Get Mystery Box with random crypto!

#መግለጫ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ጠቅላላ የመብቶች ጥሰት በተመለከተ | Zena Tube

#መግለጫ

ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ጠቅላላ የመብቶች ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩ በላከልን መግለጫ ፥ የተደራሽነት መብትን ጨምሮ የትምህርት፣ የጤና፣ የስራ እና የቅጥር መብቶች እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች መብቶች በየግዜው እየተጣሱ እና ለጥሰቶቹ ሀላፊነት የሚወስድ አካል ሳይኖር እንዲሁም ጥፋተኞችም ተጠያቂ ሳይደረጉ የመብት ጥሰቶቹ ተድበስብሰው በመታለፍ ላይ ናቸው ብሏል።

የአካል ጉዳተኞችን የመብት ጥሰቶችን ተከትሎ ተጠያቂነት ባለመኖሩም ጥሰት የሚፈጸምባቸው ሰዎች ሳይካሱ እየቀሩ እና ጥሰት ፈጻሚዎችም ድርጊታቸውን ትክክል አድርገው እንዲወስዱትና የመብት ጥሰቱም ያለከልካይ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል ብሏል።

አሁን በተግባር እንደሚታየው የአካል ጉዳተኞች የመብት ጉዳዮች በግለሰቦች መዳፍ ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው፤ አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ መብቱን እንደምጽዋት እንዲጠይቅና እንዲቀበል ተገዷል ሲልም ገልጿል።

ማህበሩ ፥ በአካልጉዳተኛ ግለሰቦች ላይ ከሚፈጸሙ አይነተብዙ የመብት ጥሰቶች በተጨማሪ ከመንግስት በኩል አካል ጉዳተኞችን በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአካታችነት መሻት በሚመነጭ ተነሳሽነት የማካተት ስራዎች በበቂ ሁኔታ እየተሰሩ አይደለም ብሏል።

ከሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ17.6 በላይ የሚሸፍነው አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ እንደሆነ ያታወቃል ያለው ማህበሩ የተለየ በጀት የማይበጀትለት መሆኑና የመብት ጥያቄ በሚያነሳበት ግዜም ፖለቲካዊ ውክልና የሌለው ማህበረሰብ መሆኑን ተከትሎ ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረት ላይ ነው ብሏል።

ማህበሩ እየተባባሰ መጥቷል ላለቸው የመብቶች ጥሰት መፍትሄ ያለውን በዝርዝር አስቀመጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia