Get Mystery Box with random crypto!

10/12/2014 በቀጣይ የሚተገበረው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ መተግበር እ | የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

10/12/2014
በቀጣይ የሚተገበረው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ።

የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጋራ በመሆን በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ከግል የት/ቤት ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ 

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት
የስርዓተ ትምህርት ትግበራው ለዜጎች ሁለንተናዊ እድገት የሚያስፈልጉ የትምህርት ጥራትን መሠረት አድርገው የሚሠጡ እንዲሆን በተለያዩ የትምህርት አደረጃጀት የሚሠጥ መሆኑን ጠቅሰው ባለፈው የትምህርት ዘመን የትምህርት ትግበራው የተገኙ መልካም ውጤቶች እንዳሉ ሁሉ በትግበራ ሂደት የነበሩ ክፍተቶች በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዩች መኖራቸውን አሳውቀዋል፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን የሚተገበረው ሁለት አይነት የስርዓተ ትምህርት አይነት ሆኖ ነባሩ ስርዓተ ትምህርት የሚቀጥልባቸው ሲኖሩ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባባቸው የትምህርት ደረጃዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በትግበራ ሂደቱም በአንደኛው ምዕራፍ አንደኛ ደረጃ በመካከለኛ ደረጃ የሙከራ ትግበራ በ2014ዓ.ም የተከናወነበት እና በ2015 ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባበት ሲሆን በቅድመ አንደኛ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሙከራ ትግበራ የሚደረግ እና በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ ይሆናል
በአገር አቀፍ የተሰራውን ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም ወደ ከተማው በማምጣት የማስማማት ስራ እየተሰራ ሲሆን ትምህርቱ በሚሰጥባቸው ቋንቋዎች ወደ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ የመተርጎም የስርዓተ ትምህርት የማስተማሪያ መፅሐፍ እና የመምህር መምሪያ ማዘጋጀት ስራ በመስራት የመፅሐፍ ህትመት ላይ እንደሚገኝ አሳውቀዋል
በዕለቱ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ በሆኑት በወ/ሮ ፍቅርተ አበራ በግል የትምህርት ተቋማት የስርዓተ ትምህርት አተገባበር ያለበት ሁኔታ በተመለከተ ሰነድ ቀርቧል፡፡በሰነዱ ላይም በተቋማቱ ላይ የሚታየውን የስርዓተ ትምህርት ክፍተት ተዳሶል
ዜጎች የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ስርዓተ ትምህርት በጋራ እኩል መተግበር ያለበት ሲሆን ጥራት ያለውን ትምህርት ለዜጎች ለማድረስ ለሁሉም የባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት መኖር እንዳለበት ወ/ሮ ፍቅርተ አስገንዝበዋል ፡፡
በተጨማሪም በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም  በተመለከተ በትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በአቶ አድማሱ ደቻሳ ሰነድ ቀርቧል፡፡ በቀረቡት ሰነዶች ላይ በተሰታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ቀርቧ ውይይት ተደርጎበታል
በውይይት መድረኩ ላይ ከትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

#ነጻ የጥቆማ የስልክ መስመር 9302
የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
"ከኮሮና ቫይረስ ራስዎንና ሌሎችን ይጠብቁ"