Get Mystery Box with random crypto!

አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡ ወጣትነትህን ከማርጀትህ በፊት | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡

ወጣትነትህን ከማርጀትህ በፊት
ጤንነትህን ከመታመምህ በፊት
ሀብትህን ከመደህየትህ በፊት
ትርፍ ጊዜህን ከመጨናነቅህ በፊት
ህይወትህን ከመሞትህ በፊት

የአሏህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሲናገሩ " ሕዝቦች አምስት ነገሮችን በመውደድ ከአምስት ነገሮቺ ይዘናጋሉ" ካሉ በኀላ ሲዘረዝሯቸው እንዲህ አሉ:

ሕይወትን ያፈቅሩና - ሞትን ይረሳሉ:

ዱንያን ያፈቅሩና -አኼራን ይዘነጋሉ፡

ህንፃ መገንባት ይወዱና - ቀብር መኖሩን ይዘነጋሉ፡

ገንዘብ ይወዱና - ከሒሳብ ( በቂያማ ግዜ መተሳሰቡን ) ይዘነጋሉ ፡

ፋጡራንን ያፈቅሩና - ፈጣሪን ይዘነጋሉ ፡፡
አሏህ ከዚህ ተግባር ይጠብቀን ኣሚን ፡፡