Get Mystery Box with random crypto!

29 ዜና ቅዱሳን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዕንቈ ብርሃን ዘገዳመ አንገብ እንኳን ለአባታ | ዜና ቅዱሳን

29
ዜና ቅዱሳን
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዕንቈ ብርሃን ዘገዳመ አንገብ
እንኳን ለአባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ተአምር

የተመረጠና የተወደደ ብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡ጸሎቱና በረከቱ ወዳጆቹ በሚሆኑ____ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
#ብፁዕና ቅዱስ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ጥቅምት 29 ቀን በአረፈ ጊዜ፤<<<<አባታችን ሆይ የገዳም ኮከብ የዓለም ብርሃን ነህ፤አባታችን ሆይ የሕሙማን ፈዋሽና ሙታንን የምታስነሳ ነህ፤አባታችን ሆይ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ የጎስቋሎች ረዳት ነህ፤አባታችን ሆይ የዕውሮች መሪ የአንካሶች ምርኩዝ ነህ>>> የሚል ብዙ ለቅሶና ዋይታ ሆነ፡፡
#ይህ ሁሉ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ የክቡር አባታችንን መቃብር የሚሸፍን አመድ/አፈር/ እና የወርቅ መስቀል ከሰማይ አወረደላቸው፡፡የአባታችን መቃብርም ቤተ መቅደስ በላይዋ በነበረባት በአንዲት ድንጋይ ውስጥ ሆነ ፤ይችህም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሰነጠቀች ነበረች፡፡ ክቡር ሥጋውንም ምድራዊ የሰው እጅ ሳይነካው አፏን ከፍታ ሥጋውን ዋጠችው/ተቀበለችው/፡፡
የብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃንና የአባ ፊልጶስ ጸሎታቸውና በረከታቸው ወዳጆቻቸው በምንሆን___ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣