Get Mystery Box with random crypto!

​​#ህዳር 6 +በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ | መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)

​​#ህዳር 6

+በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።

ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!
ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡

ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

@ortodoxmezmur