Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ክርስቶስ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ክፍል 3 የጌታችን በማህፀነ ማርያም ማደር | ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ነገረ ክርስቶስ

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

ክፍል 3

የጌታችን በማህፀነ ማርያም ማደር

ቅድስት ድንግል ማርያም "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ " በማለት በእምነት ስትቀበል አካላዊ ቃል በግብረ መንፈስቅዱስ በማህፀኗ የእለት ፅንስ ሆኗል ።ዮሀንስ ወንጌላዊ "ቃል ስጋ ሆነ" በማለት በማህፀነ ማርያም የተፈፀመውን ምስጢረ ተዋህዶ እንደገለፀ መለኮትና ትስብዕት(ስጋ) ያለ መለወጥ ፣ ያለመከፈል ፣ ያለመጨመር ፣ያለ መቀላቀል በእመቤታችን ማህፀን በመዋሀዳቸው ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባህሪ አንድ ባህሪ ፣ከሁለት ፈቃድ አንድ ፈቃድ ፣ ከሁለት ግብር አንድ ግብር በመሆናቸው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ማህፀን የተዋህዶ እምነታችን የተመሰረተበት ስፍራ ሲሆን የመሰረተውም ስጋችንን የተዋሀደው ክርስቶስ ነው

መለኮት ምሉዕ ነው አይዳሰስም አይያዝም አይራብም አይጠማም ዘመን አይቆጠርለትም ። ስጋ ደሞ ይራባል ይጠማል ውስን ነው ዘመን ይቆጠርለታል። ተዋህዶ ስንል እነዚ የስጋን ባህሪያት መለኮት ሳያጠፋው የመለኮትንም ባህሪያት ስጋ ሳያጠፋው በተዋህዶ አንድ ሆነ ። የአብ ልጅ የማርያም ልጅ ተባለ የማርያም ልጅ የአብ ልጅ ተባለ ። መለኮት በተዋሀደው ስጋ ምክንያት ዘመን ተቆጠረለት 30 አመት ሲሞላው ተባለ ፣ ተራበ ተጠማ በስጋ ሞተ ። ስጋም በተዋሀደው መለኮት አምላክ ሆነ ውስን የነበረው ምሉዕ ሆነ ደካማ የነበረው ብርቱ ሆነ ሟች የነበረው ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ ። ድንግልም እንዳትደነግጥ መልዐኩን ልኮ አበሰራት ፍቃዷንም ጠየቃት እሷም እነሆ የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለችው

ከዛች ደቂቃ ጀምሮ ማንም በማይመረምረው መልኩ ከመላዕክትም በተሰወረ መልኩ በማህፀኗ አደረ ።ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ "ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ እንደምን የድንግል ማህፀን ቻለው ? ይላል። ሊቃውንትም በመተባበር እመቤታችን በሰው መጠን ሶስት ክንድ ከስንዝር ስትሆን ርሷ ግን ከጽርሐ አርያም በላይ ርዝመቱ ከበርባኖስ በታች ጥልቀቱ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይመረመር በሁሉ የመላውን አካላዊ ቃል በማህፀኗ የተሸከመች በመሆኗ "የእግዚአብሔር ሀገር " ተብላለች


ይቀጥላል
https://t.me/abagiyorgismnale