Get Mystery Box with random crypto!

ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ በአዲስ ቴክኖሎጂ የህፃናት ማቆያ ግንባታ አስጀመሩ ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ኪ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ በአዲስ ቴክኖሎጂ የህፃናት ማቆያ ግንባታ አስጀመሩ

ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ኪዩቢክ ማኑፋክቸሪንግ ከተባለ ኩባንያ ጋር በመተባበር ጥቅም ላይ የዋሉ የኘላስቲክ እቃዎችን ወደ ተገጣጣሚ የግንባታ ግብአትነት በመቀየር በተሰራ  አዲስ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የህፃናት ማቆያ ግንባታ በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ አስጀምረዋል።

ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ የኘላስቲክ እቃዎችን ለግንባታ በሚሆን መልኩ በማምረት ጥራት ጊዜን እና ወጪን በቆጠበ መልኩ እንደሚሰራ በግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርአቱ ላይ በማኑፋክቸሪንጉ ስራ አስኪያጅ ተብራርቷል።

ቴክኖሎጂው ለግንባታ ዘርፉ አዲስ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማምጣቱም በላይ ጥቅም ላይ የዋሉ ኘላስቲኮች አካባቢን እንዳይበክሉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሏል።

ለተቋሙ ሰራተኛ ልጆች ጥቅም ላይ እንዲውል ማስገንባት የተጀመረው  ህፃናት ማቆያ  በቀጣይ ወደጋራ መኖሪያ መንደሮቸ አካባቢም እንደሚቀጥል በእለቱ ተገልጿል።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial