Get Mystery Box with random crypto!

ዜማ ቤት ⛪️ ⛪️ ⛪️Zema bet

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemabetttttt — ዜማ ቤት ⛪️ ⛪️ ⛪️Zema bet
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemabetttttt — ዜማ ቤት ⛪️ ⛪️ ⛪️Zema bet
የሰርጥ አድራሻ: @zemabetttttt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 462
የሰርጥ መግለጫ

በዜማ ቤትም መሠረታዊ ያሬዳዊ ዜማን ለመማሪያነት የሚጠቅሙ የድምጽ መዛግብትን ለማጥናት በሚመች መጠን ተከፋፍሎ ቀርቧል:: በተቻለ መጠን በዜማ ቤት በሚጠናበት ቅደምተከለልም ለማቅረብ እንሞክራለን ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ። ጥዑም ለጕርዔየ ነቢብከ፤ እምዓር ወሶከር ጥዕመኒ ለአፉየ። መዝ. 119፡ 103

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-02 13:05:53
281 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 13:05:53
264 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 07:30:38 ያሸበሩን እንደተሸበሩ ተቆጠሩ!
☞ በግጭቱ 13 ሰዎች ተገድለዋል። በሃይማኖት ስንገልጻቸው ደግሞ አምስቱ ክርስቲያን፣ ስምንቱ ሙስሊሞች ናቸው።

ጎንደር ላይ የሆነው ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ነገር ነው። የጽንፈኞቹን ተንኮል ባለመረዳት ከሁለቱም ወገን የሰው ሕይወት መጥፋቱ ሰላም ይነሳል። ተከባብሮ እና ተሳስቦ የኖረን ሕዝብ ለማባላት የተሔደበት ርቀት የመጭውን ጊዜ አደጋም ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይገባል።
ኦርቶዶክሳውያን ከጅማ እስከ አሰቦት፣ ከጅጅጋ እስከ አቃቂ በግፍ ስንገደል ጉዳዩን እንደዚህ ፖለቲካ አላደረግነውም። ሀገር ለመበጥበጥም አልተጠቀምንበትም። የጎንደሩን ጉዳይ በዚህ ደረጃ ማስጮኽ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት ሲቻል በጉልበትና በማስፈራራት፣ ሳይቻለረ የጅራፉን ጩኸት በመጮኽ እውነቱን እዚያ ውስጥ ለማዳፈን የሚደረግ አጠቃላይ ስልት አካል ነው።

የነገሩ ጥንስስ እንዲህ ነው፦

ጎንደር ላይ ማንም በማይገምተው ሁኔታ ለሽብር ያለዕረፍት የሚዘጋጁ አክራሪ እስላሞች መዋቅር ከ2ሺሕ ዓ.ም. ወዲህ በተደጋጋሚ በመንግሥት የደኅንነት አካላት ሲደረሰባቸው ተመልክተናል። የነገር እሳት ጭረው ወጣቱን ስሜታዊ በማድረግ በሚፈጠረው ጊዜያዊ ግጭት
እስልምና ላይ ጥቃት እንደደረሰ ማስመሰል ይሻሉ። በዚህ ምክንያትም በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች እንደተለመደው ክርስቲያኑን ለማረድ እና የማሳደድ ግባቸውን ለማሳካት መደላድል ለመፍጠር በአጭር ታጥቀው የተንኮል ሩጫ የሚሮጡ አሉ። ከውጭ በሚገኝ ጠንካራ ፋይናንስ እየተደገፉ በተደጋጋሚ አብሮነቱን በሚያፈርስ የተጋፊነት ተግባራት ሲሰማሩ ይታያሉ። በድብቅ በጭነት መኪና ገጀራ ሲያጓጓዙና ሲያከማቹ፣ ልዩ የጥፋት ተልእኮ አንግበው ሲደራጁና ሲዘጋጁ ታይቷል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ በድርጊታቸው የብዙኃኑን ሙስሊም ቅን ልቡና በፈለጉት መጠን በእነርሱ የጥላቻ ስብከት ሊቃኙት የተቻላቸው አይመስልም።

በእርግጠም በጎንደር ያለው የክርስቲያኑ እና እስላሙ አብሮ የመኖር ጠንካራ እሴት እና ማኅበራዊ ትሥሥር በሚገባው መጠን አልተነገረለትም። ይህ ጠንካራ የአብሮነት ገመድ በጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች የጥላቻ ሴራ እና ሴራቸውን በሚያስፈጽሙበት ከፍተኛ የገንዘብ ዐቅም፣ በተደራጀ አሠራራቸው በቀላሉ ሊበጠስ አልቻለም። ለዚህ ነው በየአጋጣሚው ተንኩሰው መልሰው ደግሞ እንደተበዳይ ለመጮህ የተዘጋጁ የሆኑት። የሰሞኑ ሁኔታም የእነዚህ አክራሪዎች የተለመደ ስልት አካል ነው። ክርስቲያኖችም እንዲህ ዓይነት ተንኳሽ አካሔዶችን ከጀርባው ያለውን ደባ በማጤን በተቻለ መጠን በሕግ አግባብ እንዲያዙ በማድረግ የብልህ መንገድን መከተል ይኖርብናል።
ብዙ ሰው የግጭቱ ምክንያት ከቀብሩ ጋር የተያያዘ ይመስለዋል። እውነቱ ግን ያ አይደለም። የከተማው ሙስሊሞች የአደባባይ አፍጥር ለማድረግ ጥያቄ ያቀርባሉ። የከተማ አስተዳደሩ አፍጥሩን በአብዮት አደባባይ እንዲያደርጉ ይፈቅዳል። የከተማው እስልምና ጉዳይ አመራሮች፣ ትልልቅ ሸኪዎች በሐሳቡ ይስማማሉ። ከወጣቶቹ አንዳንዶቹ ግን ከስብሰባው እየወጡ ከሌላ አካል ጋር እየተነጋገሩ በመመለስ በአብዮት አደባባይ ማከናወን እንደማይፈልጉ አሳወቁ።
ቀብሩ ላይ የተከሠተው ነገር አፍጥሩን በመስቀል አደባባይ ለማድረግ የሚያስችል መንገድ ማግኛው ረብሻ ነው ብለው ባመኑ አካላት የተፈጸመ ነው። አንድም ክርስቲያን አጠገባቸው ሳይደርስ መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ከበው በመቆም «አሏሃ ክበር» እያሉና መፈክር እያሰሙ መዛት የጀመሩት እነርሱ ነበሩ። ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ቢለመኑ ፈቃደኛ አልሆኑም። ተጋፊነታቸው እየጨመረ ሲመጣ ነው ራስን መከላከል ውስጥ የተገባው።

ይሁንና አሁን አየሩን ከተቆጣጠሩት መረጃዎች ውስጥ ቦታ ያገኘው አንድ ሐቅ በእስልምና ስም የሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ ጽንፈኞች የግጭቱ ጀማሪ፣ ተንኳሾች የመሆናቸው ጉዳይ ብቻ ነው። ከዛ በተረፈ ግን አብዛኛው ሰው በተለይ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጾች ሆን ተብለው ተዛብተው በሚቀርቡ «እኔ ብቻ ነኝ የተበደልኩ» ጩኸቶች የተዛባ ምስል እንዲይዝ ተደርጓል። ጽንፈኞቹ በሰላም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን መተንኮስ፣ ከዛም አሸብረው የተሸበሩ ማስመሰል፣ ሌላውን አጥቅተው የተጠቁ በመምሰል ሚዲያውን መቆጣጠር በተደጋጋሚ የሚጠቀሙበት ስልት ነው። በዚህ ድርጊታቸው ብዙኃኑ ሙስሊም የተበዳይነት ስሜት እንዲይዝ ያደርጋሉ። ክርስቲያኖችንም በተሳሳተ መረጃ ላይ ተተንርሰው ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱና እንዲያዝኑ ያደርጋሉ። ነገር ግን ውጤታማ በሆነ የተዛባ መረጃ ሥርጭት እውነትን አፍኖ ማስቀረት አይቻልም።
በርካታ ሚዲያዎች እጅግ የተጋነነ ቁጥር ያለው ሙስሊም እንደተገደለ በማውራት ሥራ ተጠምደዋል። «አትግደል!» በሚል መርሕ ላደገ ክርስቲያን የአንድም ሰው መገደል አምላኩን ያስቆጣል እና በውይይት ሊፈታ በሚገባው ጉዳይ ክቡር የሰው ልጅ ሕይወት ማለፉ በእጅጉ ያሳዝነዋል። ነገር ግን የተዛባውን መረጃ ማረም ደግሞ የተገባ ነውና እውነቱን እንገልጣለን።
☞ በእስልምና ስም የሚምሉ አክራሪዎች ሰላማዊውን ሁኔታ ወደ ብጥብጥ ለመውሰድ የሚያስችል በተደራጀ እና በተጠና አካሔድ የጠብ ጫሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል።
☞ በአክራሪዎቹ በግፍ አምስት ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈው ተገድለዋል።
☞ ስምንት ሙስሊሞች በጥይት ተገድለዋል።
ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ በሀገራችን የሽብር ህዋስ በማዘጋጀት ኢትዮጵያን ያልተረጋጋች ሀገር የማድረግ የጂኦ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ፍላጎቷን ማስፈጸም የምትፈልገው ግብጽ Daily News Egyptን የመሳሰሉ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለዓለም ማኅበረሰብ የተዛባ መረጃ በመመገብ ላይ ናት። አጃንስ ፍራንስ ፕረስን የመሳሰሉ ሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንም ያልተጣራ መረጃ ይዘው የተጋነነ የሞት መጠን እየዘገቡ ይገኛሉ። እኛ ግን በአሳዛኙ ክሥተት የተከሠተውን ጉዳት በተጨባጭ መረጃ ላይ ተተንተርሰን ማስረዳት ይኖርብናል። ጉዳቱ የአንድ ወገን አይደለም፤ የሁላችን ነው። እንዳይደገም መሥራት የሚገባንን እንሠራለን እንጂ ያሸበሩን ጥቂቶች የተሸበሩ ለማስመሰል በሚያዛቡት መረጃ ተጠልፈን እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ።
313 views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 07:02:09 @zemabetttttt
@zemabetttttt
347 views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 07:02:09
328 views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 17:35:08 https://t.me/zemabetttttt
521 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 14:09:19 ዜና እረፍት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዮስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንዲከናወን ሲኖዶሱ ወሰነ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንዲከናወን ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ የካቲት 27/2014 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ኢኦቴቢ ዘግቧል፡
592 views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 14:08:20
511 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ