የትላንቱ የጎረቤት ሶማሊያ ፓርላማ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?
• 229 ድጋፍ
• 7 ተቃውሞ
• 1 ድምፀ ተአቅቦ
በትላንትናው ዕለት የጎረቤታችን ሶማሊያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠ/ሚ ባቀረቡት የካቤኔ አባላት ላይ ድምፅ ለመስጠት ተሰብስቦ ነበር።
በዚህም ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ያቀረቡትን የካቢኔ አባላት በ229 ድጋፍ፣ በ7 ተቃውሞ ፣ በ1 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኔያቸው ያካተቷቸው የቀድሞ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ምክትል መሪ የነበሩት ሙክታር ሮቦው የሶማሊያ የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
በሌላ በኩል ፤ የቀድሞው የአልሸባብ ሰው በካቢኔ ውስጥ መካተታቸው አሜሪካን እንዳላስደሰታት በአንድንድ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ቢነገርም አሜሪካ በካቢኔው ደስተኛ እንደሆነች በመግለፅ ለፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሙሀሙድና ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ እንኳን ደስ አላችሁ ስትል ሶማሊያ በሚገኘው ኤምባሲ በኩል አሳስውቃለች።
አሜሪካ ፤ ለሶማሊያ የምታደርገውን ድጋፎች አጠናክራ እንደምትቀጥልበትም ገልፃለች።
ሀገሪቱ በሶማሊያ የሚኒቀሳቀሰው " አልሸባብ "ን ለመዋጋት ሰፊ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ሀገራት በቀዳሚነት ስሟ የሚነሳ ሲሆን በኢኮኖሚያዊና ሰብዓዊ ድጋፍ በኩልም በሚሊዮን ዶላሮችን ለሶማሊያ ድጋፍ ታደርጋለች።