Get Mystery Box with random crypto!

11/12/2014 የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለአጫጭር የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ | የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

11/12/2014
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለአጫጭር የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት በስታንዳርድ የኢንስፔክሽን ቼክ ሊስት ላይ ግንዛቤ ሠጠ።

የትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ባካሄደው የግንዛቤ መስጫ መድረክ ላይ የት/ስ/ጥ/ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ኃ/የሱስ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት
ዳይሬክቶሬቱ በአለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ያለውን ተሞክሮ በመቀመር የኤንስፔክሽን ቼክሊስት በማዘጋጀት እና ግንዛቤ በመስጠት በ2014 ዓ.ም ወደ ምዘና መግባቱን አስታውሰው ሆኖም ኤንስፔክሽን ስራው ከተከናወነ በኃላ እስታንዳርዱ እና ተቋማቱ ያሉበት ሁኔታ መራራቁን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከተማ አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ቼክሊስት ማዘጋጀት በማስፈለጉ ከዚህ ቀደም በተቋማቱ የተሰጡትን አሳቦች እና ያሉበትን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ቼክሊስቱ ላይ ማስተካከያ በማድረግ  ተዘጋጅቷል ፡፡
የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት በአገር ደረጃ የሥራ እድል ከመፍጠር አኳያ ያላቸውን አስተዋጽኦ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መሠራቱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በነዚህ ማሠልጠኛ ተቋማት የሚያልፍ ሠልጣኞች ብቁ የሆኑ ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ ጥራቱን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን የወሰደው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመሆኑ ይህንን መሠረት በማድረግ ቼክ ሊስት የተዘጋጀ ሲሆን ተቋማቱ ወደ ስታንዳርዱ እንዲመጡ ለማስቻል ጥረት ተደርጎል ብለዋል ፡፡ 
ተቋማቱ በቂ ግንዛቤ በመውሰድ ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት የተሻላ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ ኢንስፔክሽን ቼክ ሊስት ሰነድ በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ በአቶ አብርሃም ምትኩ ቀርቧል
ባሳለፍነው በጀት አመት የእስታንዳርድ ኤንስፔክሽን ተደርጎ ተቋማቱ የት ላይ እንዳሉ ለመረዳት መቻሉን ጠቅሰው የትምህርት ስልጠና ጥራት በአንድ አካል ብቻ ስለማይረጋገጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል
በቀረበው ሰነድ ላይ ጥያቄና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በግንዛቤ መስጫ መድረኩ ላይ ከ150 በላይ የሚሆኑ ተቋማት በውይይቱ ላይ መሳተፋቸው ታውቋል ፡፡

#ነጻ የጥቆማ የስልክ መስመር 9302
የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት