Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ ፋኖ! ግንባር ላይ እየተፋለሙ ያሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች የቁስለኛ ማሳረፊያና የሎጂስ | ዘሪሁን ገሠሠ

መረጃ ፋኖ!

ግንባር ላይ እየተፋለሙ ያሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች የቁስለኛ ማሳረፊያና የሎጂስቲክ ካምፓቸውን በፀጥታ አካላት እንዲለቁ ተጠየቁ!

በሀይቅ ከተማ የሚገኘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከዚህ በፊት የአውራጎዳናና የቱርክ የባቡር ፕሮጀክት ካምፕ የነበረን ቦታ ለሎጂስቲክ ማከማቻ ፣ ለቁስለኛና አዲስ ምልምል ሰልጣኞች ማረፊያ ሲገለገልበት የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የትህነግ ወረራ ገና ሳይቆም የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎችና አመራሮች ካምፑን እንዲለቁ በተለያዩ ጊዜያት ጫና ሲፈጥሩ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሠአት ጦሩ ሙሉ በሙሉ ግንባር ተሰልፎ መሪር የሆነ ዋጋን እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ፥ የተለያዩ ተተኳሾች የተቀመጠበትንና በዚህ ሳምንት ብቻ በውጊያ ላይ ቆስለው እያገገሙ ያሉበትን ካምፕ ፥ በዛሬው እለት ከመንግሥት የበላይ አመራሮች ተላክን የሚሉ የታጠቁ አካላት "የስደተኞች ማረፊያ ልናረገው ነውና ለቃችሁ ውጡ! " በማለት አስነዋሪ ተግባር መፈፀማቸው ተገልፇል፡፡

እኚህን ለህዝባቸው ክብር ሲፋለሙ በዚህ ሳምንት እንኳ በርካታ ጀግኖችን የገበሩ ፥ የደሙና የቆሰሉ ፋኖዎችን ማክበር ፣ መደገፍና ማመስገኑ ቢቀር ከስር ከስር እየተከታተሉ ይህን አይነት አሳፋሪና የነቀዘ ተግባር መፈፀማቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው በዝምታ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ ነው፡፡

ይህ ጉዳይ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጭምር የደረሰ ሲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ "ይሄን ያዘዘውን አካል እናጣራለን! ተገቢም አይደለም!" ሲሉ መግለፃቸው ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለም በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው ካምፕ የሚገኙት እጅግ በርካታ ፋኞዎች ወደግንባር ለመዝመት ሙሉ ዝግጅት አድርገው ከሳምንት በላይ የመንግሥት አካላትን ቢጠይቁም "ፈቃድ አንሰጣችሁም" ተብለው ጦራቸው እየተጉላላ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡