Get Mystery Box with random crypto!

ሌላ የምሥራች…!! '…ኢትዮ ቤተሰብ ሚድያም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ። https://rumble.c | ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

ሌላ የምሥራች…!!

"…ኢትዮ ቤተሰብ ሚድያም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ። https://rumble.com/v189t64-ethio-beteseb-media.html … ሰብስክራይብ አድርጉት።

"…ትናንት እንደነገርኳችሁ አዲሱ ዓለም ሥርዓት እኔ ባለ ማዕተቡ ዘመዴን ፈፅሞ አልወደደኝም። በራሳቸው ሜዳ በፌስቡክና በዩቲዩብ መንደራቸው ውስጥም ሊያዩኝ አልፈቀዱም። ገና ድምጼን ሲሰሙ፣ መልኬንም ሲያዩ፣ ጽሑፌን ሲመለከቱ ነው እያስነጠሰ የሚነሥራቸው። በዚህ ሰለጠነ ዘመን ደንቁሬ፣ በዲሞክራሲ ዘመን ተጨቁኜ፣ ነፃ ሃሳቤን በነፃነት እንዳላንሸራሽር እጄንም አጣምሬ እንድቀመጥ ነው የሚፈልጉት። እኔ ደግሞ ጥሎብኝ ሲፈጥረኝ እጅ መስጠት እንዴት እንደሆነ አላውቅበትም። ከዘሬም የለማ…ሃይ…!!

"…በእኔ የተነሣ መረጃ ቲቪ በሺ ከሚቆጠሩ ቪድዮዎቹ ጋር አውርደውታል። በእኔ የተነሣ የዛሬ ሳምንት ደግሞ ተወዳጁን የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያንም ያለምንም ጥፋት ከአየር አውርደውታል። እኔ ግን እስከ አሁን አለሁ። ነገም ደግሞ እኖራለሁ።

"…ይህን ያየው ወንድሜ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ትናንት የዩቲዩብ አቻ የሆነ ራምብል rumble የሚባል ቻናል ፈልጎ አግኝቶ በዚያ በኩል ሥራ እንድጀምር አድርጎኝ እንደነበር ይታወቃል። …ዛሬ ደግሞ ዕድሜ ለጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ከቀሲስ ሳሙኤል ጋር ተገናኝተው ተወዳጇን ኢትዮ ቤተሰብን በራምብል በኩል ከተፍ ብሎ እንድትመጣ አድርገዋታል። እንደተለመደው ሰብስክራይብ አድርጉት። 100 ሰው ሰብስክራይብ ካደረገው በቂ ነው። https://rumble.com/v189t64-ethio-beteseb-media.html

"…ዩቲዩብንም ሆነ ፌስቡክን ያገነንነወው፣ በህዝብም ማዕበል እንዲጥለቀለቅ ያደረግነው እኛው ነን። ራምብልንም በህዝብ ማዕበል ማጥለቅለቅ እንችላለን። በሚገርም ሁናቴ ልክ እንደ ራምብል የፌስቡክ አቻ የሆነ ሚዲያም አግኝተናል። እናም ልክ እንደ ዩቲዩብ ፌስቡክንም እንደዚያው እንቀይረዋለን። እስከዚያው ድረስ ከራምብል ጋር ወደፊት…!!

"… አበደን እጅ መስጠት ብሎ ነገርማ የለም…!!