Get Mystery Box with random crypto!

የEpic Games store በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ወደ iOS እና Android እንደሚመጣ አስ | ab app

የEpic Games store በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ወደ iOS እና Android እንደሚመጣ አስታወቀ።

Epic የGames store በአለም ላይ ተወዳጅ ጌሞችን ለPC እና Playstation ሲሙሌተሮች ጌሞችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ወደ ሁለቱም iOS እና አንድሮይድ እንደሚመጣ አረጋግጧል።

Epic Games ስቶር ለሁሉም ጌም ዴቨሎፐሮች ተመሳሳይ ፍትሃዊ ስምምነት በማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጧል። ይህ ማለት ጌም ዴቨሎፐሮች ካበለፀጉት ጌም ከሚያገኙት ገቢ 88% ድርሻ ሲኖራቸው Epic Games ደግሞ 12% ያገኛል ፤ Epic Games በተጨማሪም ዴቨሎፐሮች የራሳቸውን ክፍያ ሲስተም ለተጠቃሚዎች ካቀረቡ 100% የሚያገኙትን ገቢ መጠቀም ይችላሉ ብሏል።

እስካሁን ስቶሩ በአንድሮይድ ላይ ምን እንደሚመስል እና ከFortnite ውጪ የትኞቹ ጌሞች እንደሚካተቱ ባናውቅም ወደፊት ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል ፤
iOSን በተመለከተ የወጣ ግልፅ መረጃ የለም።

@AbApp41566