Get Mystery Box with random crypto!

በCDT አፍሪካ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት የኮቪድ 19 የሁለት ዓ | Abrehot Library

በCDT አፍሪካ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት የኮቪድ 19 የሁለት ዓመታት ተኩል ጉዞ ተፅዕኖዎች እና ሊወሰዱ በሚገባቸው ትምህርቶች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኮቪድ 19 ባለፉት ሁለት ዓመታት በላይ በመማር ማስተማሩ ሂደትና በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
አሁንም ድረስ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ የተስተጓጎሉ እና የተዛቡ የትምህርት ስርዓቶችን ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ከ50 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የትብብር ስምምነት በመፈራረም ወረርሽኙን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ማገዙን ገልጸዋል።
ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ በወረርሽኙ ዙሪያ ጥናትና ምርምሮች እንዲሰሩ መደረጉን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ዓመታትም ኮቪድን ለመዋጋት እና ለመከላከል የሚያስችሉ 14 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማበርከቱን አውስተዋል።
በተለይ ባለፉት ሁ ዓመታት ተኩል በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ የጥናት እና ምርምር ውጤቶች 50 በመቶ በወረርሽኙ ዙሪያ መሆናቸውንም በመጥቀስ በምስራቅ፣ ምእራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በምርምር ውጤቶች በቀዳሚኒት እንዲቀመጥ አስችሎታል ብለዋል።
ከምርምር ውጤቶች ባለፈ ለኳረንቲን የሚሆኑ ቦታዎች በማዘጋጀት፣ ማስክ፣ ሳኒታይዘር ያሉ ድጋፎችንም በማድረግ እንዲሁም በወረርሽኙ ተፅዕኖ ስር ለወደቁ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰራተኛው ደመወዙን ከማዋጣት ጀምሮ ድጋፍ በማድረግ የመዋጋት ሂደቱ ላይ አስተዋጽኦ ማድረጉን አንስተዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽን ጨርሶ አለመጥፋቱን በማስታወስም ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።