Get Mystery Box with random crypto!

Update....... በታማኝነቱ ላይ ትንሽ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም መቀመጫውን ፖርቹጋል ያደረገው A | New

Update.......

በታማኝነቱ ላይ ትንሽ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም መቀመጫውን ፖርቹጋል ያደረገው A Bola ይዞት እንደወጣው መረጃ ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድ የ ስፖርቲንግ ሊዝበኑን ተከላካይ ጎንሳሎ ኢናሲዮን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሷል።

በተጨማሪም A Bola ሲያክል ማንችስተር ዩናይትድ ለስፖርቲንግ የውል ማፍረሻውን 38 ሚልየን ፓውንድ ለመክፈል ፍቃደኛ እንደሆኑ ገልፀዋል ሲል አትቷል።

አሁንም ግን አፅኖት ሰጥቼ የምነግራችሁ ነገር ይህ የመረጃ ምንጭ ምንም እንኳን በብሩኖ ዝውውር ወቅት ብዙ ታማኝነት ያላቸው መረጃዎችን ያጋራ ቢሆንም አሁንም ታማኝነቱ በእጅጉ የሚወሳለት አይነት ምንጭ አይደለም ስለዚህ መረጃው እውነት ከሆነ በቅርቡ የሚሆነውን አብረን እናያለን።

[Source፦ A Bola]