Get Mystery Box with random crypto!

ጀግና ወንድ ምላሹ ምላሷ ረዝሞባት ቀሚሷ ካጠረ ሀያዋ መንምኖ ልብሷ ከተወጣጠረ ምግባሯ ተሰልቦ | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

ጀግና ወንድ ምላሹ

ምላሷ ረዝሞባት ቀሚሷ ካጠረ
ሀያዋ መንምኖ ልብሷ ከተወጣጠረ
ምግባሯ ተሰልቦ ገለዋ ከተገላለጠ
ኢማኗ እልም ብሎ ድምጿ ሀገራ ካናወጠ
በዙረት ብዛት እግሯ ከቀጠነ
መቃጠል ቀርቶባት ባህሪዋ ካልሰከነ
አካሏ በሙሉ በሽቶ ካበደ
ሰዉረኝ ጌታዬ በእዝነትህ ይሁንና
በዱኒያም በአኼራ አያዋጣምና።

ጀግና ሴት ምላሿ

ሱሪዉ መሬት ወርዶ ፂሙን ካሳጠረ
ለቢዳዓ ብሎ ከተሰባበረ
ፍየል መሆን አምሮት ጫቱን ከጎረሰ
ስርዐት አልባ ሆኖ እራሱ ከረከሰ
ቤቱን ማያስከብር ደዩስም ከሆነ
በአረህማን ብቻ ዉስጡ ካላመነ
ሰዉረኝ ጌታዬ ከንዲ አይነት ልፍስፍስ
በዱንያም በአኼራ ሰላሜ  እንዳይፈርስ።


የቴሌግራም ቻናላችን
#join
ያድርጉና ይቀላቀሉ

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
   ሼር JoiN & Share
https://t.me/AAASELEFYA