Get Mystery Box with random crypto!

(ኢትዮጵያዬ) '''''''''''''''''''''''''' ጋራ ላይ ሰቅለውሽ አባቶች አያቶች በብርቱ | ዜና ማን~ሲቲ

(ኢትዮጵያዬ)
''''''''''''''''''''''''''
ጋራ ላይ ሰቅለውሽ
አባቶች አያቶች በብርቱ ትከሻ
በምን ጉልበታችን
ወጥተን እንመርምረው ልክሽን ስንሻ..?
ዘመን እየገፋ
ቁልቁል የሰደደን ድንክዬ ልጆችሽ
እንዴት እንመልከት
ጋራውን አሻግረን ሲናፍቀን መልክሽ...?

አደራ እናት አለም
አንዴም ሳንገናኝ አንዴም ሳንተያይ
ምፅአት እንዳይመጣ
ዘም'በል በይልን
ቀን ፈቅዶ ከማማው
አፋፍ እስክንወጣ !


#ዳግም/ኪዮርና/

@Ethio_Poem_Gallery