Get Mystery Box with random crypto!

ኑዛዜው   አንድ ሰው ይሞታል።17 ግመሎች እና 3 ልጆች ነበሩት።ኑዛዜ ሲነበብ 'የግመሎቼን ግማ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

ኑዛዜው  

አንድ ሰው ይሞታል።17 ግመሎች እና 3 ልጆች ነበሩት።ኑዛዜ ሲነበብ "የግመሎቼን ግማሽ ለመጀመሪያው ልጄ አንድ ሶስተኛውን ለሁለተኛው ልጄ እንዲሁም የግመሎቼን አንድ ዘጠነኛ ለመጨረሻው ልጄ ተናዝዣለሁ"ይላል። ልጆቹ ግራ ተጋቡ ምንድን ነው ማድረግ የሚችሉት? የ17ቱ ግመሎች ግማሽ ለመጀመሪያው ልጅ ይሰጥ ተብሏል የ17 ግማሽ 8 ይሆን እና አንድ ግመል ይተርፋል እና አንዱ ግመል ሊሰነጠቅ ነዉ? ይሄንንም ቢያደርጉ እንኳ መፍትሄ አይሆንም ምክንያቱም የግመሎቹ አንድ ሶስተኛ ደግሞ ለሁለተኛው ልጅ ይሰጥልኝ ብሏል አባትዬው። ይሄም ቢሆን ችግሩን አይፈታውም።የግመሎቹ አንድ ዘጠነኛ ደግሞስ ለሦስተኛው ልጅ ይሰጥ ይላል ኑዛዜው። ግመሎቹ ሁሉ ተቆራርጠው ማለቃቸው እኮ ነው።ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት በመንደሩ የታወቀ የሒሳብ ምሁር ዘንድ አመሩ።ሰውየው በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ቢያስብበትም መፍትሄ ግን ሊያገኝለት አልቻለም።           

"እኔ በህይወቴ ቁጥሮችን እንጂ ግመሎችን አካፍዬ አላውቅም ይሄ ተራ ማጃጃያ ነው የሚመስለኝ።ኑዛዜው በትክክል መተግበር ካለበት ግን ግመሎቹን መሰንጠቅ ግድ ነው።" አላቸው ልጆቹ በሰውየው ምክር አልተስማሙም። ግመሎቹ እንዲሰነጠቁ አይፈልጉም። ታዲያ ምን ተሻለ??? ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው ወደ እነሱ ጠጋ ብሎ "ከቁጥር ይልቅ ስለ ግመሎች የሚያውቅ ሰው ብታማክሩ ይሻላችኋል" ሲል መከራቸው። እነሱም በሰውዬው ምክር ተስማምተው ስለ ግመሎች የሚያውቅ ሰው ሲፈልጉ አንድ እርጅና የተጫጫነው፣ያልተማረ፣ነገር ግን ከህይወት ልምድ ብልህነትን የቀሰመ አዛውንት አገኙና ችግራቸውን አማከሩት።

አዛውንቱ ሰው ስቆ "አታስቡ ነገሩ ቀላል ነው"አላቸው ከዛም አዛውንቱ የራሱን አንድ ግመል አበደራቸውና የግመሎቹ ቁጥር 18 ሆነ "ከዚህ በኋላ ተካፈሉ" አላቸው። በኑዛዜው መሰረት የግመሎቹ ግማሽ 9 ነውና ለመጀመሪያው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው። የግመሎቹ አንድ በሶስተኛ 6 ነውና ለሁለተኛው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው። የግመሎቹ አንድ ዘጠነኛ 2 ነውና ለሶስተኛው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው።አንድ ግመል ቀረ ሽማግሌው አንድ ግመል አበድሯቸው አልነበር፣ያበደራቸውን አንድ ግመል መልሶ ወሰደ።"አሁን መሄድ ትችላላችሁ" ብሎ አሰናበታቸው፤እነሱም ተደሰቱ።         

ተራ እውቀት(Knowledge) ተግባራዊ አይደለም።በልምድ የካበተ ጥበብ(wisdom) ግን ተግባራዊ እና ተጨባጭ ነው።ተግባራዊ የማይሆን እውቀት ተራ የቃላት ጨዋታ ነው ጥበብ እና ብልህነት ግን ከህይወት ልምድ የተጨለፉ ናቸው።                               

Osho

@zephilosophy