Get Mystery Box with random crypto!

ሳሩ እንጂ ገደሉ የማይታያቸው ቆሞ ቀሮች! ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስትን መቅጣት የሚቻለው | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

ሳሩ እንጂ ገደሉ የማይታያቸው ቆሞ ቀሮች!
ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስትን መቅጣት የሚቻለው በምርጫ ካርድ ብቻ ነው! ህዝባችን ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን ሰጥቶ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ተመስርቷል! በዚህ ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያው ጀምሮ በቋሚነት በቋሚ ተቃውሞ የሚታወቁ እንደ ጅብ የፊት የፊታቸውን ብቻ የሚያዩ ቁሞ ቀሮች እያንዳንዱን አጋጣሚ ለራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ሀገርን ለእርድ የሚያመቻቹ "ሳሩን እንጂ ገደሉ የማይታያቸው ቆሞ ቀሮች ዛሬም ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም ነጠላ ዜማ ላይ ናቸው! ጅል አንድ ዘፈን ነው የሚያውቀው እንዲሉ አበው በምርጫ ያላገኙትን የመንግስት ስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን አስይዘው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ጋር ከመጋረጃ ጀርባ ይዶልታሉ .. . እኛም እንመከራለን የኢትዮጵያን የመንግስት ስልጣን በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ እንጂ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሲፈልጉ የሚሰጡት ሲፈልጉ የሚወስዱት ተራ ኃላፊነት አይደለም !
መንግስት ህዝብ የሰጠውን ኃላፊነት ተጠቅሞ ለህዝብ ቃል የገባውን ካልፈጸመ ፤ በየአምስት አመቱ የሚደረገውን የምርጫ መርሃ ግብር የተሻለ ሀሳብ ይዞ በመቅረብ ሀሳብን ሽጦ መንግስት ሁኖ መመረጥ የሚያስችልን ዕድል መጠቀም ይቻላል! ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ በኋይል የህዝብን አደራ በግርግር ለሌባ አሳልፎ የሚሰጥ ደካማ መንግስት አለመኖሩን ያሰባችሁትን በሃይል ማሳካት ሳትችሉ ስትቀሩ ይገባችኋል! በተጨማሪ ለተቃውሞ እና ለአመጽ ከሚወጣው ህዝብ በእጥፉ ለድጋፍ እና መንግስቱን ለመጠበቅ እንደሚወጣም መዘንጋት የለበትም!
አለቀ ደቀቀ
የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/