Get Mystery Box with random crypto!

የነፃነት ሦስት አውታሮች ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ) ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ ነፃነት ባለሦስት አ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የነፃነት ሦስት አውታሮች

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ

ነፃነት ባለሦስት አውታር ክስተት ነው፡፡ የመጀመሪያ አካላዊ አውታር ነው፡፡ አካላዊ ባርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለህ፣ ለብዙ ሺህ ዓመታትም፣ ሰው እንደማንኛውም ቁሳቁስ ገበያ ወጥቶ ሲሸጥ ቆይቷል:: በዓለም ዙሪያ ነበሩ። ሰብዓዊ መብቶቻቸው አይከበሩላቸውም፣ በሰው ደረጃ ሳይሆን በከፊል ሰውነት ይታዩም ነበር:: አሁንም ቢሆን ሰዎች በከፊል ሰውነት ይታያሉ፡፡ ህንድ ውስጥ ሱድራዎች ወይንም የማይነኩት በመባል የሚታወቁ ህዝቦች አሉ:: የሀንድ ህዝቦች አሁንም በአብዛኛው ባርነት ውስጥ ይኖራሉ:: መማርና፣ ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት በባህል ከተወሰነላቸው ሙያ ውጭ ሌላ ሙያ ውስጥም መግባት አይችሉም፡፡ እነሱን መንካት ሳይቀር ያቆሽሻል ተብሎ ስለሚታሰብ የነካቸው ሰው ወድያውኑ ገላውን መታጠብ አለበት፡፡ እንኳን አካሉን ይቅርና ጥላውን እንኳን ከነካኸው መታጠብ ይኖርብሀል።

በዓለም ዙሪያ፣ የሴት ልጅ ሰውነት ከወንድ ልጅ እኩል አይቆጠርም፡፡ ከወንድ እኩል ነፃነት የላትም፡፡ ቻይና ውስጥ ለብዙ ምዕተ ዓመታት ባል ሚስቱን መግደል ይችል ነበር፡፡ ምክንያቱም የግል ንብረቱ ነች። ልክ ወንበርህ፣ ጠረጴዛህና ቤትህ ንብረትህ በመሆናቸው ልታቃጥላቸው ወይንም ልታወድማቸው እንደምትችል ሁሉ ሚስትህም ላይ ይኸው መብት ይኖርሀል። በቻይና ህግ ሚስቱን ለሚገድል ባል መቀጫ የሚሆን ህግ አልወጣም፣ ምክንያቱም ሴት ልጅ ነፍስ የላትም ተብሎ ይታሰባል። ሴት ልጆችን የምታመርት መሣሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም።

ስለዚህ አካላዊ ባርነትና አካላዊ ነፃነት አሉ፡፡ አካላዊ ነፃነት ማለት ያለመታሰር ከሌላ ከማንም አካል ዝቅ ተደርጎ አለመታየት፣ አካልን በተመለከተ እኩልነት ማግኘት ማለት ነው። ግን ዛሬ ድረስ እንኳን ይህ ነፃነት በሁሉም ሥፍራ አይገኝም፡፡ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም፡፡

አካላዊ ነፃነት ማለት ጥቁርና ነጭ፣ የወንድና የሴት ወይንም የሱ አይነት ልዩነቶች ያለመኖር ማለት ነው፡፡ ማንም ሰው ንፁህ አይደለም ማንም ሰው ቆሻሻ አይደለም አካላቶች አንድ ናቸው፡፡

የሁለተኛው አውታር፣ የስነልቦና ነፃነት ነው:: በዓለም ዙሪያ ስነልቦናዊ ነፃነት ያላቸው ግለሰቦች እጅግ ጥቂት ናቸው:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአንድ ርዕዮተአለም ተከታይ ከሆነ ስነልቦናዊ ነፃ አይደለም። የልጆች አስተዳደጋችን ባጠቃላይ ባርነት ውስጥ የሚያስገባቸው ነው። የፖለቲካ የማሕበረሰብና የግል አስተሳሰቦች ባሪያ እናደርጋቸዋለን፡፡ በራሳቸው እንዲያስቡ፤ በራሳቸው እውነትን እንዲፈልጉ እድል አንሰጣቸውም:: መልክ እንገልፅላቸዋለን:: ወላጆች ለልጆቻቸው ስለእግዚአብሔር ያስተምሯቸዋል፣ ግን ስለእግዚአብሔር የሚያውቁት ምንም ነገር የለም።

ራስህ የማታውቀውን ነገር ለልጆችህ እያስተማርካቸው ነው:: የአንተ አእምሮ በወላጆችህ የተቀረፀ ስለሆነ አንተም የልጆችህን አእምሮ እየቀረፅክ ነው:: በዚህ ሁኔታ በሽታው ከአንድ ትውልድ ወደሌላው ትውልድ ይተላለፋል፡፡

ስነልቦናዊ ነፃነትን ማምጣት የሚቻለው፣ ልጆች እንዲያድጉ ሲፈቀድላቸው፣ የበለጡ ጥበበኞች ሆነው እንዲያድጉ ዕርዳታ ሲደረግላቸው፣ የበለጠ አስተዋይ፣ ንቁ እና አመዛዛኝ ሆነው እንዲያድጉ ሲፈቀድላቸው ነው:: በምንም ዓይነት እምነት እንዲያዙ ማድረግ አይገባም፡፡ እውነቱን በራሳቸው መርምረው እንዲደርሱበት የተቻለውን ያህል ልባቸውን ማነሳሳት እንጂ በምንም ነገር እንዲያምኑ ማስተማር አይገባም፡፡ ከመጀመሪያውኑ፣ «የራሳችሁ እውነት፣ የራሳችሁ ግኝት ነፃ ያወጣችኋል። ከዚህ ነፃ ሊያወጣችሁ የሚችል ምንም ነገር የለም»

እውነትን መዋስ አይቻልም:: ከመጽሐፎች አይጠናም፡፡ ማንም ስለእውነት ሊነግራችሁ አይችልም፡፡ እውነት በሕይወት ህላዌ ውስጥ ፈልገህ ለማግኘት፣ ራስህ ማስተዋልህን መቅረፅ አለብህ:: አንድ ታዳጊ ለነገሮች ክፍት፣ ተቀባይ፣ ንቁ እንዲሆን ከተደረገና፣ ነገሮችን እንዲፈትሽ ማበረታቻ ከተሰጠው፣ ስነልቦናዊ ነፃነትን ለማግኘት ይችላል። ስነልቦናዊ ነፃነትን ተከትሎም ከፍተኛ ሀላፊነት ይመጣል። ይህን ልታስተምረው ይገባሀል፣ የስነልቦናዊ ነፃነት ጥል ሆኖ ይከሰታል። ካስተማርከው ያመሰግንሀል። ካልሆነ ግን ቤተሰቦቹ አእምሮውን በመሰላቸው በመቅረፅ፣ ነፃነቱን እንዳንኮታኮቱበት ማንኛውም ታዳጊ ህፃን በወላጆቹ ላይ ንዴት ያድርበታል፡፡ ገና ምንም ጥያቄ ሳይጠይቃቸው በፊት እነሱ አእምሮውን በመልሶች ሞልተውታል ምክንያቱም መልሶቹ የራሱን ልምዶች መሠረት ያደረጉ አይደሉም፡፡

ሶስተኛ አውታር የነፃነት ፍፁማዊነት ነው:: ይህም አንተ አካልህና አዕምሮህ ያለመሆንህንና፣ ንፁህ ሀሳብ መሆንህን ማወቅ ነው፡፡ እውቀት ከመስጠት እንደሚገኝ ማወቅ ነው፡፡ ይህ ከአካልህ ይለይሀል፣ ከህሊናህም ይለይሀል፣ እናም አንተ በንፁህ ሀሳብና በንፁህ እውቀት መልክ ብቻ ህልውና ይኖርሀል። ይህ መንፈሳዊ ነፃነት ነው፡፡

ለአንድ ግለሰብ የሚያስፈልጉት ሶስቱ መሠረታዊ የነፃነት አውታሮች እነዚህ ናቸው፡፡

ሰዎች በጠቅላላ እንደአንድ ሲታዩ ነፍስም ሆነ ህሊና የላቸውም፡፡ ይህ አንድ የሰው ልጅ ህልውና አካልም የለውም፣ ስም ብቻ ሆኖ ይገኛል፡፡ ቃል ብቻ ነው ለጠቅላላው አንድ ህልውና ነፃነት አያስፈልገውም፡፡ ሁሉም ሰው ነፃ ሲሆን፣ ጠቅላላው አንድ ነፃ ይሆናል፡፡ ግን በቃላት የተገዛን ከመሆናችን የተነሳ፣ ቃላት ምንም ጭብጥ እንደሌላቸው እንዘነጋለን፡፡ ጠ ቅላላው አንድ፣ ማለትም ህብረተሰቡ፣ ማህበረሰቡ፣ ሀይማኖት ቤተክርስቲያኑ ሁሉም ቃላት ብቻ ናቸው:: ከበስተጀርባ ምንም እውነት ነገር የለም፡፡

አንድ ትንሽ ታሪክ ትዝ አለኝ። «ኤሊስ ኢን ወንደርላንድ» በተባለው በሉዊስ ካሮል በተፃፈው መጽሐፍ ላይ፣ ኤሊስ ንግስቲቱ ወደምትኖርበት ሥፍራ ትመጣለች። በደረሰች ጊዜ ንግስቲቱ እንዲህ ብላ ትጠይቃታለች፡፡ «ወደ እኔ ስትመጪ መልዕክተኛ አግኝተሻል»
ልጅትም ስትመልስ፣ «ማንንም»
ንግስቲቱም «ማንንም» ማለት የሰው ስም መሰላት፣ «ታዲያ ማንንም እስካሁን እዚህ ያልደረሰው ለምንድነው» ብላ ጠየቀቻት፡፡

ልጅትም፣ «ማዳም፣ ማንንም ማለቴ እኮ ማንንም ነው» አለቻት»

ንግስቲቱም እንዲህ አለች፣ «የማይረጋ ነገር አትንገሪኝ ገብቶኛል፡ ማንንም ከማንንም ሌላ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህ ከአንቺ በፊት እዚህ መድረስ ነበረበት። ማንንም ሲራመድ ከአንቺ ይልቅ ቀሰስተኛ ነው ማለት

አሊስም ስትመልስ፣ «ማንንም ከእኔ ይልቅ ቀሰስተኛ ሆኖ አላየሁም» በዚህ መልኩ ውይይቱ ይቀጥላል። በንግግራቸው ላይ ግን «ማንንም » አንድ ሰው ይሆንና፣ አሊስ ንግሥቲቱን ማሳመን ያቅታታል፡፡

ጠቅላላው አንድ እጅግ አደገኛ ሀሳብ ሆነ። በጠቅላላው ሰም፣ ግለሰቡ ማለትም እውነት ዘወትርም መስዋዕት ይደረጋል፡፡ እኔ ይህን ሃሳብ
በፍፁም እቃወመዋለሁ።

ሕዝቦች በህዝብ ስም ግለሰቦችን ሆነዋል። «ህዝብ» ግን ከቃላት አያልፍም በካርታ ላይ ተስለው የምናያቸው መስመሮች በምድር ላይ የሉም:: ጨዋታዎች ናቸው:: በእነዚያ መስመሮች የተነሳ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ሞተዋል። በሌሎች መስመሮች ያሉ ሠዎችም ሞተዋል። እናንተ ደግም የሞቱትን የሀገር ጀግኖች ትሏቸዋላችሁ::

@Zephilosophy
@Zephilosophy