Get Mystery Box with random crypto!

ቀን፡- ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም     የሐዘን መግለጫ   የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና | Abrehot Library

ቀን፡- ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
 
 
የሐዘን መግለጫ
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በኃላፊነት ቦታ ሲያገለግሉ የነበሩት ኮማንደር ዶ/ር ዳንኤል ገ/እግዚአብሔር ሕልፈተ ሕይወት የሰማነው በጥልቅ የሐዘን ስሜት ነው፡፡ ኮማንደር ዶ/ር ዳንኤል ለአመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና በሴፍቲና ሴኪዩሪቲ ዳይሬክተርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲው በቆዩባቸው ጊዜያት ውስጥ ለዩኒቨርሲቲው ያበረከቱት አስተዋፅኦ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምንግዜም ሲታወስ ይኖራሉ፡፡
 
ስለሆነም በመላው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስም በኮማንደር ዶ/ር ዳንኤል ገ/እግዚአብሔር ህልፈት የተሰማንን ልባዊ ሐዘን እየገለጽን ለነፍሳቸው እረፍትን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት