Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት! ግንቦት 5/2014 ዓ.ም ቀድሞ በተያዘ መርሐግብ | ዜማ ቤት ⛪️ ⛪️ ⛪️Zema bet

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት!

ግንቦት 5/2014 ዓ.ም ቀድሞ በተያዘ መርሐግብር ብጹአን አባቶቻችን ለማነጋገር ቤተክህነት ተገኝተው የነበሩት ኢዮኤል_ግርማ እና ዳዊት_አሰፋ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፍርድ ቤት ቀርበው በመታወቂያ ዋስ እንዲለቀቁ ተወስኖ ተፈትተዋል።

ቃለአብ_ታመነ እና ዓለምነህ_ዳኘው ከኮልፈ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ200 ብር ዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ይግባኝ ተጠይቆባቸው ልደታ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህን ምንም ጥፋት ያላጠፉ ቀሪ ሁለት ወንድሞቻችንን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታቸው አበክረን እየጠየቅን ይህንኑ ጉዳይ መላው ሰንበት ት/ቤቶች በማሕበራዊ ገጻችሁ በማጋራት ለወንድሞቻችሁ ያላችሁን ድጋፍ እንድታሳዩ እናሳስባለን።