Get Mystery Box with random crypto!

#ርዕስ_አልባ_ግጥም_2 . . በጠብ መንጃ አፈሙዝ የተገዛ ወንበር፣ በትውልድ ደም ላቦት የተገኘ መ | ግጥም

#ርዕስ_አልባ_ግጥም_2
.
.
በጠብ መንጃ አፈሙዝ የተገዛ ወንበር፣
በትውልድ ደም ላቦት የተገኘ መንበር።
.
.
አንከባሎ ያመጣው እስኪያጠፋው ድረስ፣
ሺ ቅልጥም ቢሰበር የሺ ሰው ደም ቢፈስ።
.
.
ለፌዝ እዘኑ እንጂ ከቶ አትሸበሩ፤
ወገን ገደል ይግባ!! ዝም ብላችሁ ምሩ፣
"ሀገር እግር ትብላ!!"
እስኪያቅረን ድረስ ቅዠቱን ደስኩሩ።
.
.
መቼም....
ቀን ያጣመመውን የትውልድ ደባ፣
ሲጎርፈው የኖረ የሻገተ እንባ።
በኪነጥበቡ እስኪያለሰልሰው፣
በ"ቢቸግር" ቅኝት ስቀን እናልቅሰው።
.
.
ዘመን ሲያባዝተው ቀን ሲያንቀው አክራሞት፣
ምንም ሆኖ ያልፋል የሰው ልጆች መሞት።!!

"........እንላቀስ ጎበዝ........"


ዓቢይ ( @abiye12 )

Join & share

@sinekal
@sinekal
@sinekal