2022-06-15 09:43:19
እንደ ክርስቲያን ለመኖር ካልወሰንን የክርስትና ምልክቶች ያሉባቸው ነገሮች ባናንጠለጥል መልካም ነው፡፡
ከጌታ ጋር ያለኝን ግንኙነት የሚገለፀው በምለጥፋቸው ጥቅሶች፣ በማንጠለጥላቸው መስቀሎች ወይም ቤተክርስትያን መሄዴ አይደለም፡፡ በቃሌም የሽመደድኳቸው ጥቅሶች ፣ያሉኝ የክርስትያን መፅሐፎች፣ ካሴቶች እና ሲዲዎችም አይደሉም::
#የክርስትናዬ ማስረጃ መሆን የሚችለው በፍቅር የማፈራው ፍሬ ነው፡፡
የሚያጋጥማችሁን ሁሉ በተረጋጋ መንፈስ መጋፈጥ እንድትችሉ መጸለይ እንዳለባችሁ እመክራችኋለሁ፡፡ የሚያበሳጩ ነገሮች እንደሚያጋጥሙን የታወቀ ነው። ነገር ግን አስቀድመን ተዘጋጅተን ከሆነ በእርጋታ የመጋፈጥን ብቃት እናገኛለን፡፡
ሁልጊዜ ስሜታችንን በመቆጣጠር ተረጋግቶ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ነገሮች እንዳቀዱት አልሄዱ ሲላቸው ቱግ ሲሉ እናያለን።
አንዱ መልካም ተፅዕኖ እንዲኖረን ከሚያደርጉን መንገዶች ውስጥ ነገሮችን
በተረጋጋ መንፈስ መወጣት መቻል አንዱ እንደሆነ አምናለሁ፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ ከሁሉም ሰው ጋር በትዕግስት እንድኖር እና ቁጡዎች እንዳንሆን ያስተምረናል (1ተሰ 5፡ 14 ) በሰዎች ዘንድ ከሚኖረን ጥሩ ምስክርነት በተጨማሪ ለራሳችንም ጥሩ ነው፡፡
አብዝተን ታጋሽ በሆን ቁጥር ጭንቀትን እየቀነስን እንመጣለን፡፡
እግዚአብሔር ሰዎች እንዲድኑ ስለሚፈልግ በአስደናቂ ሁኔታ ይታገሰናል( 2ኛ ጴጥ 3፡4) መፅሐፍ ቅዱስ ከሁሉም ሰው ጋር በትዕግስት እንድኖር እና ቁጡዎች እንዳንሆን ያስተምረናል (1ተሰ 5፡ 14 ይመልከቱ)
በሰዎች ዘንድ ከሚኖረን ጥሩ ምስክርነት በተጨማሪ ለራሳችንም ጥሩ ነው።
በድርጊታችን ሰዎችን ሁሌም እናስተምራለን፡፡ ትምህርት ሁሌም በቃል ብቻ የሚደረግ አይደለም፡፡
ሁላችንም በሌሎች ላይ ተፅዕኖ ስላለን በምን መልኩ ተፅዕኖአችንን እንደምናሳርፍ መጠንቀቅ ይገባናል።
የኢየሱስን መስቀል አንገቴ ላይ አንጠልጥዬ የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ሰዎች ላይ ብበሳጭ እና ፍቅርን ባላሳይ ለእኔም ሆነ ለጌታ የሚጠቅመው ነገር የለም።
እውነቱን ለመናገር ባለፈው አስር ዓመት ሰዎች ሲያደርጉት ያየሁትን ሳስበው ያቅለሸልሸኛል፡፡
በ1ኛ ቆሮ 13 ጳውሎስ ስለ ፍቅር በፃፈው የፍቅር ዋነኛውና መጀመሪያው መገለጫ ትዕግስት ነው። ጳውሎስ ሲፅፍ ፍቅር ይታገሳል ይላል። ፍቅር ታጋሽ ነው ነገሮች እኛ ባቀድናቸው መንገድ አልሄዱ ባሉን ወቅት እንኳን ፍቅር አይለወጥም።
አሜን!
እግዚአብሔር ታጋሾች ያድርገን።
መልካም ቀን
https://youtube.com/c/ZekariasTadesseOfficial
490 views06:43