Get Mystery Box with random crypto!

ዮቶር

የቴሌግራም ቻናል አርማ yotor61921 — ዮቶር
የቴሌግራም ቻናል አርማ yotor61921 — ዮቶር
የሰርጥ አድራሻ: @yotor61921
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 407
የሰርጥ መግለጫ

ዮtor የteleግራም አውታር

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 20:20:21
#አዲስ_ዝማሬ "በአፌ ነው ስምሽ" ዘማሪት ትዕግስት አበራ

https://t.me/yotor61921
32 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 19:47:14 100 ብር ሲታደል 10ብር አታምጣ!

በጾመ ፍልሰታ ውስጥ ህዝቡ አስቀድሶ ሲመለስ አባ ደግሞ በዓታቸው ውስጥ ቆይተው የሚዘክሩት ማኅበር ስላላቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ያዘግሙ ጀመር ሕዝቡ እስቀድሶ ሲመለስ ፊት ለፊት ይገናኛሉ አንዱን ጠሩት እና የኔ ልጅ አሉት በጣፋጭ አንደበታቸው ልጁም አቤት አባ አለቸው በትህትና ና እስኪ ጫማዪን እሰርልኝ አሉት እሺ ብሎ ጎበስ ብሎ እያሰረ እያለ የኔ ልጅ ቤተ ክርስቲያን ሄደህ ምን አድርገህ መጣህ? አሉት እሱም መልሶ አስቀድሼ መጣሁ! አለ እሳቸውም ማስቀደስ ብቻ? አሉት አዎ አለ ኮራ ብሎ እሳቸውም መልሰው 100 ብር ሲታደል የ10 ብር ይዘህ መጣህ! አሉት ማለት? ብሎ ሲጠይቃቸው ደህና ዋል ብለውት ሄዱ እሱም በልቡ እያወጣ እያወረደ ሄደ .አሁንም ሲሄዱ አንዱን ሰው ጠሩና ቤተ ክርስቶስ ምን አድርገህ መጣህ? አሉት ጸሎት አድርጌ እና አስቀድሼ መጣሁ አላቸው 100 ብር እየታደለ 20 ብር ይዘህ ብለውት ሄዱ እሁንም አንዱን ጠሩና ቤተ ክርስቲያን ምን አድርገህ መጣህ? አሉት ሰግጄ ጸልዪ አስቀድሼ መጣሁ አላቸው 100 ብር እየታደለ 30 ብር ይዘህ መጣህ ብለውት ሄዱ አሁንም ሲሄዱ አንዱን ጠሩና ቤተ ክርስቲያ ምን አድርገህ መጣህ? መጽውቼ ሰግጄ ጸልዪ አስቀድሼ መጣሁ አላቸው እሳቸውም 100 ብር ሲታደል 40 ብር ይዘህ መጣህ! አሉት እና ሄዱ አሁንም አንዱ ረጋ ያለ ልጅ ገና ሲያቻው ደህና ዋሉ አላቸው እግዚአብሔር ይመስገን ልጄ ቤተ ክርስቲያን ምን አድርገህ መጣህ? አሉት አልቅሼ መጽውቼ ሰግቼ ጸልዪ አስቀድሼ መጣሁ! አላቸው እሳቸውም መልሰው 100 ብር እየታደለ 50 ብር ይዘህ መጣህ አሉትና በል ደህና ዋል ብለውት ሄዱ... ከዛ ቤተ ክርስቲያን በሩ ላይ ደርሰው ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰላም ላንቺ ይሁን ብለው ቀና ሲሉ አንዲት ነጭ በነጭ የለበሰች አፏን ሸፍና ሽፍንፍን ብላ መጣችና ቀስ ባለ ድምጽ አባ አለች እሳቸውም በጣም ደስ ስላለቻቸው አትኩረው እየተመለከቱዋት አልሰሟትም አባ አባ አለች ጮክ ብላ አቤት የኔ ልጅ ብለው መስቀድ አወጡና ባርከዋት የኔ ልጅ ቤተ ክርስቲያን ምን አድርገሽ መጣሽ? አሏት እሷም መልሳ ስለ ኃጢያቴ አልቅሼ መጽውቼ ሰግቼ ጸልዪ አስቀድሼ በመጨረሻም ቅዱሥ ሥጋ ወደሙን ተቀብዪ መጣሁ አለቻቸው በእውነት እግዚአብሔር ይባርክሽ ሙሉ 100 ብር እየታደለ 100 ብሩን ይዘሽ የመጣሽ አንቺ ብቻ ነሽ እግዚአብሔር ይባርክሽ እግዚአብሔር ይፍታሽ በረከትሽ ይደርብኝ አሏት ውይ አባ ኧረ የእርስዎ በረከት ይደርብኝ እንጂ እኔማ ደካማይቱ ምን በረከት አለኝ አለች ተይ የኔ ልጅ በረከት እኮ የሚሰጠው በልዩ ልዩ ነው አንቺ ደግሞ በረከቱን በሙሉ ሰብስበሽ መጣሽ አሏት እሷም እግዚአብሔር ይመስገን አለች ነይ ብለው ወደ ዝክሩ ጋር ወስደዋት ተመገበች መርቀው አስተምረው ወደ ቤቷ ሸኙዋት !

እናንተስ? ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄዱ ምን ይዛቹ ነው ምትመጡት? 10 ብር ወይስ 100 ብር ? አያችሁ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ በረከትን ታድላለች በዋጋ ለሁሉም እንደ እየ ስራው ዋጋው ይሰጠዋል እናም እናንተ ዋጋችሁ ተመናችሁ ስንት ነው የ100 ብር ወይስ የ10 ብር ?

መልሱ ለእናንተ ተውኩ!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መሥቀሉ ክቡር ይቆየን.....

ደራሲ ዲ/ን አቤል (ፍቅረ አብ)
መልካም ሱባዔ

https://t.me/yotor61921
34 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 16:49:40
ዮቶር

መሐረነ አብ ጸሎት

https://t.me/joinchat/AAAAAFLFMxwzbhHUAByMLQ
44 views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:44:47 Channel photo updated
05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:22:52 ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ

ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
መጣሁ ከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ
ማን አፍሮ ያውቃል ባንቺ ለምኖ
በኪዳንኪ ተማህጽኖ

የነፍሴ እረፍቷ ታዛ መጠጊያ
ካንቺ ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ
በሰላምታሽ ድምጽ ተባርኳል ቤቴ
የጌታዬ እናት ለኔም እናቴ

ማርያም ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ
እስመ ተማኅፀንኩ አንሰ ተማኅፅኖ
ለሥዕልኪ ስዕለ አድኅኖ እሰግድ ለኪ

(ማርያም የሕይወቴ መጠጊያ
ሁኚኝ መማጸንን ተማጽኜሻለሁ
ለሚያድን ስዕልሽ እሰግድልሻለሁ)
አዝ
ቀንን ስናፍቅ በለሊት ሆኜ
አላተረፍኩም በሰው ታምኜ
ቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ
አሳስበሽልኝ አልፏል ስቃዬ

ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለልቡናየ ብርሃኖ
እስመ ተማኅፀንኩ አንሰ ተማኅጽኖ
ለስእልኪ ስዕለ አድኅኖ እሰግድ ለኪ

(ኪዳነ ምህረት ሁኚ ለልቤ ብርሃን
መማጸንን ተማጽኜሻለሁ ለሚያድን
ስእልሽ እሰግድልሻለሁ)
አዝ
ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ
በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ
ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ
ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ

ወላዲተ አምላክ ኩኒ ለእርቃንየ ክዳኖ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማህጽኖ
ለሥዕልኪ ስዕለ አድህኖ እሰግድ ለኪ

(ወላዲተ አምላክ ለመራቆቴ ልብስ
ሁኚኝ መማጸንን ተማጽኜሻለሁ
ለሚያድን ስዕልሽ እሰግድልሻለሁ)
አዝ
የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና
ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና
አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል
ከትናንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል

በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

https://t.me/yotor61921
55 views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:15:18 ቅዳሴ ተሰጥኦ (ማለትም በቅዳሴ መሀሉ ምዕመኑ የሚመልሰው ወይም የሚሳተፈው ) ነው


https://t.me/yotor61921
43 views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:03:25 https://t.me/yotor61921
42 views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:38:25 ​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/yotor61921
53 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 09:46:48 https://t.me/yotor61921
57 views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 03:48:56 ፆመ ፍልሰታ
(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች

የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን

https://t.me/yotor61921
78 views00:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ