Get Mystery Box with random crypto!

የቀብር ሳጥን ነጋዴዎች Vs ETHIO 360! የቀብር ሳጥን መሸጫ ሱቆች ባለቤት ጠዋት ወደ ስራ ሲ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የቀብር ሳጥን ነጋዴዎች Vs ETHIO 360!
የቀብር ሳጥን መሸጫ ሱቆች ባለቤት ጠዋት ወደ ስራ ሲሄዱ "ፈጣሪ ሆይ ሰው እንዳይሞት አድርግ" ብለው ሊፀልዩ አይችሉም። "የዛሬውን ገበያ አድራልኝ" ነው የሚሉት፤ ይህም ሰው ይሙት ማለትነው።
ሞት በሚበዛ ወቅት ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ ቢዝነስ ይደራል። የሞተባቸው አዝነው ባለ ሱቆቹ ተደስተው ማየት የዘወትር ትእይንት ነው። በዚህኛው ገበያ ሰው ወደ ሱቆቹ የሚሄደው ሰው ሲሞትበት እንጂ ሞት ፍለጋ አይደለም።
የዩቲዩብ ሚዲያዎች ጥሩ ገንዘብ የሚከፈላቸው ብዙ ተመልካች ሲያገኙ መሆኑ ይታወቃል። ጥሩ ተመልካች የሚያገኙት ሰው ሲሞት በመሆኑ እንደ ቀብር ሳጥን ነጋዴዎቹ "ፈጣሪ ሆይ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን፤ ሰው አይሙት" ብለው ሊፀልዩ አይችሉም። ለምሳሌ በቅርብ በነበረው የዜጎች ሞት ኢትዮ360 ከ200ሺ በላይ ተመልካች አግኝቶ ነበር፤ ገቢም ደርቶለታል። ሞት ለሚያው ቢዝነስ ነው። ብዙ ጊዜ ኢትዮ360 ሞት ሲበዛ ብዙ ተከታይ መኖሩን ስለሚያውቁም ሮጠው 'GoFundMe' ከፍተው ተከታዮቹን እርዱኝ ማለትም ያዘወትራሉ።
በመሆኑም ለቀብር ሳጥን ነጋዴዎቹ እና የኢትዮ360 አይነት ሚዲያዎች ሞት ቢዝነሳቸው ነው፤ እንዳይቋረጥም ይፀልያሉ።
ከደንበኞቻቸው አንፃር ሁለቱም ጋር የምንሄደው ሰው ሲሞትብን መሆኑ ቢያመሳስላቸውም ከቀብር በኃላ ግን ሳጥን ቤት ዳግም አንሄድም። ሚዲያዎቹ ጋር ግን ከቀብር በኃላም ለሌላ ሞት ፍለጋ ደግመን መሄዳችን ከሞት ጋር ሱስ የያዘን መሆኑን ነው የሚያረጋግጠው።

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩየጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች1/