Get Mystery Box with random crypto!

[2/28/23 10:35 PM] በአድዋው ጦርነት ከፍተኛ የመከላከል ሃይል የነበረው በሜጀር ጄኔራል | " የዞስካለስ እይታዎች "

[2/28/23 10:35 PM]

በአድዋው ጦርነት ከፍተኛ የመከላከል ሃይል የነበረው በሜጀር ጄኔራል Dabormida የሚመራው የጣሊያን ጦር ነበር። የምኒልክ special force የሚባለው ገጠመውና አልቻለም።

ኋላ ላይ በራስ አሉላ እና በራስ መንገሻ የሚመራው የትግራይ ጦር እንዲገጥመው ነው የተደረገው። በነዚህ የትግራይ ጀነራሎች የሚመራው የትግራይ ጦር በመጀመሪያ ያደረገው 2 ሰአት የፈጀ ምስጥራዊ ከበባ ማካሄድ ነበር።

ጦር ረዣዥም ሳር፣ ድንጋያማ ቦታዎች እየፈለገ ቦታ ከያዘ በኋላ ይህ ጣሊያን የምትተማመንበት ሰራዊት ሰአታት ባልወሰደ ኦፕሬሽን ከጥቅም ውጭ አደረገው። በዚህ front የተሰለፈው የጣልያን ሰራዊት ከተሸነፈ በኋላ ጣልያን በአድዋ ላይ መሸነፏ ተረጋገጠ፤ በተለያየ አቅጣጫ ሃይሉን እያሰባሰበ ድጋሚ ለመግጠም ሲሞክር የነበረው ሰራዊት ጣልያንም ይኽ የሚተማመኑበት ሃይል ተመትቶ መበታተኑ ሲሰሙ ብትንትኑ ወጣ።

በዚህ መንገድ ነበር አድዋ የድል ችቦ የለኮሰችው። የዚህ ሁሉ ዕቅድ አውጪ የጦር ጠበብቱ ኣሉላ ሲሆኑ አጠቃላይ የስለላ ኦፕሬሽኑ የሚመሩት ደግሞ ባሻይ ኣውዓሎም ሓረጎት ነበሩ።

በተለይ በስለላው (መረጃ በማቀበል) በኩል የአካባቢው ህዝብ ጉልህ ሚና እንደተጫወተ የታሪክ መዛግብትና ምሁራን ይመሰክራሉ።




JOIN US :- @zooskales_views