Get Mystery Box with random crypto!

ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች ! ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካ | Zena Tube

ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች !

ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል።

በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች።

የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦

6 ወርቅ፣
5 ብር
1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን በመከተል 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።

የተመዘገበው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ #ከፍተኛው ውጤት ነው።

ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።

ሜዳሊያ ያስመዘገቡ የነገዎቹ የሀገር ተስፋዎች እነማን ናቸው ?

#ወርቅ

ኤርሚያስ ግርማ (800 ሜትር)
መልክነህ አዘዘ (3000 ሜትር)
አዲሱ ይሁኔ (5000 ሜትር)
ሳሙኤል ዱጉና (3000 ሜትር መሰናክል)
ብርቄ ሀየሎም (1500 ሜትር)
መዲና ኢሳ (5000 ሜትር)

#ብር

ኤርሚያስ ግርማ (1500 ሜትር)
ሳሙኤል ፍሬው (3000 ሜትር መሰናክል)
ፅዮን አበበ (3000 ሜትር)
መልክናት ውዱ (5000 ሜትር)
ሲምቦ አለማየሁ (3000 ሜትር መሰናክል)

#ብር

መሰረት የሻነህ (3000 ሜትር መሰናክል)

እንኳን ደስ አለን አላችሁ !

ይቀላቀሉ : @tikvahethsport
https: //t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia