Get Mystery Box with random crypto!

  ራስን መተሳሰብ አንድ ሙእሚን ሁሌ ራሱን ሒሳብ ማድረግ አለበት። እየአንዳንዱ ሰው ነገ አላ | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

  ራስን መተሳሰብ

አንድ ሙእሚን ሁሌ ራሱን ሒሳብ ማድረግ አለበት። እየአንዳንዱ ሰው ነገ አላህ ፊት ቆሞ ሒሳብ ይደረጋል። ዛሬ ዱንያ ላይ ራሱን ሒሳብ ካደረገ የዛን ቀን ሒሳብ ይቀልለታል። ስለዚህ ለየአንዳንዱ እንቅስቃሴ ሒሳብ ያስፈልገዋል። በተለይ አሁን ያለንበት የረመዳን ወር የመጀመሪያው 10 አልቆ ሁለተኛው አስር ተጀምሯል። እየአንዳንዱ ቀን የሰራንበትን ይዞ ላይመለስ ይሄዳል የቂያማ ቀን ነው የምንገናኘው።
 
➲ ይህ ከረመዳን ውጪም የሚቀጥል ሂደት ነው። ታዲያ ይህ ስራችንን በምናስቀምጥበት የጊዜ ካዝና ምን አለን ብለን ማየት ብልህነት ነው።
ነገ አላህ ፊት ያለው ምርመራ እኛ አይደለንም የአላህ መልእክተኛና ሶሓቦቻቸውም የፈሩት ነው። 
ለዚህ ነው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ እንዲህ የሚለው፦
قال عمر بن الخطاب – رضي الله عنه:-
"حاسبوا أنفسكم قبل أن تحاسبوا، وزنوها قبل أن توزنوا، فإنه أهون عليكم في الحساب غداً أن تحاسبوا أنفسكم اليوم، وتزينوا للعرض الأكبر، يومئذ تعرضون لا تخفى منكم خافية"
أخرجه الإمام أحمد والترمذي بسند صحيح

"ከመመርመራችሁ በፊት ራሳችሁን መርምሩ (ሒሳብ አድርጉ ), መዝኑዋት ከመመዘናችሁ በፊት, ነገሩ ዛሬ ራሳችሁን ሒሳብ ማድረጋች ለነገ ሒሳባችሁ የቀለለ ነው። ለትልቁ ቀን መቅረብ ተሸለሙ (ተዘጋጁ) የዛን ቀን ከናንተ የሚደበቅ ነገር ሳይደበቅ ትቀርባላችሁ።"

➪ ሰለፎች አኼራን በዚህ መልኩ ነበር የሚያዩት እስኪ ራሳችንን እንይ!!! ያለፈውን እያሰብን መድከም አያስፈልግም አሁን ያገኘነውን እድል ተጠቅመን ተውበት አድርገን እንመለስ ራሳችንን እናዘጋጅ።

https://t.me/bahruteka