Get Mystery Box with random crypto!

ምክር በምሳሌ🦿

የቴሌግራም ቻናል አርማ ababal1 — ምክር በምሳሌ🦿
የቴሌግራም ቻናል አርማ ababal1 — ምክር በምሳሌ🦿
የሰርጥ አድራሻ: @ababal1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.73K
የሰርጥ መግለጫ

ጠቃሚ አባባሎችና የስኬት መንገዶች
ምክሮችን ከታላላቅ ሰዎች
ለኢትዮጲያ ሃገራችን መልካም የሰሩ የሚታወሱበት
ጀግኖችን የምናስብበት፡ ጀግና ለመሆን የምንነሳሳበት
የምንሳተፍበት የምንሸለምበት ቻናል ነው።
ኢትዮጲያዊነትን እንሰብካለን!!
@dav_ab

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-19 22:36:26 የምያቆስለው ብዙ ነው፤ ግን የምፈውስ አንድ አለ።
የምጥል ብዙ ነው ፤ ግን የምያነሳ አንድ አለ።
የምሰብር ብዙ ነው ፤ ግን የምጠግን አንድ አለ።
የምገፋ ብዙ ነው ፤ ግን የምወደን አንድ አለ።

ባይወደን ኖሮ ባይጠነቀቅልን ኖሮ
ባያፅናናን ኖሮ ጣልቃ ባይገባልን ኖሮ
ህይወት በምን ይጠበቃል
የመኖር አቅም ከወዴት ይመጣል
የመራመድ ተስፋ ከየት ይገኛል

አንገታችንን ቀና አድርገን #መራመድ_የቻልነው በኛ ተስፋ ያልቆረጠ #አምላክ እንዳለን ተረድተን ነው።፤

#ፍቅሩ፦ የቆመ የምፀናበት
የወደቀ የምነሳበት
ያዘነ ምፅናናበት
የደከመ የምበረታበት
የተፍገመገመ የምደገፍበት
የተሰበረ ምጠገንበት
➠ህይወትን የምዘራ #ሀይል ነው።
➠መልሶ #መቋቋሚያችን ነው።

#የእግዚአብሔር_ፍቅር_እኛን_ያቆመ_ምሰሶ_ነው።

#አሁንም_እግዚአብሔር_ይወድሃል!!



join us @NWWGC
247 viewsMercy, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:37:31 ሰማይ ያወቀን እንዴት ነው #በክርስቶስ

ህይወት ያገኘነው በማን ነው #በክርስቶስ

አድራሻችን የተለወጠው በማን ነው #በክርስቶስ

ዘላለምን እንዴት ወረስን #በክርስቶስ

በማን አረፍን #በክርስቶስ

የኀጥያት እዳችን በማን ተከፈለ #በክርስቶስ

ከስጋት ነፃ የሆነው በማን ነው #በክርስቶስ

እግዚአብሄርን አባት ለማለት ድፍረት ከየት አገኘን #በክርስቶስ

በአብ ቀኝ ለመሆን ብቃት ከየት አገኘን #በክርስቶስ

ጨለማን፣ ሞትን፣ ኀጥያትን ድል ለማድረግ አቅም ከየት አገኘን #በክርስቶስ

እግዚአብሔር ሰውን በአገልግሎቱ፣ በዝማሬው፣ በነብይነቱ ወይም በፀሎቱ አያውቀውም። እግዚአብሔር ሰውን የሚያውቀው በክርስቶስ ብቻ ነው!!!

አሪፍ የፀሎት ሰው ወይም ጎበዝ ዘማሪ በመሆናችን እግዚአብሔር አይገረምም፤ በመውደቃችን ወይም በመነሳታችንም አይገረምም፤ የአብ መደነቂያ የአብ መገረሚያ አንድ እና አንድ እርሱም ኢየሱስ

መድረኮች ሁሉ የሚገቡት፤ ብቻውን ሊወራለት የሚገባው፤ የአብ ርዕስ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ የሆነው ኢየሱስ

መታወቂያችን፤ መድመቂያችን፤ መዋቢያችን፤ ብቃታችን፤ ሁሉ ነገራችን ኢየሱስ


@NWWGC
435 viewsMercy, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:05:10 ምክር ለሰሚው

ወዳጄ ሆይ !

ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። ከአገሬ በቀር አገር የለም ፣ ከእናቴ በቀር እናት የለም ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም ፣ ከእገሌ በቀር አገልጋይ የለም አትበል ። ጨርሶ መናገር ለዚህ ዓለም ነዋሪ ትዝብት ያተርፍለታል ። በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሰቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም ። ሌላው ሲያለቅስ የሳቁ በኀዘናቸው አጋር አያገኙም ። ካልገዛ በቀር ስጦታውን የሚያቃልል የእግዚአብሔርና የሰው ወዳጅ መሆን አይችልም ። ፍላጎት መልካም ነው ፣ ከልክ ያለፈ መሻት ግን በቀን ሰላም ፣ በሌሊት እንቅልፍ የሚነሣ ነው ።

ወዳጄ ሆይ !

ሲሰበክ እየተኛህ ፣ ሲወራ የምትነቃ ከሆነ አእምሮህን ጠላት እያደባበት ነውና በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተዋጋ ። የዛፍ የመጀመሪያ አካሉ ለስላሳ ነው ። የመጀመሪያ ግንኙነትህም ዕድገት እንዲኖረው በመልካም ፍቅርና ትሕትና ወጥነው ። ሀብታቸውን ሊያሳዩህ ለሚሹ እዘንላቸው ። ከእነርሱ ይልቅ የሠሩት ቤት ዕድሜ አለውና ። አንተም ተመክተህ ያለህን ለማሳየት በተነሣህ ቀን መጀመሪያ መቃብርህን ቆፍረህ ሂድ ።

ወዳጄ ሆይ !

የታረሰ መሬት የዘር ሞትና ትንሣኤ ነው ። የተከፈቱ ልቦችም የቃሉን ዘር ሲያገኙ እኔነትን ቀብረው ፣ አዲስ ሕይወትን ያወጣሉ ። የግል ንግግርን አደባባይ ላይ አታውለው ። ስሜትህን ለማያውቁህ አታስነብበው ። ጥረትህ ኪሣራ ቢያመጣም በዚህ ዓለም እስካለህ ጣር ። የጉባዔ ታላቅነት የሚለካው በሰው ብዛት ሳይሆን በእግዚአብሔር መገኘት ፣ በታላላቆች መታደም ሳይሆን በእውነተኛ አምልኮ ነው ። የሚወጥኑ ፣ የሚገነቡ ብቻ ሳይሆን የሚተቹም ያስፈልጉሃል ። ተቺዎች በነጻ የሚያገለግሉህ የጥራትና ደረጃ ባለሙያዎች ናቸው ። ችላ ተብለህ አድገህ ከሆነ ችላ የተባሉትን አስባቸው ። የእምነት ሰዎች ሲወድቁ ብታይ በጣም አትፍረድ ፣ የመነሻውን ምሥጢርም ያውቁታልና ። ያሉ የመሰሉ ነገር ግን የሌሉ ፣ የሌሉ የመሰሉ ነገር ግን ያሉ ብዙ ሰዎች ናቸው ።

ወዳጄ ሆይ !

ሙሴን ሰው እንዳልቀበረው አስታውሰህ ፣ ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደገነዙት አስበህ ሞትህ ሰርግ እንዲመስል አትጓጓ ። ክፉ ሰዎችን እየተመለከትህ ታዝናለህና ለሚመለከቱህ ኀዘን ላለመሆን ፈሪሀ እግዚአብሔር ይኑርህ ። እግዚአብሔር ለሁሉም ጾታና ወገን ክብር እንዳለው አስብ ። በወንዱም በሴቱም ላይ ይሠራልና ምሉዕ እግዚአብሔርን አታጥብበው ። ሕይወቴ እግዚአብሔር ነው ማለት ቀርቶ ሕይወቴ ሌላ ነው የሚል ሰው ፣ ለመግደል የማይመለስ ጨካኝ ነው ። አንተ የምታስፈልገው ለጠወለጉ ሰዎች ፣ ለተጎሳቆሉ ነፍሶች ነው ። ቃላትህ የድምፅህ አቅም ከሞት የሚመልስ እንጂ ወደ ሞት የሚሰድድ አይሁን ።

ወዳጄ ሆይ !

የጠነከሩ ልቦችን እንደ ወርቅ የሚያቀልጥ የፍቅር እሳት ነው ። ልትደርስበት ያቃተህን ነገር ባዶ ነው ብለህ አትናቀው ። ሲኖርህ ድሀን ካላሰብህ ሳይኖርህ ልታስብ አትችልም ። ስለማንም ሰው ክፉም ደግም በእርግጠኝነት መናገር አትችልም ። የመናገር ብቻ ሳይሆን የመኖር ድፍረትህ እግዚአብሔር ነው ። አንድ የካደ ሰውን ስታሳምን የክርስቶስን መስቀል አገዝከው ማለት ነው ። ንግግር ማብዛት በራስ ላይ ወጥመድ መታታት ነው ።


ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
539 viewsMercy, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:25:59
በረከቱ ብቻ ሳይሆን ሰጭውም የኛ ሆኗል፤
ያለውን ብቻ ሳይሆን #እራሱን ሰቶናል።
ኢየሱስ


@NWWGC
600 viewsMercy, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 12:45:56
እግዚአብሔር ሁሉም በሥራ ላይ ነው።
ወይ እኛን እየሰራ ነው ፤
ወይ የኛን ነገር እየሰራ ነው።
690 viewsMercy Mekete, 09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 09:06:03 "ሰው ከንቱ"
****
ስለ ሰው ከንቱነት ለማውራት ስለ ፈጣሪው ፣ ስለመገኛው ፣ ስለምንጩ ማውራት ተገቢ ነው....የአንድን ፍጡር ማንነት እና ምንነት የሚወስነው ራሱ ፈጣሪው እንጂ ሌላ እሱን መሰል ፍጡር ሰው አይደለም......እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ የሚያየው ክርስቶስ በሚባል ውድ መነጽሩ ነው......የሰው ዋጋ የተተመነው አለማት ሳይፈጠሩ ፣ ኃጢአትም ሳይጀመር ፣ ውድቀትም ሳይመጣ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ነው!!

❝ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።❞
—ኤፌሶን 1: 4

ወዳጄ ሆይ የዋጋህን ውድነት ሳታውቅ ተወደሀል....የዋጋህን ውድነት ባታውቅም ውድ ነህ.....ግን የዋጋህን ውድነት ታውቅ ዘንድ የአብ ፈቃድ ነው!!....እናማ ዋጋህን እወቅ!!


የሰው ዋጋ ያለው መስቀል ላይ በተቤዤው በገዥው እጅ ነው.....የሰው(ያመነም ያላመነም) ዋጋ የፈሰሰለት የክርስቶስ ደም ነው.....የሰው ዋጋ ምትክ ሆኖ የሞተለት የአብ የልብ ትርታ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው....

❝ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።❞
—መዝሙር 49: 12


ሰው ዋጋውን አላወቀም ማለት ዋጋ አልወጣበትም ማለት አይደለም.....ሰው ከንቱ ሀሳብ ያስባል ማለት ሰው ከንቱ ነው ማለት አይደለም.....ሰው ስለነገ አያውቅም ማለት ሰው ከንቱ ነው ማለት አይደለም......ሰው በጌታ አላመነም ማለት ሰው ከንቱ ነው ማለት አይደለም.....ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት ሰው ከንቱ ነው ማለት አይደለም.....እግዚአብሔር ፍቅር የያዘው ከኃጢአተኛ እንደሆነ ላስታውስህ እወዳለሁ(ኢየሱስን የኃጢአተኞች ወዳጅ እንዲሉት!!)

ወዳጄ....ሰው ከንቱ ሲባል Yes የሚለው እግዚአብሔር ሳይሆን ሰይጣን ነው......ሰውን ከንቱ እንደሆነ የሚያሳምነው አዳኙ ሳይሆን ገዳዩ ነው.....የሰውን ከንቱነት የሚሰብከው ሰሪው ሳይሆን መሰሪው ነው.....ሰውን ከንቱ ነህ የሚለው ወዳጁ ሳይሆን አሳዳጁ ነው.....ባጭሩ እግዚአብሔር በልጁ ውድነትህን እንጂ ከንቱነትህን አላስታወቀህም!!

ኧረ ለመሆኑ እንደ ሰው የከበረ ማን አለና ነው ከንቱ የምንለው?.....እንደ ሰው በእግዚአብሔር የተወደደ ያውም እስከ መስቀል ሞት የተፈቀረ ማን አለና ነው ከንቱ የምንለው?....እንደ ሰው ክርስቶስ ራሱን ባዶ ያደረገለት ማን አለና ነው ከንቱ የምንለው?....እንደ ሰው ዋጋ የተከፈለለት በውድ ዋጋ የተገዛ ማን አለና ነው ከንቱ የምንለው?......

አንድኛው መዝሙር ላይ ሰው ከንቱ ነው ስንልና ቀጣዩ መዝሙር ላይ ሰው ክቡር ነው ስንል ሁላኮ አይጋጭብንም....

እንደ አንድ የክርስቶስ አማኝ.....
የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ.....እግዚአብሔር ደሞ ከንቱ ልጅ የለውም!!
የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነኝ.....እግዚአብሔር ደሞ ከንቱ ቤተመቅደስ የለውም

ስለ እኔ የተዋረደው ክርስቶስ ስለ እኔ ሲል ከብሯል!!.....እርሱ በከበረበት ክብር ልክ አክብሮኛል....በተቀመጠበት የክብር ዙፋን ከእርሱ ጋር አስቀምጦኛል!!...በዋጋ ተገዝቻለሁ የራሴ አይደለሁም.....እና ምን ልልህ ነው?

እንኳን ሌላ ሰው እኔ ራሴ ራሴ ላይ ዋጋ አልተምንም!!....የገዛኝ የዋጀኝ ባለቤት አለኝ!! ከንቱ ሳልሆን ውድ ነኝ.....የክርስቶስ አምባሳደር ነኝ!!
ብጹዕ ነኝ....ቅዱስ ነኝ....ጻድቅ ነኝ....ክቡር ነኝ!! ዋጋዬ ጎኑን የተወጋልኝ ነው!!

ወዳጄ ዋጋህ ስንት ነው? ዋጋህን ዋጋ ከከፈለልህ ብቻ ስማ!!

H.A
773 viewsMercy Mekete, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 10:21:49 እኔን ብቻ ስሙኝ
*
ብዙሀኑ "እኔን ብቻ ስሙኝ" በሚሉበት በዚህ ጊዜ አባቱ "እርሱን ስሙት" ያለለትን ኢየሱስን ብቻ ስሙት!!

የክርስቶስ ልብ ያለህ አንተ ሆይ ሊኮንን የጸደቀ ማንም የለም!!

ከመናገርህ በፊት ኢየሱስ ቢሆን ምን ይናገራል በል!!

ከመጻፍህ በፊት ኢየሱስ ቢሆን ምን ይጽፋል በል!!

ከማድረግህ በፊት ኢየሱስ ቢሆን ምን ያደርጋል በል!!

ወዳጄ፦
አንተ እንደሞትክ ክርስቶስ በአንተ ሕያው ሆኖ እንደሚኖር ታውቃለህ?

❝ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ #እኔም_አሁን_ሕያው_ሆኜ_አልኖርም_ክርስቶስ_ግን_በእኔ_ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።❞
—ገላትያ 2: 20

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ሰደቡኝ ብለህ አጸፋ አትመልስም፡፡ #ክርስቶስ_አይሳደብማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ወንድምህ ላይ አትሳለቅም፡፡ #ክርስቶስ_አይሳለቅማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ጥግ ይዘህ አታፌዝም፡፡ #ክርስቶስ_አያፌዝማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ወንድምህን አትኮንንም!! #ክርስቶስ_አይኮንንማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ወንድምህን አታዋርድም፡፡ #ክርስቶስ_አያዋርድማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ ወንድምህን ስታማ አትውልም፡፡ #ክርስቶስ_ሲያማ_አይውልማ!!

አንተ ሞተህ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ ሲገባህ በወንድምህ ላይ አታላግጥም፡፡ #ክርስቶስ_አያላግጥማ!!

ወዳጄ፦
ያጠፋውን መገሠጽ ያላወቀውን ደግሞ ማስተማር ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ክርስቶስን ስበክ!!

መጽሐፍ እንደሚል..........
❝እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ #ሰውን_ሁሉ_እየገሠጽን_ሰውንም_ሁሉ_በጥበብ_ሁሉ_እያስተማርን_የምንሰብከው_እርሱ_ነው፤❞
—ቆላስይስ 1: 28

ማንም የሳተ ቢኖር አበሳጭተህ አትመልሰውም፤ አናደህ አታቃናውም!!

የሰው ቁጣ ትርፉ ለኢየሱስ ወግኖ የኢየሱስ ማደሪያ ላይ መሳለቅ ብቻ ነው!!

❝የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።❞ —ያዕቆብ 1: 20

እኔ ማለት ካልቆመ መበሻሸቅ አይቆምም፤ መበሻሸቅ ካልቆመ እርሱ ማለት አይኖርም፤ እርሱ ማለት ከሌለ እኔ ማለት አይቆምም!!

እርሱን ስሙት!!




#ሄኖክ_አሸብር
739 viewsMercy Mekete, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:55:25     “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፥ ይነሣማል፤”
                    — ምሳሌ 24፥16


      ሕይወት እስካለህ ድረስ መውደቅ አለ ደግሞም መነሳት አለ። ውድቀት ባንተ ፍላጎት ላይ ላይመሰረት ይችላል መነሳት ግን ያንተን ፍላጎትና ውሳኔ ይፈልጋል።

      በዚህ ምድር ላይ ታሪክን የለወጡ፣ ነገርን የገለበጡ ሰዎች አትጠቅሙም የተባሉ ሰዎች ነበሩ። #አልበርት አንስታይን አራት አመት እስኪሞላው ድረስ መናገር አይችልም ነበር። በአስተማሪውም አንተ ለትምህርት የማትጠቅም ሰው ነህ ተብሏል። በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ገብቶ ለመማር ብዙ ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም። ነገር ግን በትዕግስትና በጥረት ፈተናዎችን ተቋቁሞ የክፍለ ዘመናችን ተወዳዳሪ የማይገኝለት ምርጥ የሒሳብ ሊቅና ሳይንቲስት ሆኗል።

      ዛሬ ጠላት አንተኮ አትችልም ይልሃል፣ አንቺኮ እንዲህ አይነት ድክመት አለብሽ ስለዚህ ይህንን ማድረግ አትችዪም ይልሻል፣ ሰዎች ይመጡና ይህ በእናንተ አቅምና እውቀት አይሳካም ብለው ተስፋ ያስቆርጧችኋል። ወዳጆቼ እናንተ ግን ከአይቻልም በላይ አሻግራችሁ ይቻላልን ተመልከቱ። ከተሸነፈበት ጊዜ በላይ አንድ ጊዜ መነሳት የሚችል ሰው አሸናፊ ይሆናል። መውደቅ ችግር አይደለም። ነገር ግን ወድቆ መቅረት ችግር ነው። ተነሳ ምክንያቱም ስኬት የሚጀምረው ከወደክበት በመነሳት ነው።
   
      አንዳንድ ነገሮች የማይቻሉ ዓለቶች ሆነው ውስጣችን ተቀምጠው ይሆናል። እስራኤላውያን ሁሉ ጎልያድን የሚጥል ምንም ኃይል አለው ብለው አላሰቡም። እጣችን ብለው ያሰቡት በእርሱ እንደ እንጀራ ተጠቅልሎ መጎረስና በእርሱ አለንጋ መሞትን ነው። ነገር ግን አይቻልምን አልፎ ማየት የቻለው ብላቴናው ዳዊት ግን ይቻላል ብሎ ተነሳ ትልቁን ትንሽ አደረገው ገዳዩን ሙት አደረገው። በህይወታችን ከእግዚአብሔር ጋር የማንችለው ነገር የለም።

     ዛሬም ወዳጆቼ የውድቀት ዜማን ልናዜም እንችላለን። ደክሞኛል በጤንነቴ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷስ ስለዚህ ራዕዬን መፈፀም አልችልም፤ ገንዘብ በማጣት በጣም እየተፈተንኩ ነው ስለዚህ እቅዴን ዳር ማድረስ አልችልም እያልክ ይሆናል። ለአመታት ምንም ቢገጥምህ እንደምታሸንፍና ጥሰህ እንደምታልፍ ታምን ነበር አሁን ግን ሰልችቶሃል ደክሞሃል የሚሆን አይመስለኝም ማለት ጀምረሃል።

      ወዳጄ በአንተ አይን ፊት ሁሉም ችግር ከባድ ነው። እስቲ ችግርህን በእግዚአብሔር ዓይን ተመልከተው። እስቲ ፈተናህን በእግዚአብሔር አይኖች ተመልከተው።
ፈተናህን የምታልፍበት ገንዘብ የለህም ግን ከገንዘብ በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን ይዘሃል፤ መከራህን የምትጋፈጥበት እውቀትና ጥበብ የለህም ግን ከእውቀትና ከአዕምሮ ጥበብ በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን ይዘሃል።

      አይዞህ አልችለውም የምትለውን የሚያስችልህ ጌታ ካንተ ጋር ነው። አይሆንም የምትለውን ነገር የሚያሳካልህ ጌታ ካንተ ጋር ነው። አንተ ብቻ መሞከርህ እንዳታቋርጥ።
አዶኒ
78 viewsMercy Mekete, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:10:44 "ሕጋዊያን እንደ ሕጉ"

ሺ መልካም ብትሰራ ሺ ዝምታ ነው። አንድ ክፋ ስትሰራ ሺህ ጫጫታ ነው። ተራራ የሚያህለው መልካምነት አይታይም ፣ ጉድፍ የምታህል ጉድለትህ ግን ትጎላለች።

ስትመሰገን አብረው ያላመሰገኑ ፤ ስትራገም ሰልፋን ይመራሉ።

በጎ ስትሆንላቸው ምስጋና በልብ ነው ያሉ ስታስቀይማቸው ግን ርግማን በአዋጅ ነው ይላሉ።

ህግ የሌለ ይመስል ፣ በጎ ስትሰራ ድምፁን ያጠፋል ፣ ትንሽ የበደልህ ቀን ግን ፖሊስ ይልክብሃል ፣ ከሳሽ ፣ ምስክር ዐቃቤ ህግ ያሰናዳባሃል።

ህጋዊያን እንደ ህጉ ናቸው። መልካም ስትሰራ አይሸልሙህም ባህሪያቸው አይደለምና ፣ ክፋ ስትሰራ ግን ይኮንኑሃል። ህጋዊያን ናቸውና።
346 viewsMercy Mekete, 10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 12:59:24 መታገል የማይፈልግ ታምራት እንደ ናፈቀ ይኖራል፤

በተስፋ ብቻ ከጎለቱህ ይልቅ በጦር ያባረሩህ ሰዎች የተሻለ ቦታ ያደርሱሃልላ፤

አላማ የሌለውን የቀኑ ወሬ፣ የሳምንቱ ክስተት ፣የወሩ ፊልም ስወዘውዘው ይኖራል፤

ያለፈ ስህተቱን የምደግም ከእድሜው በታች ኗሪ ነው፤

ታማኝነት እንደ መስታወት ነው አንደ ከተሰበረ እንደ በፊቱ ማየት አትችልም፤

በሰው የዘራኸው ባንተ ይበቅላል ፤

ምኞት ውጭን ስያይ ፍቅር ውስጥን ያያል፤

ፍቅር ተግባር ስያንሰው ማብራርያ ይበዛዋል፤

ምን ያህል አፈቅረዋለው የምለውን የምትለካው፤ያፈቀርከውን ስህተት በታገስከው መጠን ነው፤

ፍቅር ፍፁምነትን ከፈለገ ፍቅር አይደለም።ፍቅር ጎዶሎውን ፍፁም አድርጎ ስመለከት ያን ግዜ ፍቅር ነው።

የፍቅር ዕድሜ ምረዚመው በመከባበር እንጂ በክባድ አይደለም።


@NWWGC
488 viewsMercy Mekete, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ