Get Mystery Box with random crypto!

አድዬ የኔ.... / Adama Ketema F.C

የቴሌግራም ቻናል አርማ aadamaa — አድዬ የኔ.... / Adama Ketema F.C
የቴሌግራም ቻናል አርማ aadamaa — አድዬ የኔ.... / Adama Ketema F.C
የሰርጥ አድራሻ: @aadamaa
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.36K
የሰርጥ መግለጫ

....... ╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗....…
║ እንኳን ደህና መጡ ║
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
ይህ ቻናል የአዳማ ከነማ ደጋፊዎች ቻናል ነው።
ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎችን በቀጥታ ከ ስታድየም ከማህበራዊ ድረገፆች ፣ አዴን የተመለከቱ ማናቸውንም መረጃ እናቀርባለን፡፡
★አዴን ለመደገፍ ብዙ ምክንያት አለን★
ለአስተያየት ✍፡
@AdamaCityFC_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 21:00:42
ዋልያው አቻ ተለያይቷል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ባደረገው የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል ።

ዋልያዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን በቀጣይ ሳምንት ነሐሴ 28 በሩዋንዳ የሚያደርጉ ይሆናል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር የሚያደርገውን የደርሶ መልስ ጨዋታ ካሸነፈ ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል ።
709 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:18:37
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !

በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚካፈሉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ዋልያው የመጨረሻ ማጣርያ ጨዋታውን ከ ሩዋንዳ ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ያከናውናል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ጨዋታ የሩዋንዳ አቻቸውን ካሸነፉ ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ ።
795 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:57:58 አዳማ ከተማ ወሳኝ ዝውውሮችን ፈፅሟል!

በ2014 የውድድር ዘመን በሊጉ መቆየቱን ለማረጋገጥ የመጨረሻ ሳምንታት ጨዋታ ውጤቶችን ለመጠበቅ የተገደደው ክለባችን ለ 2015 የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን በዋና አሰልጣኝነት ለማስቀጠል ከወሰነ በኃላ በዝውውር ገበያው እንብዛም ሲንቀሳቀስ ባለመታየቱ ብዙ መሻሻሎችን የሚሻው ቡድን ዝምታን መርጦ መቆየቱ በብዙዎች ዘንድ ቀጣይ የውድድር አመት በምን መልኩ ሊቀርብ ነው በሚል ጥያቄን ሲፈጥር የነበረ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። ዘግይቶ ወደ ዝውውር ገበያ የገባው ክለባችን ክለቡን ያጠናክራሉ የተባሉ ወሳኝ አዳዲስ ዝውውሮችን ሲፈፅም የነባሮቹንም ውል አድሷል።

አንጋፋው የብሄራዊ ቡድናችን አማካይ መስኡድ መሀመድ መዳረሻው አዳማ ከተማ ሆኗል። የእግር ኳስ ህይወቱን ለመብራት ሀይል በመጫወት የጀመረው ባለ ብዙ ልምዱ አመለ ሸጋው ተጫዋች ያለፈውን የውድድር ዘመን በጅማ አባጅፋር ቆይታ ካደረገ በኃላ ለአዳማ ከተማ ለመጫወት ተስማምቶ ፊርማውን አኑሯል።

ብዙ ውዝግቦች የነበሩበት የዊልያም ሰለሞን ዝውውርም እልባት ሲያገኝ መዳረሻውን አዳማ ከተማ በማድረግ ተቋጭቷል። ወጣቱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ከሲዳማ ቡና ጋር የቅድመ ውል ስምምነት አድርጎ የነበረ ቢሆንም እልህ አስጨራሹ የዝውውር ሂደት በመጠናቀቁ
ለቀጣዩ 2 አመታት በክለባችን መለያ የምንመለከተው ይሆናል።

ቦና አሊ እና አድናን ረሻድም በዝውውር መስኮቱ ክለባችንን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነው ተመዝግበዋል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከሊጉ በተሰናበተው ጅማ አባጅፋር ቆይታ የነበራቸው ሲሆን ምንም እንኳን ክለቡ በሊጉ መቆየት ባይችልም በግላቸው ጥሩ የውድድር አመት ካሳለፉ በኃላ ቀጣዮቹን አመታት በክለባችን ለመቆየት ተስማምተው ፊርማቸውን አኑረዋል።

ግብ ጠባቂው ሰኢድ ሀብታሙ ጀማል ጣሰውን ተክቶ አዳማ ከተማ ደርሷል። ያለፈውን የውድድር አመት በወልቂጤ ከነማ ያሳለፈው ግብ ጠባቂው በቀጣይ በክለባችን የምንመለከተው ይሆናል።

ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብ ለተጨማሪ 2 አመታት ውሉን አራዝሟል። ያለፉትን 2 አመታት ከክለባችን ጋር ቆይታ የነበረው የቀኝ መስመር ተከላካዩ በሂደት በሚያሳየው ጥሩ ብቃት እና መሻሻል በደጋፊው እጅጉን ከሚወደዱ ተጫዋቾች መሀል እራሱን ማስቀመጥ ችሏል። ተጫዋቹ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በርካታ የዝውውር አማራጮች የነበሩት ቢሆንም ውሳኔው ግን ከአዳማ ከነማ ጋር ለመቆየት ሆኗል።

ክለባችን በቀጣይም ተጨማሪ ተጨዋቾችን ለማስፈረም በድርድር ላይ የሚገኝ ሲሆን ዝውውሮቹ እንደተጠናቀቁም ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

ክለባችንን አስመልክቶ ትክክለኛ እና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ የሆነውን የፌስቡክ እና የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ!
አድዬ የኔ. / Adama kenema
t.me/AAdamaa
1.9K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:56:58
1.4K views19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 14:32:47
የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ሙሉ ፕሮግራም
2.0K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 11:44:32
የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ሳምንት ፕሮግራም

ኢትዮጵያ መድህን ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ፋሲል ከነማ ከ አዳማ ከተማ
መቻል ከ ሀድያ ሆሳዕና
ሀዋሳ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
ባህር ዳር ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ወልቂጤ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

የውድድሩ ቀን እና ሰዓት ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል

ሀትሪክ
1.6K viewsedited  08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:21:55
እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያ በድምር ውጤት ደቡብ ሱዳንን 5 ለ 0 አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።

የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና የማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ውጤት

ደቡብ ሱዳን 0 - 5 ኢትዮጵያ

(32' ረመዳን የሱፍ ፣ 33' አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፣ 66' ፒተር ሜከር (በራስ ግብ ላይ) ፣ 86' መስዑድ መሐመድ ፣ 90' ይገዙ ቦጋለ)

- ዋልያዎቹ በቀጣይ ሩዋንዳን የሚገጥሙ ይሆናል።
2.0K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:38:07
#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል።

#ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው።

በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

ከተገኙት አራት #ወርቆች መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው።

ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ?

ወርቅ

ለተሰንበት ግደይ
ጉዳፍ ፀጋይ
ጎተይቶም ገ/ስላሴ
ታምራት ቶላ

ብር

ወርቅውሀ ጌታቸው
ሞስነት ገረመው
ለሜቻ ግርማ
ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ

ዳዊት ስዩም
መቅደስ አበበ

አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው።

የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል።

ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል።

እንኳን ደስ አለን !
2.1K views03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:19:14
749 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 16:14:30
ካኑ መከላከያ የተቀላቀለ ሌላኛው የ ቀድሞ ተጫዋቻችን !
831 viewsedited  13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ