Get Mystery Box with random crypto!

ማለዳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ aaabbbeeelllaaa — ማለዳ
የቴሌግራም ቻናል አርማ aaabbbeeelllaaa — ማለዳ
የሰርጥ አድራሻ: @aaabbbeeelllaaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 516
የሰርጥ መግለጫ

ካነበብኳቸው መጣጥፎች እነሆ
Join us
https://t.me/aaabbbeeelllaaa

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-09 09:36:37 ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡
መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡
ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡
እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ መልክ
የላይ ማንነትን እንጂ የውስጥ ሰብእናን አይገልጥም ፡፡
ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣ ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው
204 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 18:47:33 ናስሩዲን ከተከታዮቹ ጋር በአጀብ ሆኖ በአንድ የገበያ ስፍራ ያልፋል። ምንም ነገር ቢያደርግ ተከታዮቹ የሚያደርገውን ይደግማሉ። ጥቂት ራመድ ይልና እጆቹን ሰቅሎ ይወዘውዛል፣ ዝቅ ብሎ እግሮቹን ይነካል፣ ወደላይ እየዘለለም ይጮሃል። ተከታዮቹም እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ሳያዛቡ ይደግማሉ።

ታዲያ አንድ ነጋዴ ወዳጁ " ምን እያደረክ ነው የዱሮ ጓዴ? እነዚህ ሰዎችስ ለምንድነው የምታደርገውን የሚያስመስሉት? " በሚል ይጠይቀዋል

"የሱፊ ሼክ ሆንኩ እኮ! እነዚህ ደግሞ መንፈሳዊነትን ለመለማመድ የተከተሉኝ ተማሪዎቼ ናቸው ። ወደ መንፈሳዊ አብርሆት ይሸጋገሩ ዘንድ እየረዳኋቸው ነው። " ናስሩዲን መለሰ።
ወዳጁ ግራ ተጋብቶ ጠየቀ። "አሃ! አብርሆት ላይ መድረሳቸውን በምን ታውቃለህ?

ናስሩዲንም " ያ ቀላል ነው። በየማለዳው ተከታዮቼን እቆጥራቸዋለሁ። ከሰልፉ የጎደሉት በርቶላቸዋል ማለት ነው!"

P.S: የናስሩዲን አይነት አሰላፊዎች ሞልተውናል። አሰላፊዎቹ የስሜት ህዋስህን በገዛ አንጎላቸው ያዙታል።

ባላበጀኸውና ባልፈተሽከው ሃሳብ ላይ ተለጥፎ ሰልፍ ውስጥ ራስህን ካገኘኸው "ዘናጭ በግ" ሆነህ ሰዎችን ተከትለህ አትትመም!
220 viewsedited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 09:37:51 በጎ ሃሳቦች የስኬታማ ሕይወት ማስፈንጠሪያ ናቸው። ልበ ሙሉነትና ጉልበትን እየሰጡ በራስ የመተማመን ስሜትን ከፍ የማድረግ ሀይል አላቸው። በጎ አስተሳሰብ የማነቃቂያ ሃሳቦች ማለት አይደሉም።

ከማንነትህና ፣ ከስብዕናህ ጋር ተሰናስለውና በልክ ተሰፍተው ከሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎችህና ተግባራቶችህ ጋር ተመጣጥነው በልኬት የሚመዘኑ ናቸው። ይበልጥ በጎና ቀና አሳቢ በሆንክ ቁጥር ፣ በሁለንተናዊ ሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛና ስኬታማ እንድትሆን ማስቻል አለባቸው።

አሉታዊ አስተሳሰቦችን ደግሞ በተቃራኒው መልኩ ልንረዳቸው እንችላለን። ደካማ ፣ እርባናቢስና ፈሪ እንድትሆን በማድረግ በራስ መተማመንህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ ዜሮ እንዲገባ ያደርጉሃል። አሉታዊ ሃሳብን ባሰብክ ቁጥር በውስጥህ ያለውን የመለወጥና የቀናነት መንፈስ ከእጅህ እንዲወጣ ታደርጋለህ።

በዚህም ተናዳጅና የተከላካይነት ስሜት ይጋባብሃል። በአሉታዊ አስተሳሰብ ውስጥህ መቃኘት ሲጀምር ፍርሀት፣ ተጠራጣሪነትና ሀዘን ውስጥህን እየተፈራረቁ መጎብኘት ይጀምራሉ።
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ይህ አሉታዊ አስተሳሰብህ ሙሉ በሙሉ ሰውነትህን ይቆጣጠረውና ራስህን ከመጉዳት አልፎ ከሌሎች ጋር ያለህም የርስ በርስ ግንኙነት እስከማበላሸት ይደርሳል።

ከአሉታዊ አስተሳሰብ በተቃራኒው በጎ(አወንታዊ) አስተሳሰብ በአንጻሩ ለአእምሮ ጤናና ለተሻለ የስራና የመንፈስ አፈጻጸም በርን ይከፍታል።

ስትኖር ደስተኛና ጤናማ ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግክ በጎ አስተሳሰብህን እያዳበርክ አሉታዊ አስተሳሰብህን ተጠራጣሪ ስሜትህን ከአእምሮህ ጠርገህ ማውጣት እንዳለብህ ይመከራል።

መልካም ቀን
254 views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 09:23:26 የጠቢቡ ሉቅማን ምክር ለልጁ…

ልጄ ሆይ፣ በዝምታዬ ተፀፅቼ አላውቅም…
ልጄ ሆይ፣ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አትጨምር
ልጄ ሆይ፣ ምላስህን 'ፈጣሪ ሆይ ማረኝ' ማለትን አለማምድ፡፡ ለፈጣሪ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት አሉትና፡፡
ልጄ ሆይ፣ ጥበብ(እውቀት) ምስኪኖችን የነገሥታት ደረጃ አድርሳለች፡፡

ልጄ ሆይ፣ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች፡፡
ልጄ ሆይ፣ ከመገረም ጋር አትሳቅ፣ ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡
ልጄ ሆይ፣ ሁለት ነገሮችን አታውሳ፤ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና፣ ለሰዎች ያደረግከውን መልካም ነገር፡፡

ልጄ ሆይ፣ በጣም ጣፋጭ አትሁን እንዳትዋጥ፤ መራራ አትሁን እንዳትተፋ፡፡
ልጄ ሆይ፣ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ፤ ከምትመገበው ለውሻ ብትጥለው የተሻለ ነው፡፡
ልጄ ሆይ፣ የፈጣሪን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው፤ ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡፡

ልጄ ሆይ፣ አደራህን በብድር ላይ፤ ብድር የቀን ውርደት የማታ ጭንቀት ነው፡፡
ልጄ ሆይ፣ የማይረዳን ከማስረዳት ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል፡፡
ልጄ ሆይ፣ ባወከው ነገር እስከምትሰራ ያላወከውን አትማር፡፡

ልጄ ሆይ፣ መጥፎ ጎረቤት ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል
ልጄ ሆይ፣ መራራ ነገሮችን ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር አልቀመስኩም፡፡
ልጄ ሆይ፣ አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ ካለፍክ... ካልሆነ ተጠንቀቀው፡፡

ልጄ ሆይ፣ በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ ዓይንህን ጠብቅ፤ በስብስብ መካከል ከሆንክ ምላስህን ጠብቅ፤ በጸሎት/ሰላት ውስጥ ስትሆን ልብህን ጠብቅ፡፡
273 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 10:23:28 01) ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም
ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!
02) ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም
ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
03) ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም
በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!
04) አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም
ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!
05) ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም
በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!
06) ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!
07) ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!
08) ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት
አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ
ማለት እንጂ!
09) ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም
ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!
10) ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም
ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!
11) ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም
ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ
ሁን ማለት እንጂ!
12) እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት
አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!
13) አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም
ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!
14) ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም
ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!
15) ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም
አምሮብሃል ማለት እንጂ!
16) አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም
ብልህ ሁን ማለት እንጂ

መልካም ቀን
325 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 15:33:16 ይሄን ያውቃሉ ?
በኢትዮጵያ ውስጥ ለ፮(6) ሰዓታት ብቻ የነገሠ ንጉስ አለ ።
ንጉስ #አይዙር ይባላል ።

ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከ ፯፻፶፱-፯፻፯፪ (759-772) ዓ.ም ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ የነገሰው ንጉስ #ኦደጎሽ ለ ፲፫ (13) ዓመታት ያክል ሲሆን ከ ፯፻፯፪-፯፻፯፯ (772-777) ድረስ ደግሞ ለ፭ (5) ዓመታት የነገሰው ንጉስ #ድድም ይባላል ።
እንግዲህ በነዚህ ንጉሶች መካከል ፯፻፯፪ ላይ የተፈጠረ ክስተት ነው ንጉስ ኦደጎሽ ከንግስናው ወርዶ የተተካው ንጉስ አይዙር ነበር ከ 6 ሰዓት በኋላ ግን ንጉስ ድድም መንበረ ንግስናውን ያዘ ።
ያው ዘመኑ ዘመነ መሣፍንት ስለነበር ንጉስ ድድም የንግስናውን ዙፋን እንዴት እንደያዘ ማስረዳት አይጠበቅብኝም ።

ለጦማሩ ምንጭ የሆነኝ :- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክብር በጥራዝ መልክ የተቀመጠው የነገስታት ዜና መዋዕል ነው ።

ከፌስቡክ መንደር
300 views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 06:35:06 አንዱ ከ 12 አመት በኋላ ፍርድ ቤት ይሄድና ጎረቤቱን ይከሰዋል።

የክስህ ምክኒያት ምንድነው? ሲባል
''ከዛሬ 12 አመት በፊት አዉራሪስ ብሎ ሰደሰቦኛል!''
ዳኛዉ ፈገግ ብሎ''ጎበዝ ከ 12 አመት በኋላ ስድቡ እንዴት ትዝ አለህ''ሲባል

''ዛሬ አይደል እንዴ አዉራሪስ ምን እንደሚመስል ያየሁት''

ተስፋሁን ከበደ/ፍራሽ አዳሽ

መልካም ቀን
310 views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 22:29:55 #ቀኖች
በየእለቱ እጅግ የሚያስደንቁን ነገሮች ይፈጠራሉ።በሁሉም ነገር የምንደሰትባቸው ከት ብለን የምንስቅባቸው ዳግም መወለዳችንን የምንናፍቅባቸው ቀኖች አሉ።
በጣምም የሚያሳዝኑን እንባ እንባ ሚለንም ቀን አለ
እምባ እምባ ማለት ብቻ አደለም ደም እንባ የሚያስነቡ አቁሳይ ማንነት ጋ የተቆራቸኙ በክፉ ማንነት ክፍ ቀን የምንላቸው እለታት የትየለሌ ናቸው።
አንዳን ቀኖች ደሞ አሉ በሚገርም ሁኔታ የማናውቃቸውን ነገሮች የምናውቅባቸው በሕይወታችን አዲስ ምን አልባትም አዲስ ምዕራፍ ሊከፍቱልን ምን አልባትም በጎርባጣ መንገድ የዛሉ እግሮቻችንን የሚያሳርፉ ሕይወታች የሚቆጠቁጡ ብሩህ ቀናቶች አሉ።
ደግሞ በጣም የሚያናድዱን ነገሮች ሁሉ ባልጠበቅንበት ሁኔታ የሚመሩብን እራሳችንን መቆጣጠር እስከማንችልባቸው ደረጃዎች እምንደስባቸው ቀናቶች አሉ።
ከሁሉም ደግሞ ሁሉ ነገር የሚታክተን ኑሮ ሕይወት ትርጉማቸው እስኪጠፋን ሞታችንን የምንመርጥባቸው ቀኖች አሉ።
በዚህ ሁሉ ግን ሀቅን ከታጠቅን የማንሻገራቸው ቀኖች አይኖሩንም።

መልካም አዳር
302 views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 13:33:41 ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በቅድሚያ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን እስኪ ከበአል ጋ ያላችሁን ገጠመኝ በዉስጥ መስመር ጀባ በሉን።

በድጋሚ መልካም በአል

@Enatu16
293 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 11:21:16 ሦስቱ ያባቴ ምክሮች (ከሞት ነጋዴው የተቀነጨበ)
***
ልጅ እያለሁ እጅግ በጣም ራስ ወዳድና ሁሉንም ነገር ለኔ ባይ ነበርኩኝ” አሉና ጀመሩ ጨዋታ ቢጤ... እኝህ ማናቸው የቻይናው ፕሬዝዳንት? ‘ሺ ጂንግ ፒንግ’ የሚሏቸው ሰውዬ። አልፎ አልፎ እንዲህ በል ሲላቸው በንግግራቸው መሀል ስላሳለፉት የልጅነት ጊዜ ያወራሉ። አሁንም ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ወደኋላ በትዝታ ተመልሰው ልጅ ሳሉ የሰሯቸውን ተንኮሎች በዝምታ ሲያሰቡ ቆዩና ቀጠሉ ንግግራቸውን።
“ራስ ወዳድ ከመሆኔ የተነሳ ሁልጊዜም ጥሩ ጥሩውን ለራሴ ነበር የምወስደው። ይኽ ባሕሪዬ ቀስ በቀስ ጓደኛ እያሳጣኝ መጣ። በመጨረሻም ጓደኞቼ ሁሉ ሸሽተውኝ ጓደኛ አልባ ሆንኩ። እኔ ግን ጥፋቴ ምን እንደሆነ አልገባኝም ነበር። ጓደኞቼ ስለሸሹኝ ኮነንኳቸው እንጂ ምን እንዳጠፋሁ ራሴን አልጠየኩም። ችግር እንዳለባቸው አሰብኩ እንጂ ችግር እንዳለብኝ አልፈተሽኩም። ቢሆንም አባቴ ሕይወትን በመልካም መንገድ እንዴት መምራት እንደምችል በተግባር አስተማረኝ።
“የአባቴ የሕይወት ትምህርት ሦስት ደረጃዎች ነበሩት።
“አንድ ቀን አባቴ ለሁለታችን የሚሆን ምግብ አዘጋጀና በሁለት ሳህን ከፍሎ የምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። የተዘጋጀው ምግብ ፓስታ በእንቁላል ነበር። አባቴ ፓስታውን ሲያስቀምጠው በአንደኛው ሳህን ከፓስታው በተጨማሪ የተቀቀለ አንድ እንቁላል ከአናቱ አድርጎበታል። በሌላኛው ሳህን ግን ከፓስታው በላይ እንቁላል የሚባል ነገር የለበትም። ከዚያ አባቴ ወደ እኔ እየተመለከተ፣
“ልጄ! የትኛውን ትፈልጋለህ? አንዱን ሳህን ምረጥና አንሳ...” አለኝ።
በጊዜው፣ እንቁላል እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ምግብ አልነበረም። ድህነቱ፣ ገንዘብ ማጣቱ በሁላችንም ቤት ጫን ያለ ስለነበረ አዲስ ዓመት ካልመጣ ወይም ዓመትባል ካልደረሰ በቀር እንቁላል መብላት ዘበት ነው። ታዲያ እኔ፣ አንዱን ሳህን መርጬ እንድወስድ አባቴ ሲጠይቀኝ ፈጥኜ እንቁላል ያለበትን ሳህን መረጥኩ። እንዴ ማን ይሞኛል? እንቁላል ተገኝቶ ነው? በሰዓቱ እንቁላል ያለበትን ሳህን ሳነሳ ቅንጣት ታህል አላመነታሁም ነበር። ደስ እያለኝ ፓስታ በእንቁላሌን መብላት ጀመርኩ።
አባቴ ሁለተኛውን ሳህን አንስቶ መመገብ ሲጀምር ግን ዐይኔን ማመን አቃተኝ። አባቴ ከሚበላበት ሳህን ውስጥ ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች በፓስታው ተሸፍነው ኖሯል። አቤት አንዴት እንደተናደድኩ! ቆጨኝ በጣም! ቸኩዬ በመወሰኔ ራሴን ወቀስኩት። ምናልባትም በሕይወት ዘመኔ እንደዚያ ቀን የተበሳጨሁበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ይኼን ጊዜ አባቴ እየሳቀ፣
“የእኔ ልጅ… ዐይኖችህ የሚያዩት ነገር ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ መቼም እንዳትረሳ! ደግሞ በሰዎች ላይ ብልጣብልጥ ለመሆን ስትሞክር ትጎዳለህ!!” አለኝ።
በሌላ ቀን አባቴ በተመሳሳይ ምግብ አዘጋጅቶ ሲያበቃ እንደተለመደው ፓስታውን በሁለት ሳህን አቀረበው። አንደኛው ሳህን አናት ላይ አንድ የተቀቀለ እንቁላል አስቀምጦበታል። ሌላኛው ላይ ግን ካናቱ ምንም እንቁላል አላደረገበትም። ከዚያ እንደተለመደው አባቴ ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየጠቆመ፣
“በላ ልጄ! ምረጥና የምትፈልገውን ሳህን ውሰድ..እየጠቆመ፣
ካለፈው ሥህተቴ በመማር በጥንቃቄ መምረጥ እንዳለብኝ አሰብኩና ቀልጠፍ ብዬ ካናቱ እንቁላል የተደረገበትን ትቼ ሌላኛውን መረጥኩ። ከዚያ በፍጥነት ፓስታውን ገላለጥኩና ሳህኑን ዐየሁት። በጣም ደነገጥኩ! ሳህኑ ውስጥ አንድም እንቁላል የሚባል ነገር የለውም። አባቴ በድጋሚ እየሳቀ፣
“ልጄ… ሁልጊዜ በልምድህ ላይ ብቻ የምትተማመን ከሆነ ትከስራለህ። አንዳንዴ ሕይወት ራሷ ልታሞኝህ ወይም ቁማር ልትጫወትብህ ትችላለች። ዳሩ ግን በዚህ ብዙ ልታዝን ወይም ልትቆጣ አይገባም… ትምህርት እንደሚሆንህ ቆጥረህ ብቻ እለፈው። እንዲህ ያለውን እውቀትየተቀቀለው መጽሐፍት ላታገኝ እንደምትችል አስታውስ!!” ብሎኝ፣ ያቺ ቀን አለፈች።
ለሦስተኛ ጊዜ አባቴ ምግብ አዘጋጀ። እንደተለመደው ፓስታና እንቁላሉ በሁለት ሳህኖች ቀርቧል። ባንዱ ሳህን የተቀቀለው እንቁላል ከፓስታው በላይ ተቀምጧል። በሌላኛው ሳህን ደግሞ ፓስታ ብቻ። እንግዲህ የውስጡን አላውቅም… ከላይ ግን እንቁላል የለውም። አባቴ የተለመደ ጥያቄውን አቀረበልኝ። ወደ ምግብ ጠረጴዛው በአገጩ እየጠቆመ፣
“ልጄ ምን ትጠብቃለህ? ምረጣ!! የትኛው ሳህን ይሁንልህ?” አለኝ።
አሁን እኔ ከሁለቱ ሥህተቶቼ በደንብ ትምህርት አግኝቻለሁ።
“አባቴ አንተ የቤቱ አባወራ ነህ! ለቤተሰባችን ሰርክ የምትለፋ፣ ደከመኝ ሳትል ቀን-ከሌት እኛ እንዳይርበን የምትሠራ አባት ነህ። መጀመሪያ መብላት ያለብህ አንተ ነህ… ለስኩለት። ስለዚህ ቅድሚያ አንተ አንሳ…” ስል መለስኩለት።
አባቴ በጭራሽ አላቅማማም። ከአናቱ እንቁላል የተቀመጠበትን ሳህን አንስቶ መብላት ጀመረ። እኔም ሁለተኛውን ሳህን አንስቼ ፓስታዬን ለመብላት አቀረቀርኩ። እርግጠኛ ነበርኩ፣ ሳህኑ ውስጥ እንቁላል እንደማይኖር። ከፓስታው በታች ሁለት እንቁላሎችን ሳገኝ ግን ዐይኔን ማመን አልቻልኩም። ቀና ብዬ ሳየው አባቴ ፈገግ ብሎ በፍቅር ዐይኑ እያስተዋለኝ ነበር። ከዚያም እንዲህ ሲል መከረኝ፣
“የኔ ውድ ልጅ! ለሌሎች ሰዎች መልካም መልካሙን ስታደርግ ተፈጥሮ ራሷ መልካም መልካሙን ወደ አንተ ታመጣለች! ይኼንን መቼም እንዳትዘነጋ!!” አለኝ።
ከዚያን ጊዜ በፊትም ሆነ ከዚያን ጊዜ በኋላ አባቴ ብዙ ጊዜ መክሮኛል! ገስፆኛል! ገርፎኛል! አብዛኞቹን ማስታወሴን እጠራጠራለሁ። ነገር ግን እነዚህን ሦስት ምክሮቹን በፍጹም አልረሳቸውም! እስክሞትም ድረስ የምረሳቸው አይመስለኝም። እነሆ ሕይወቴም በዚህ ምክንያት የተስተካከለ ሆኗል። ከአባቴ ምክር በኋላ ስኬት መንገዷን ወደእኔ አድርጋለች።

መልካም ቀን
ከተመቻችሁ ፔጁን ላይክ &ሼር በማድረግ ያጋሩ ።
297 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ