Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዘማህበረ ናታኒም መሀረኒ ድንግል መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2× | ✝ዘንዶ አስራ በአታ ለማርያም ገዳም✝

ዝማሬ ዘማህበረ ናታኒም
መሀረኒ ድንግል
መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
አዝ...............
ይጠሩሻል ካህናቱ
ንዒ ይሉሻል በሳታቱ
ለለመነሽ የማትቀሪ
በልቤ ውስጥ ፀንተሽ ኑሪ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ

መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ

ያዲስ ኪዳን ኪሩ የሆንሽ
ለምኚልን ካንዱ ልጅሽ
ርግብየ ሰናይትየ
ነይ ወደኔ ነይ ወልድየ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
..............................................
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ 2×
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ
አዝ.........................
ባለም መኖር ሰልችቶኛል
መልካም መስራት አቅቶኛል
እጄን ይዘሽ ድንግል ምሪኝ
አዛኚቷ አትለይኝ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ

መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ

እበላለው ብዬ ማርያም
እመካለው ባንቺ አላፍርም
ካንቺ ወዴት እሄዳለው
ስምሽን ልጥራው እፅናናለው
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ

ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ 2×
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ
ማህበረ ናታኒም ዘደብረ ፀሐይ