Get Mystery Box with random crypto!

College of Health Sciences . Addis Ababa University .Externale Relations Office

የቴሌግራም ቻናል አርማ aau_chs2013 — College of Health Sciences . Addis Ababa University .Externale Relations Office C
የቴሌግራም ቻናል አርማ aau_chs2013 — College of Health Sciences . Addis Ababa University .Externale Relations Office
የሰርጥ አድራሻ: @aau_chs2013
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 827
የሰርጥ መግለጫ

Tesfaye Solomon Hundie

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 16:18:21
1.0K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:24:42 በህጻናት ላይ የሚፈጠር የስኳር ህመም
የስኳር ህመም አዋቂዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ህጻናትም ላይ ይከሰታል:: ስኳር በየትኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል። የአይነት አንድ ስኳር ህመም በየትኛውም የህጻናት እድሜ ሊከሰት ቢችልም ከ4-6 አመት እና ከ10-14 አመት ባለው እድሜ ክልል የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል። ስኳር በዘር የመተላለፍ እድል አለው። ከአይነት አንድ ይልቅ አይነት ሁለት ስኳር በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
የስኳር በሽታ ሥር የሰደደ የጤና ችግር ሲሆን ይህም በሰውነት ውስጥ ምግብን በተለይም ስኳርን (ካርቦሃይድሬትን) ወደ ሰውነታችን ሀይል የመቀየር ችሎታ ላይ ችግር ይፈጥራል::
ህጻናት ላይ በቀዳሚነት የሚያሳዩት ምልክቶች እነዚህ ናቸው:-
● ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት ፣በተለይም በምሽት ላይ፣
● ተኝቶ ሽንት ማምለጥ፣
● ውሃ ቶሎ ቶሎ መጠጣት፣
● ምግብ ቶሎ ቶሎ መብላት፣
● የድካም ስሜት፣
● ክብደት መቀነስ ወይም እድገት ማቆም፣
● በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ፣
● የማቅለሽለሽ ስሜት
ዓይነት አንድ የስኳር በሽታን ለመመርመር በአንጻራዊነት ቀላል ነው፡፡ ልጅዎ ዓይነት አንድ የስኳር በሽታ ምልክቶች ካጋጠሙዎት፣ እነዚህን ምርመራዎች ያደርጋል::
● በማንኛውም ሰዓት በሚደረግ የስኳር መጠን ምርመራ - በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን 200 ሚሊግራም በዴሲሊተር (ሚግ/ዲኤል)፣ ወይም 11.1 ሚሊሞል በሊትር (mmol/L) ወይም ከዚያ በላይ መሆን የስኳር ህመምን ያሳያል ::
● የA1C ምርመራ - ይህ ምርመራ ላለፉት 3 ወራት የልጅዎ አማካይ የደም ስኳር መጠንን ያሳያል። በሁለት የተለያዩ ምርመራዎች ላይ የA1C ደረጃ 6.5% ወይም ከዚያ በላይ የስኳር በሽታን ያሳያል::
● ከቁርስ በፊት በሚደረግ የስኳር መጠን ምርመራ -ለ 8 ሰዓት ያህል ምግብ ሳይበላ የሚደረግ ምርመራ ነው:: የደም የስኳር መጠን ምርመራ ከ126 ሚ.ግራም/ዴ.ሊ. እና ከዚያ በላይ መሆን የስኳር በሽታን ያሳያል።
ለዓይነት አንድ የሚሰጡት የስኳር በሽታ ሕክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-
● ኢንሱሊን መውሰድ፣
● የስኳር መጠንን መከታተል፣
● ጤናማ ምግቦችን መመገብ፣
● አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ናቸው፡፡
459 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:24:20
380 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 16:53:56
542 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 16:53:38 የጡት ካንሰር
የጡት ካንሰር የሚከሰተው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ ነው። እንደሌሎች ካንሰሮች የጡት ካንሰር በጡት ዙሪያ ወደሚገኝ ቲሹ ውስጥ ገብቶ ሊያድግ እና ሊሰራጭ ይችላል። ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም በመጓዝ አዳዲስ እጢዎችን ሊፈጥር ይችላል።
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር አይነቶች አንዱ ሲሆን ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ በብዛት ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ብዙውን ጊዜ ከ 50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ሲጋራ እና አልኮል መጠቀም ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት ፣ የሆርሞን ወሊድ መከለላከያ ወይም ሌላ የሆርሞን መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም እና የጨረር ህክምና ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋሉ:: በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጅን ከ30 አመት በኋላ መውለድ፣ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት፣ ከ12 ዓመት እድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ 55 ዓመት እድሜ በኋላ የወር አበባ ዘግየቶ መቆም እንደ መንስኤ ሊወሰዱ ይችላሉ ::
የጡት ካንሰር ምልክቶች
● በጡትዎ መጠን ወይም ቅርጽ ላይ ለውጥ፣
● እንደ አተር ትንሽ የሆነ እብጠት፣
● በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የመልክ ወይም የቆዳ ለውጥ፣
● በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የቆዳ መቅላት፣
● ከቆዳው በታች እብነ በረድ የመሰለ ጠንካራ ቦታ መኖር፣
● ከጡት ጫፍ ውስጥ በደም የተበከለ ወይም ንጹህ ፈሳሽ መኖር፣
● የተሠራጨ ዕጢ ከሆነ ደግሞ የደረት ህመም፣ የአጥንት ህመም እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ፣ አልትራሳውንድ፣ እና PET የተሰኙትን ምርመራዎች እንጠቀማለን:: አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል ::
ሕክምናን በተመለከተም ቀዶ ጥገና፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በርካታ የጡት ካንሰር ሕክምና አማራጮች አሉ። ሕክምናው የሚወሰነው ዕጢው ያለበት ቦታ እና መጠን፣ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶች እና ካንሰሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መስፋፋቱን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ነው።
ሕክምናው ቀደም ብሎ ከተሰጠ የመዳን እድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያለበት ሰው በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡
#breastcancer #disease #tikuranbessa, #health, #ህክምና, #ጤና, # ጥቁርአንበሳ, #ጡትካንሰር, #ጡት, #ካንሰር
487 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 16:53:07
354 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 16:48:57 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀላፊነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ሁለት የትምህርት ቤት ዲኖች በክብር ሸኘ፡፡
ኮሌጁ በክብር የሸኛቸው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት ዲን የነበሩትን ዶ/ር ተቅዋም ደበበ እና የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ ትምህርት ቤት ዲን የነበሩትን ዶ/ር ሁሴን መኮንን ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አንዱአለም ደነቀ የሃላፊነት ጊዜያቸውን ላጠናቀቁት የትምህርት ቤት ዲኖች እውቅና ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀትና ትሮፊ አበርክተውላቸዋል፡፡
349 views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:55:23
511 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:54:35 ደም ማነስ

የደም ማነስ የሚከሰተው በቂ ቀይ የደም ሴሎች ሳይኖሩ ሲቀር ነው:: የደም ማነስ የሚባለው የሂሞግሎቢን መጠን ለወንዶች ከ13.5 ግራም/ደሊ በታች፣ ለሴቶች ደግሞ ከ12.0 ግራም/ደሊ በታች ሆኖ ሲገኝ ነው::

ብዙ ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ በአንጀት መታወክ፣ ሥር በሰደዱ በሽታዎች፣ በኢንፌክሽን እና በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት ለደም ማነስ የተጋለጡ ይሆናሉ። በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች፣ እርጉዞች እና ሥር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ለዚህ በሽታ በጣም የተጋለጡ ናቸው።

የተለያዩ የደም ማነስ ዓይነቶች ቢኖሩም እያንዳንዳቸው የሚመሳሰሉበት ነገር አላቸው:: እርሱም በደም ዝውውር ውስጥ ያሉ ቀይ የደም ሴሎች ቁጥር የሚቀንስ መሆኑ ነው::

የደም ማነስ ምልክቶች እነዚህን ያካትታል

● የድካም ስሜት
● ራስ ምታት
● የትንፋሽ ማጠር
● የቆዳ መገርጣት እና መድረቅ
● የልብ ምት መጨመር
● በታችኛው እግር ላይ ያልታሰበ እንቅስቃሴ
● ቀዝቃዛ እጅ እና እግር
● በአንዱ ወይም በሁለቱም ጆሮዎች ላይ ያልተለመደ ድምጽ ወይም ጩኸት

የደም ማነስ ካለብዎት የአይረን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እንደ የበሬ ሥጋ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ለውዝ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፎሊክ አሲድ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች እንደ ሎሚ እና ብርቱካን፣ እና ጥራጥሬዎች መመገብ ይመከራል::

Anemia occurs when there are not enough red blood cells. Anemia is when the hemoglobin level is below 13.5 g / dL for men and 12.0 g / dL for women. Many people are at risk for anemia due to malnutrition, intestinal disorders, chronic diseases, infections and other conditions. Menstruating women, pregnant women and people with chronic health problems are at increased risk.

Although there are different types of anemia, each one has something in common. This is to reduce the number of red blood cells in the bloodstream.

Symptoms of anemia include the following

● Feeling tired or fatigue
● Headache
● Shortness of breath
● Pale and dry skin
● Increased heart rate
● Unexpected movement of the lower leg.
● Cold hands and feet
● An unusual sound or noise in one or both of your ears(tinnitus)

If you have anemia, it is recommended to eat foods high in iron, such as beef, green leafy vegetables, nuts, dairy products, foods high in folic acid, such as lemons, oranges, and grains.
#anemia, #iron, #health, #weightloss, #tikuranbessa, #disease, #ጥቁርአንበሳ, #ጤና, #ህክምና, #ደም, #ደምማነስ
446 views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 17:54:34
396 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ