Get Mystery Box with random crypto!

' ------ ' በይኝ በሽመሉ   ምቺኝ በከዘራ       የቀረሽ እሱ ነው       ካየሁት | " የዞስካለስ እይታዎች "

" ------ "

በይኝ በሽመሉ
  ምቺኝ በከዘራ
      የቀረሽ እሱ ነው
      ካየሁት መከራ
አትያዢ ነገር
የተልባ እግር
      እንቆቅልሽ ሆነ
      የአንቺማ ነገር
ይታይሽ ጉዳቴ
ነግ በእኔ በይና
      አስታውሺው ችግሬን
      እንደ ራስ እዪና
ትዝ ይበልሽ እንጂ _ _ የቀድሞ ቃልሽ
እንደ ሐምሌ ዝናብ _ _ አይሁን አመልሽ

12/01/2015 ዓ,ም

ቴሌግራም ይቀላቀሉን እና ያካፍሉን :- CHANNEL :- @zooskales_views

ቡድን: - https://t.me/Literary_revolutionaries