Get Mystery Box with random crypto!

' ደልቶሻል አትበሉኝ ' ........በእኔ ቦታ ሁነው ~~ ኑሮዬን ሳይኖሩት ሲባል ውጭ ሀገር | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

" ደልቶሻል አትበሉኝ "

........በእኔ ቦታ ሁነው ~~ ኑሮዬን ሳይኖሩት
ሲባል ውጭ ሀገር ነው~~በምቾት ስለውት
....አንችማደልቶሽ ነዉ
ብዙ አመት የኖርሽው ~~ብለው የሚያወሩት

...ባያውቁት እኮ ነው

ደስታ እና ፈገግታ ~~ ከላዬ ላይ ጠፍተው
እንቅልፍ እና እረፍት~~ከእኔ ዘንድ እረቀው
በይሆናል ተስፋ ~~ አካሌን አፅንቼ
ልቤን በሙሉ እምነት~~በተስፋ ሞልቼ
ናፍቆት ባይገታ ~~ ጉልበቴን ታቅፌ
በእንባ ጠብታ ~~ ልቤን አሸንፌ

አንዱ ሞላልኝ ስል ~~ አንዱ እየጎደለ
ነገ ወይ ዛሬ ስል ~~ልቤ ሁለት ቦታ እንደ ተከፈለ

......እስከዛሬ ድረስ ~~ሳይፈታ ህልሜ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ~~ ተስፋን ተሸክሜ
ለነገ እንደምኖር ~~ ለዛሬ ደክሜ

እናም ወዳጆቼ

የጥርሴን ፈገግታ ~~ ከውጭ እያያችሁ
የልቤ ኡኡታ ~~ፍፁም ሳይገባችሁ
ደልቶሻል አትበሉ~~ተውኝ እባካችሁ

https://t.me/umufwzan/5541
https://t.me/umufwzan/5541