Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሰዓታት ባጋጠመው “የሲስተም ችግር” ምን ያህል ብር ወጪ ሆነ? ባለፈው | ab app

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሰዓታት ባጋጠመው “የሲስተም ችግር” ምን ያህል ብር ወጪ ሆነ?

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ ተፈጠረ በተባለው ችግር ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መውጣቱ እየተነገረ ነው።

ከዚህ በፊት በአገሪቱ የባንክ ሥራ ታሪክ አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ በተከሰተው በዚህ ችግር የባንኩ ደንበኞች ካስቀመጡት የገንዘብ መጠን ውጪ ከገንዘብ መስጫ ማሽኖች (ኤቲኤም) እንዲሁም ከሞባይል ባንኪንግ ከፍተኛ መጠን ያለው ብር ወስደዋል።

ባንኩ አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን አሶሺየትድ ፕሬስ (ኤፒ) ዘግቦ ነበር።

የባንኩ ፕሬዝዳንት ጨምረው እንደተናገሩት የሲስተም ብልሽት በደረሰ ወቅት 10 ሺህ የሚሆኑ ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የማይመልሱ ከሆነ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው አስታወቋል በዚህም ገንዘቡን ተመላሽ የማያደርጉትን ሰዎች ስም ዝርዝር እና መረጃ ለፖሊስ እሳልፎ እንደሚሰጥ ገልጿል።

አንድ ትሪሊዮን ብር ጠቅላላ ሃብት መሰብሰብ የቻለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገሪቱ ዋነኛ ተቋማት ከሚባሉት ጥቂት ተቋማት መካከል አንዱ ነው ፤ በእአአ 2020/21 የበጀት ዓመት 20 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያገኘው ባንኩ በዚሁ የበጀት ዓመት 735 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ማድረግ መቻሉን ይፋ አድርጎ ነበር።

@AbApp41566