Get Mystery Box with random crypto!

ህመሙ ቢበዛ ምን ያስጨንቀኛል ምህረት ብታገኚ ምንስ ያስከፋኛል ደግሞስ ብት | " የዞስካለስ እይታዎች "

ህመሙ ቢበዛ
ምን ያስጨንቀኛል
ምህረት ብታገኚ
ምንስ ያስከፋኛል
ደግሞስ ብትተኚ
አልጨነቅ ብዙ
አጠገብሽ አልሆን
አሉሽ ሰዎች ብዙ
ደግሞ ብትሞቺ
ፈፅሞ አላለቅስም
አፈርም አይብለሽ
እላለሁኝ እኔ ዝም
ዝምታዬ ለምን እንደሆነ
ሲያምሽ ታምሜያለሁ
ስትተኚም ማቀቅሁ
ስታጣጥሪብኝ ቀድሜሽ
ነው የሞትሁ .


28/09/2014
ለ ዮርዲ