ ሲዘጋጅ በዐቂዳና ሚንሀጅ ላይ ታዋቂ ኡስታዞች ተመርጠው የሚሰጥ የነበረ ሲሆን በኋላ የዶክተር የማስተኛት ቫይረስ በመሪዎቹ ላይ ስራውን ሰርቶ በኢብኑ መስዑድ ስም የሚዘጋጁ ኮርሶች ወደ ሰፊና ወረዱ !!!!! ። ኮርስ አለ ይባላል ። ከየ ክፍለሀገሩ ዱዓቶች ተጠርተው ይመጣሉ የሚሰጠው ኮርስ ኪታቡ ጠሃራ ሆነ ። ምነው ሲባል ዱዓቶች ገና ናቸው ስለፍቅህ ሳያውቁ ትላልቅ መስአላ ላይ ይናገራሉ ይህ መሆን የለበትም መባል ጀመረ ። እየቀጠለ ሄዶ በየጊዜው የማለዘብ ሙሀደራዎች በኢልያስ አሕመድና በሌሎችም እየተሰጠ ወጣቱ ከንቃቱ ወጥቶ ወደ ሰመመን መግባቱን ሲያዩ 30 የጥልቅ እንቅልፍ ክኒኖችን በማዘጋጀት ወጣቱን አላህ ካዘነለት ውጪ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ አስተኙት ።
ዶክተሩም በኢብኑ መስዑድ ላይ የታቀደው ሴራ ከግቡ መድረሱ ሲያይ ፊቱን ወደነኢብኑ ሙነወር አዞረ ። በምን መልኩ እንደሆነ ዝርዝሩ ባናውቅም በእነርሱም በኩልም የፈለገውን ውጤት እንደሚያገኝና እነርሱም ከአቋማቸው ወደ ኋላ ሊሉ እንደሚችሉ በትእግስት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስረግጦ ተናገረ ። ያለው አልቀረም እነ ኢብኑ ሙነወር መጀመሪያ ሲያወግዙዋቸውና ከእነርሱ ሲያስጠነቅቁ የነበሩትን የመርከዙ ሰዎች ሙኻለፋቸውና ጥመታቸው እየጨመረ ሲሄድ ዝም ከማለት አልፈው ከእነርሱ የሚያስጠነቁቁትን መተቸትና ምን አዲስ ነገር አለ ማለት ጀመሩ ። ከዚህም አልፈው እኛ መጀመሪያ ረድ ያደረግነውና ያስጠነቀቅነው ኡዝራቸውን ሳናውቅ በፊት ነበር አሁን ለመስላሃ መሆኑን ነገሩን ተቀበልናቸው ሰለፍዮች ናቸው አብሮ መስራት ይቻላል ማለት ጀመሩ !!!!!! ።
ነገሩ በዘህ አላበቃም የመርከዙ ሰዎች ድንበር ታልፎባቸዋል ሰለፈረዮች ናቸው ኑ እንከራከር ብለው ለሰለፍዮች ጥሪ አቀረቡ ።
የመርከዙ ሰዎች ደግሞ ከሸራተኑ የአንድነት ድለቃ ጀምሮ በሰለፍዮች ላይ እየዘመቱ ከኺዋን ጋር ያላቸውን ትስስር እያጠበቁ በመጅሊስ ስልጣን ዋዜማ የእንኳን ደስ ያላችሁና በርቱ ወደፊት ገስግሱ የሚል የግጥም ስንኝ ቋጠሩ ። በመጅሊሱ የኢኽዋን ስልጣን መረከብ ላይ የሚችሉትን ሁሉ ለእንጀራ አባታቸው አበረከቱ ። በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ በመገኘት የተለመደው ሰቅጣጭ ቅርሻቶች ሲቀረሹ በስምምነት አሳልፈው ወጡ ። ከእነዚህ ውስጥ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን ንግግር ያደረገበት ሲንና ሷድ ( ሰለፍይና ሱፍይ ) የሚሉት ቃላቶች አይለያዩንም የሚለው ይገኝበታል !!!! ። አለመለያየታችን እጃችሁን አውጥታችሁ አሳዩኝ ሲል ከመርከዙ ተወካይ አንዱ የነበረው ሳሊህ አህመድ እጁን ሊያወጣ ሲል ጓደኛው መሀመድ ሐሰን ( ማሜ ) ዞር ብሎ ሲያየው እጁን መልሶ የተባለውን አንድነት አፅድቀው ወጡ ። ይህ የመርከዙ ሰዎች ምን አዲስ ነገር አመጡ ለሚሉት እነኢብኑ ሙነወር እንዲያስቡበት ለመጠቆም እንጂ በየቀኑ አዳዲስ ነገር ከማምጣት አልቦዘኑም ።
በነገራችን ላይ አንድ ሰው ወይም አንጃ ጥመቱን አውቀህ ረድ አድርገህ አስጠንቅቀህ ካልተመለሰ ዝም በል ሌላ አዲስ ነገር እስኪያመጣ መጠበቅ ግድ ነው ካልሆነ በሱ ላይ መናገር ሐራም ነው የሚል የሰለፍያ መርህ የለም ። የመርከዙ ሰዎች ከነበሩበት ተውበት አድርገው ሲመለሱ ብቻ ነው ዝም የሚባለው ። ማለት የነበረባቸው እኛ ረድ አድርገናል አስጠንቅቀናል አልተመለሱም አግዙን ተባብረን ህዝቡን እናስጠንቅቅ ጥመታቸውን ግልፅ እናድረግ ነበር ።
ዶክተሩም ሴራው በሁለቱም በኩል የሰራ መሆኑን በማየቱ ሲደሰት በሌላ በኩል ያላሰበው ውጋት አጋጠመው ። አሁንም ዝም ይላል ማለት አይደለም በተምዪዕ ( ማለዘብ ) ካልተሳካለት ወሰን በማለፍ ለማፈራረስ መምጣቱ አይቀርምና እንጠንቀቅ ። ምክንያቱም ሸይጧን ወደ አማኞች በዝንባሌያቸው በኩል ስለሚገባ ። የሱሩርያ መሪው ዶክተር ሰለፍያን የማፈራረስ ውጥኑ በሸይጧን እየታገዘ እያስኬደ ነውና ። በጣም የሚገርመው ኢኽዋንም ሆነ የትኛውም አንጃ እንዳጠቃላይ ከሀዲያን የኢስላም ጠላቶች ሰለፍያን ለማጥፋት የሚጥሩትን ያክል ማንንም ለማጥፋት አይጥሩም ።
አላህ ሰለፍዮችን ከሱሩርዮች ተንኮል ይጠብቃቸው ።
http://t.me/bahruteka
76 viewsአቡ ፊርደውስ, 14:48