Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስ | ዘሪሁን ገሠሠ

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገለፁ!

ሙሉ ወለጋን ጧት ማታ በንፁሃን ደም የሚያጥበው አሸባሪው ኦነግ ፥ ከወለጋ አልፎ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት ካደረሰባቸው ብሎም ግልፅ በሚባል ደረጃ ታጣቂዎችን ከሚመለምልባቸው አካባቢዎች መካከል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ነው፡፡

ይህ ጨፍጫፊ ቡድን ከሰሞኑ ያስመረቃቸውን ጨምሮ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጨፍጫፊዎቹን ከወለጋ አጓጉዞ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ዳሊ-ዳክ የተባለ ቀበሌ ላይ በሚገኝ ጫካ አስፍሮ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ለጨፍጫፊው ቡድን ከአካባቢው ተመልምለው አብረው የመጡ የቡድኑ አባላት "አወጡት" በተባለውና በአካባቢው ነዋሪዎች ለጥንቃቄ በተላለፈው መልዕክት መሠረት ፦ ቡድኑ በቀጣይ ቀናት ፥ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ብሄር ተወላጆች የሚኖሩበትን አመያ ወረዳ በማፅዳት ፥ በአበሽጌ ወረዳ በሚገኘው ጊቤ በረሀ ጫካ አልፎ የሽብር ተግባሩን ወደደቡብ ክልል የማስፋፋት ተልእኮ ተሰጥቶት ወደስፍራው እንደመጣ ተገልፇል፡፡

"መንግስት ከዚህ ቀደም የተፈፀሙ ጥቃቶችንና ግድያዎችን ከመፈፀማቸው በፊት የድረሱልን ጥሪ ብናስተላልፍም በዳተኝነት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎናል" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ፥ አሁንም የከፋ ፍጅት ከመፈፀሙ በፊት በስፍራው የፀጥታ አካላትን በበቂ ሁኔታ አሰማርቶ ዜጎችን የመጠበቅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል !

#ሼር በማድረግ መረጃውን ተደራሽ ያድርጉ!