Get Mystery Box with random crypto!

channel 0

የቴሌግራም ቻናል አርማ aaumuslimstudentsunion — channel 0 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ aaumuslimstudentsunion — channel 0
የሰርጥ አድራሻ: @aaumuslimstudentsunion
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም "ቻናል" ሁሉንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የሚመለከት ነው። በውስጡም ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ አስተማሪ ታሪኮች፣ ለትምህርት ጥንካሬ ሊያግዙ የሚችሉ አስተምህሮቶችና የተለያዩ የሙሐደራ፣ ዳዕዋና መሰል አዘል ኢስላማዊ ዜናዎችና መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው።
አስተማሪና ጠቃሚ የሆነ ጽሁፍ ሲኖራችሁ፣ አስተያየትና ጥያቄ ሲኖራችሁ @Awn1ua ላይ አስፍሩት።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-13 22:40:36 አንድት ሴት ከመገላለጥ
ትጠንቀቅ



አንቺ ውዷ እህቴ ሆይ ዛሬ ላይ ብዙሃን ሴቶች እያደረጉት ያለው ድርጊት ከትልልቅና አፀያፊ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል፦ ከቤታቸው ሌሎችን አማላይና ለራሳቸው የማለሉ ሆነው ተቀባብተው ተውበው መውጣታቸው ትልቅ የፊትና በር ከፋቾች ሆነዋል።

ያም ጌጥን ውበትን መገላለጥ
ሸቶ መቀባባት የተላያዩ ፈታኝ የሰውነት ክፍሎችን ማሳየት ወንዶችን መቀላቀል ይህ አስቀያሚ ድርጊት ይፈፅማሉ በራሳቸውም ላይ የአሏህን ቁጣ ያረጋግጣሉ።


قال الله تعالى: - (وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ٍۖ )
هود (101)

አሏህ እንድህ አለ፦ 【እኛ አልበደልናቸውም ነገር ግን እነሱ እራሳቸውን በደሉ።】
ሱረቱል ሁድ [101]

والله عز وجل يقول : " وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَى " [سورة الأحزاب، الآية : 33].

አሏህ እንድህ አለ፦ ((ቤታችሁ ተቀመጡ የቀደምት የመሀይማንን አገላለጥ አትገላለጡ))።
ሱረቱል አህዛብ [33]

ويقول سبحانه : " وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ " [سورة النور، الآية : 24].

ሉኡሉ ጌታችን ይላል፦ ((ጌጣቸውን ግልፅ አያድርጉ))
ሱረቱ ኑር [24]

وقال النبي صلى الله عليه وسلم «صنفان من أهل النار لم أرهما : قوم معهم سياط كأذناب البقر يضربون بها الناس، ونساء كاسيات عاريات مائلات مميلات رءوسهن كأسنمة البخت المائلة، لا يدخلن الجنة ولا يجدن ريحها، وإن ريحها ليوجد من مسيرة كذا وكذا»
رواه مسلم وغيره

የአሏህ ነብይ እንድህ አሉ፦ «ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ናቸው አሁን አላያቸውም ፤ ሰዎች ናቸው ከነሱ ጋር ሰዎችን የሚደበድቡበት የከብት ጅራት መሰል አለንጋ ያላቸው ፣ እናም ለብሰው ያለበሱ ለራሳቸው የሚማልሉ ሌሎችንም የሚያማልሉ ሴቶች ናቸው ፀጉራቸው እንደተዘነበለ ግመል ሻኛ ነው ጀነት አይገቡም ሽታዋንም አያገኙም…።»
ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል

አንድት ሙስሊም የሆነች ሴት ጠባብ ዘርዛራ የሰውነት ቅርፅን ከሚያሳይ የሰውነትን ውበት ከሚያጋልጥ ልብስ መራቅ ይኖርባታል።

እንድሁም ከመሰባበር ድምፅን ከማቅለስለስና በአካሄድ ሰዎችን ከመፈተን ልትጠነቀቅ ይገባታል።

ከራሷ ላይ ሂጃብ ማንሳት ከደረት ከክንድ ከባት መሰል የሰውነት ክፍሎችን መግለጥን ትጠንቀቅ።
ጋጠ ወጥ የሆኑ ሴቶች የሚለብሱትን አይነት አጫጭር ልብስ ከመልበስ ልትጠነቀቅ ይገባታል።
ይህ አሏህ እርም ክልክል ካደረገው ነገር ስለሆነና እንድሁም ለአደገኛ ፊትና ስለሚያጋልጥ።

قال العلامة ابن باز رحمه الله :
فالواجب الحذر من ذلك، والمرأة عورة وخطرها عظيم على نفسها وعلى غيرها، فالواجب عليها أن تكون بعيدة عن أسباب الفتنة بالتحجب ولبس الجلباب الذي يسترها ...

ኢማም ኢብኑ ባዝ አሏህ ይዘንላቸው እንድህ ነበር ያሉት፦
«ግዴታው ከዚህ ልትጠነቀቅ ነው ፣ ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሃፍረተ ገላ ነው ፣ አደጋዋም በራሷም ሆነ በሌሎች ላይ የከፋ ነው ፣ ግደታው እሷነቷን ልሸፍን የሚችለውን ጅልባብ በመልበስ ከፊትና ምክናየቶች የራቀች ልትሆን ነው…።»

ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሊገለጥ የማይገባው ሃፍረተ ገላ ነው ወደ ሱቅ ስትወጣ ሸይጧን ይክባታል።
ለዚህም ልትሸፈንና ሂጃቧን አጥብቃ ልትይዝ ይገባታል ይህ የሰላም ምክናየት ስለሆነ።

والله يقول سبحانه في كتابه العظيم: (وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ ذَلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ )[الأحزاب:53]،

አሏህ በተከበረው ቃሉ እንድህ አለ፦ 【እቃን ስትጠይቁ ከመጋረጃ ጀርባ ሆናችሁ ጠይቁ ይህም ለናንተም ሆነ ለነሱ ልብ ንፅህና የተሻለ ነው።】
ሱረቱል አህዛብ [53]

እህቴ በመሸፈንሽ የሌሎችንም የራስሽንም ልብ ከተለያዩ በሽታዎች ትጠብቂያለሽ።

እህቴ አሏህ ይዘንልሽ እነዚያ ምርጥ ቆነጃጅት የነብዩ ምርጥ የነብዩ ባልደረቦች የነበሩት ጀግና ሴቶችን ሞደል አድርጊ ፤ እነዚህ ዛሬ ላይ ክብራቸውን ማንነታቸውን አርግፈው የጣሉ ክብራቸው መደፈሩ የማያሳስባቸው የዝንብ መዋያ የሆኑ ሴቶች እስታይል እንዳይሸውድሽ ስልጣኔ መስሎች የስልጣነውን ማማ የስልጣነውን ሰገነት አውልቀሽ አልሰለጠነው አውሬነት እንዳትመለሽ።

ያነበባቹህ በሙሉ ሼር

የሴት ልጅ መስተካከከል
ለኢስላም ኡማ ቁልፍ ነዉ

ለሂዳያ ስበብ አንሁን
ለወድ እህቶቼ አድርሱ

Via, areb genda mesjid jemea
281 views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:13:10
... عيد مبارك ...

أسئل الله ان يوفقنا حج بيته الحرام والوقوف بلعرفة ...

وان يتقبل اعمالنا ويغفر خطايانا ويعننا على ذكره وحسن عبادته وان يثبتنا على صراطه المستقيم ...
406 views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:34:03 የተሟላች ሚስት ሲፈልግ የኖረው ሰው...

አንድ ሕይወቱን ሙሉ ሚስት ያላገባ ሰው ነበር። ይህ ሰው ታዲያ እድሜው 90 ይደርስና ለመሞት ቀናቶች ሲቀሩት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል።

"ሕይወትህን በሙሉ ሚስት ሳታገባ አሳልፈሃል። ያላገባህበትንም ምክንያት ነግረኸን አታውቅም። አሁን ግን ህመምህ እያዳከመህ እንደሆነ እያየን ነውና ያለማግባትህን ሚስጥር ብትነግረን?"

ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ...

"አዎ! ያለማግባቴ ሚስጥር አንድና አንድ ነው። እኔ ያላገባሁት ትዳር ስለምጠላ አልነበረም። ያላገባሁት የተሟላች ሴት ስፈልግ ስፈልግ፥ እድሜዬ ስላመለጠኝ ነው።..."

ጠያቂውም መልሶ እየተገረመ እንዲህ አለ...

"ምድር ሰፊ ሁና፥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እየኖሩባት፥ ከነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ሆነው እያለ ላንተ የምትሆን የተሟላች ሴት እንዴት ልታጣ ቻልክ?"

ሰውየውም እንባው በአይኑ ላይ እየተንኳለለ እንዲህ አለ...

"በርግጥ አንዲት የተሟላች ሴት አግኝቼ ነበር..."

ጠያቂውም ደንግጦና ጓጉቶ እንዲህ አለው...

"እና? ምን ተፈጠረ? ለምን አልተጋባችሁም??"

ሰውየውም....

"አልተጋባንም። ምክንያቱም እሷ የምትፈልገው የተሟላ ባል ነበር..."

እናም ወንድሞቼ! ጥሩ ሚስት ስትፈልጉ ጥሩ ባል፥ አፍቃሪ ስትፈልጉ ተፈቃሪ፥ ወዳጅ ስትፈልጉ ተወዳጅ መሆናችሁን ወደ ራሳችሁ ዞር ብላችሁ ተመልከቱ።

መልዕክቱ ጠቃሚ ነው ብለው ካመኑ ሼር በማድረግ ያጋሩት!

ቤተ-ፈታዋ
515 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:55:15
702 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 12:48:20
ይጠቅማል እንዳያለፋችሁ።
888 views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 21:50:31 ሁሉም ኪታብ ደጋግመህ ባነበብከው ቁጥር ትሰለቸዋለህ። ዋጋው እያነሰ፣ የሚያስጨብጥህ አዳድስ ሀሳቦች እያለቁ ይሄዳሉ። ቁርአን ብቻ ሲቀር። ብዙ ጊዜ ስታበበው ብዙ ጊዜ ይናፍቅሃል። ደጋግመው ስትመልከተው አድስ፣ አሁንም ሌላ አድስ መልእክት ታገኝበታለህ።

T.me/telkhis
519 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 12:51:34 ውድድሩን በጥራት ለመከታተል
የውድድሩን ዋና ዳኛ የፕሮፌሰር ወሊድ ኢድሪስ ሙኒሲን የቀጥታ ስርጭት ሊንክ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1044755316458124&id=100008508851050
491 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:56:43 ለነገው ፕሮግራም በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል።
606 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 08:49:14 ይህ በቪዲዮ ላይ የምትነለከቱት ወጣት አብዱልአዚዝ አብለጢፍ ይባላል ከ 4 አመት በፊት በሳውዲ አለምአቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሲወዳደር ይታያል። አሁን ላይ በ AAU (ሰፈረሰላም ግቢ) የ3ኛ አመት የሜዲስን ተማሪና የጀመአ አስተባባሪ ነው።

ቪዲዮውን በቅርቡ ካየነው ቡሃላ ደስ ብሎናል።
አላህ ይቀበለው።




750 viewsedited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 14:48:21 ማታ ስለ ሲሕር ያነሳሁት ያለምክንያት አልነበረም፡፡

ከሲሕር ጋር ከሀያ ዓመት በላይ የዘለቀ ሃይ ስኩል እያለ በትምህርቱ እጅግ ጎበዝ የነበረ ጓደኛ አለኝ፡፡ ባየሁት ቁጥር ዉስጤ በቁጭት ይነዳል፡፡ ወይ አልሞተ ወይ አልኖረ እንዲሁ አለ፡፡ ለዚሁ ነው ኢስላም የደጋሚዎችን ቅጣት ከባድ ያደረገው፡፡ አንገቱን በሰ *ይፍ ቅሉት ይላለ፡፡ የሰዉን ሕይወት አበላሽተው ለራሣቸው ዘና ብለው የመኖር ተስፋ እንዳይኖራቸው፡፡

የገረመኝ ሙስሊሞች ሆነው ጭምር በሲሕር መኖር የማያምኑ መኖራቸው ነው፡፡ እንደ ኢስላም እጅግ አጥፊ ከሆኑ ሰባት ከባባድ ወንጀሎች ዉስጥ አንዱ ነው ሲሕር፡፡ በቁርኣንም በሐዲሥም የተረጋገጠ ነው፡፡ በተጨባጭም የምናየው የምንሰማው ነው፡፡ ሃኪሞች እንኳን የአንድን ታማሚ ኬዝ አጥንተው፣ በላቦራቶሪም በምንም ፈትሸው ጤነኛ ሲሆንባቸው ወደ መንፈሳዊ ህመም በማስጠጋት እንደየ ሃይማኖትህ ታከም ይሉታል፡፡

ለሁሉም ግን ደጋሚን ለመድገምም ሆነ ለማስደገም የሚያነሳሳው ሒስድ/ ምቀኝነት ነዉና ከምቀኛ ዐይን ይጠብቃችሁ፡፡ ከሰው በበለጣችሁ ቁጥር ተናነሱ እንጂ አትኩሩ፡፡ በጤናም፣ በመልክም በሀብትም አትመፃደቁ፡፡ ከምቀኛ ዐይን ያተርፋቸኋልና አላህ ከሠጣችሁ ከማንኛዉም ፀጋ ላይ ሶደቃ አውጡ፡፡ አላህ የሠጣችሁን ፀጋ ለሌሎችም ይሠጥ ዘንድ ዱዓ አድርጉላቸው፡፡

ምቀኛ ከዐይኑ ከጠፉ የሚመቀኘው ነገር አይኖርም፡፡ ምቀኝቱ የሚታወቅን ሰው አትታዩት፣ ዓላማችሁን አታውሩት፣ ስኬቶቻችሁንም አትንገሩት፡፡ በዚህ ጉዳይ ለተፈተኑትም ሰዎች ዱዓ አርጉላቸው እንጂ አትሳቁ፡፡ ወሬዉንም አታጣጥሉ አትናቁ፡፡ የበዛ ፍርሃትም አይደርባችሁ፡፡
የታመማችሁ እንደሆን ሥር ሳይሰድ በቁርኣንና ሐዲሥ፣ በዱዓ፣ ከወንጀሎች በመራቅና ወደ አላህ በማልቀስ ታገሉት፡፡ ሥነልቦናዊ ምላሻችሁ ጠንካራ ይሁን፡፡ ቢኢዝኒላህ ትድናላችሁ።

በተረፈ ከክፉ ነገር ሁሉ የሚጠብቅ አላህ ነው፤ ጥበቃዉን ተማፀኑ፡፡ ጠዋት ማታ በዚክር ታጠሩ፡፡ ግና እንዲህ ነኝ ብላችሁ በኢማናችሁና በተወኩላችሁ አትመኩ፡፡ በአላህ ጥበቃ እንጂ እኛ ብልሃትም ሆነ ኃይል የለን፡

Muhammed seid Abx
607 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ