Get Mystery Box with random crypto!

ዮቶጵ ኢትዮጵያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yotop77 — ዮቶጵ ኢትዮጵያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yotop77 — ዮቶጵ ኢትዮጵያ
የሰርጥ አድራሻ: @yotop77
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 323
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ በአምላክ የተወደደች፤ የጥንተ ስልጣኔ ምንጭ አኩሪ ባህል እና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። የሀገር ፍቅር መገለጫው አንዱ ስለ ታሪኳ ጠንቅቆ ማወቅ ነውና ስለ ኢትዮጵያ ያልተነገሩ እና ድንቅ ታሪኮቿን ለማወቅ፤ ይቀላቀሉን።

ለማንኛውም አስተያየት : @Dawit77

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-19 20:54:30 Abel_balehager:
ንግስተ ሳባ ማን ናት?
ረጅሙን ታሪክ ባጭሩ ለመከተብ ያክል

አንዳንዶች ኢትዮጵያዊት አንዳንዶች የመናዊት አንዳንዶች ናይጀሪያዊት ናት ይሏታል እነዚህ ሀገራት ስለርሷ ቅኔ ይቀኛሉ ተውኔት ይደርሳሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ያቀርባሉ ነገር ግን እውነታውና በታሪክ ሚዛን የደፋው ኢትዮጵያዊት መሆንዋ ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ አዜብ ይላታል ይህም ማለት ደቡብ ምዕራብ ማለት ነው በድሮ ዘመን አቅጣጫ የሚታወቀው ከእየሩሳሌም አንፃር ስለነበር ነው ከቅዱስ መፅሀፍ "በምድር መካከል መድሀኒትን አደረገ " ከሚለው በመነሳት እየሩሳሌም የምድር መካከል ናት ከሚለው አንፃር ሲታይ አዜብ ከእየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ ላይ ስለምትገኝ የደቡብ ምዕራብ ንግስት እንደማለት ነው ትክክለኛ የስሟ መጠሪያ ግን ማክዳ ይባላል።

የመኖች በልቂስ ይሏታል ብዙዎች የዓለም ሀገራት "Queen of Sheba" ይሏታል እኛም የሳባ ንግስት እንላታለን ንግስተ ሳባ ጥበብ አሳሽ ነች ባህረ ኤርትራን አቋርጣ ጥበብ ፍለጋ እስራኤል ድረስ ሄዳለች የቁንጂና ምሳሌ ናት የሚሏትም አሉ።

ማክዳ ትውልዷ አክሱም ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ957-982 ተወልዳለች ተብሎ ይታመናል የንግስና ዘመኗም 25 አመት ነበር።

ማክዳ የንጉስ ሰሎሞንን ዝና እየሩሳሌም ድረስ በሚመላለሱ ነጋዴዎች ትሰማ ነበር እሷም የማወቅ ጉጉት ያድርባትና ታምሪን የተባለውን ነጋድራስና የጠቢቡ ሰሎሞን የቅርብ ባለሟል አስጠርታ በደንብ ይገልፅላታል እሷም ንጉሱን ለመጎብኘት እንዳሰበች ትነግረዋለች መልዕክትም ትልካለች ንጉስ ሰሎሞንም ዝግጁ መሆኑን ገልፆ ስጦታ አብሮ ላከላት ማክዳም ወደ እየሩሳሌም ለመሄድ አጃቢዎቿን፣ደንገጡሮቿን ፣የቅርብ ባለሟሎቿን መለመለች ለጉዞም ተዘጋጀች ።

የቤተመንግስት የቅርብ ሰዎችንም ሰብስባ እንዲህ አለች "ነገሩን አድምጡኝ እኔ ጥበብን እሻለሁ ጥበብ ከሰማይ በታች ከማር ትጣፍጣለች ጥበብ ከወይን ታስደስታለች መንግሰትም ያለ ጥበብ አይቆምም ሀብትም ያለጥበብ አይጠበቅም እግርም ያለ ጥበብ በቆመበት አይፀናም ጥበብ ልዕልት ናት እንደ እናት እወዳታለሁ እሷም እንደ ህፃን ታፈቅረኛለች እኔ የጥበብን መንገድ ፍለጋ እከታተላለሁ እሷም እስከ ዘላለም ትጠብቀኛለች ለሁልጊዜ ትሆነኛለች ዱካዋን እከታተላለሁ ከእሷ አልጣላም እጠጋታለሁ እሷም የዲንጋይ ካብ ሀይልና ብርታት ትሆነኛለች የጥበብን ዱካ ልንከተል ይገባል ጥበብ ከንብረት ሁሉ ትሻላላች ወርቅና ብር የሰበሰበ ያለ ጥበብ አይጠቅመውም " ብላ ነገረቻቸው

ከዛም ማክዳ ስጦታዎቿን በግመል ጭና ጉዞ ወደ እየሩሳሌም ጀመረች ስጦታዎቿም ብዙ ሽቶ፣ዝባድ፣እንቁ ነበሩ ማክዳ በጠቢቡ ሰሎሞን ግዛት እንደደረሰች የደመቀ አቀባበል ተደረገላት ....
ከዚህ በኋላ ምን ሆነ ?
ይቀጥላል....


ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
120 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 የፍቅር መድረሻው!
(አኑ)

ሂድ ስትለው መጣ፣
ውረድ ሲባል ወጣ፣
ውጣ ሲባል ሲወርድ፣
አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣
ከራሱ ተጣልቶ፣
ከራሱ ተኳርፎ፣
ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ

(ያቺ ሴት)

የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች
በፍቅሩ የከነፈች፣
ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት!
እሱም የሚያፈቅራት
ከጎና ማይጠፋ
ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት!
አንድ'ዜ በሀይቅ
አንድ'ዜ በየብሱ
አንድ'ዜ በአየር
ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር።

(ዛሬ)

ተጣልተው
ተኳርፈው
ደግሞም ተለያየተው
አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው
ጎጆውን አፍርሰው
ተነጣጥለው አሉ
ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ።

(እሱ)

ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ
ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ
( ሁለት ነው ያዘዘው)
አንደኛው ለራሱ
ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ
እርግጥ ነው የለችም
በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ
(እንዲኽ ነው ሀሳቡ)

ትዕዛዙ እስኪመጣ
ጋዜጣ ያነባል
የጋዜጣው ርዕስ
ጥያቄ ይጠይቃል

(ጥያቄው)
ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል?
ከርዕሱ በታች
የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣

(እዚህ ጋር)

ቄሱም ሆነ ሼኹ
የፃፉትን ፅህፈት፣
የሰበኩት ስብከት፣
ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት!

(እውነቱ)

የቄሱም የሼኹም
የኣላህም የእግዜሩም
ቃሎች ሲመረመር
ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል
ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል)

ሳይጠጣው ተነሳ
ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ
ሚጓዝበት መንገድ
ማይሽር ፣ የማይጠፋ
ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ።
እርምጃው ፈጠነ
ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል
ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣
በሯን ደበደበ፣
እየሮጠች ወጣች፣
የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል
የምትለው ጠፋት
ፍርሀት ነብሷን ዋጣት




ተንበርክኳል
እግሯ ስር ተገኝቷል
በስስት ፣ በፍቅር
ሽቅብ አይኗን ያያል
ይቅርታ የሚል ቃል
ከአንደበቱ ይፈልቃል




አለቀሰች
አይኗን እንባ ወረሰው፣
አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣

ተነሳ አቀፈቹ
ሲያያት ሳመቹ









አለች
እየሳቀች

ጋዜጣውን አየ

ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

ይኽን አስታውሶ
ፊቱን ብርሀን ሞላው።



ከ #ግጥምብቻ @getem

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
80 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 #__ቁዝም....

የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ
እኩል አይታይም
ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ።

እያረፋፈደ
የሚገለጥ ሰማይ
ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ
ጨክኖ መጨከን የተለማመደ
የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ
ነጋ...ነጋ ...ባዩ
ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ።




መአቱ
ክንትው ....አለ ስንቱ
ሺ ዘመን ቢኖሩ ...
ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ
የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ
ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ



ይገርማል !!!

በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ
ፅልመት ያው....ፅልመት ነው
ተገባም ....ተወጣ
ሁሉን ይጋርዳል
ከነጭ ጥርስ ኋላ
የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል
እውነት የሚመስል
ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል
የተወለደም ዘር
ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል
ቀመሩ ያልገባው
ልቡ የታወረ
ኗሪ እንደ ደረጃው
ለእግሩ ጧፍ ያነዳል
ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ...
ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል
እንዲ ነው ክፉ ቀን
ይሄ ነው ጨለማ
ይህ ነው ሰንካላ እድል
እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል
ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል
ይህ ነው እርኩስ ወራት
ይህ ነው ብላሽ እድል
ምንም ማለት ማቃት
ምንም ማድረግ መሳን
ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል
ዳሩ ቀን ሲጎድል
ቀን ሲጥል ቀን እንጂ
ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ?
የት ችሎስ ይፈርዳል !!!

#አብርሀም_ተክሉ

ከ #ግጥምብቻ @Getem


@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
67 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 ስህተት ያልሠራ ሰው አዲስ ነገር በጭራሽ አልሞከረም ፡፡ - አልበርት አንስታይን
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ስህተቶች ማምለጥ የማትችሉት ነገር ናቸው. ይህ ከሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ
የማይቻል ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ ነው ፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ
ስህተት ያልፈጸመ አንድም ሰው የለም ፡፡ ስህተቶች ከሌሉ የሰው ሕይወት
አይኖርም። ደህና ፣ ስህተቶችን ለማስወገድ ብዙ ጥረት እንደሚሰጡን
እንገነዘባለን።
ግን አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው ​​በእርስዎ ቁጥጥር ስር አይደለም። እናም በዚያን ጊዜ
ስህተቶችን ከማድረግ በስተቀር ምንም ማድረግ አይችሉም ፡፡ እኛም ስህተቶች
መሥራት ልብዎን እንደሚያፈርስ እናውቃለን ፡፡ ስህተት ከሠሩ በኋላ ሁሉም ነገር
ተጠናቅቋል ብለው ያስባሉ። ግን እውነታው ትንሽ ለየት ያለ ነው ፡፡ ስሕተታችን
እጅግ በጣም ጥሩ ከሆኑት አስተማሪዎችዎ አንዱ መሆኑን ማወቅ አለብዎት።
በሕይወት ውስጥ በጣም ከባድ ትምህርቶችን ለመማር ይረዱዎታል ፡፡ ደህና ፣
ስህተት ካልሰሩ እነዚያን ትምህርቶች መማር ከባድ ይከብዳል ፡፡ ስለዚህ
ስህተቶችዎን ከአሉታዊ ገጽታዎች አንዱ እንደሆኑ አይመኑ ፡፡ ይልቁን እነሱን
ለእድገታቸው መሣሪያ አድርገው ይቆጥሩዋቸው። ማድረግ የሚችሉት በጣም
ጥሩ ነገር እርስዎ የሠሩትን ስህተቶች መድገም አይደለም ፡፡
አንዳንድ ዋጋ ያላቸውን ግንዛቤዎችን ለመሰብሰብ ይረዳዎታል። እና ለእነዚያ
ለህይወትዎ እድገት እነዚያን ግንዛቤዎች ማካተት ከቻሉ ስኬት ይመሰክራሉ ፡፡
ከዚህ የተሻለ ምንም ነገር የለም
ከስህተትዎ መማር. በተጨማሪም ፣ ውሳኔ የመስጠት ችሎታዎን ያሻሽላል ፡፡ እና
ያ ወደፈለጉት መድረሻ ላይ ለመድረስ ይረዳዎታል ፡፡


ከ #ይስማዕከወርቁእናሌሎችም


@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
64 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 የቀጠለ...

... ማክዳ ባቀባበሉ እጅግ ተደሰተች ከሀገሯ ስትመጣ አዋቂን ለመፈተኛ የሚሆኑ እንቆቅልሾችን ይዛ ነበርና መጠየቅ ጀመረች ሰሎሞንም ጠቢብ መሆኑን አስመሰከረ አንድም ከሱ የተሰወረ ነገር አልነበረም በሚገባ መለሰላት እርሷም ይበልጥ ለሱ ያላት ስሜትና አድናቆት ጨመረ ከዚያም ማክዳ ሰርቶት የነበረውን ቤት፣ የማዕዱን መብል ፣ በቤተመንግስት ያሉ አሳላፊዎች አለባበስ ፣ለእግዚአብሔር የሚያሳርገውን መስዋት ባየች ጊዜ እንዲህ አለችው "ስለነገርህ ከሰማሁት ዝና በላይ እውነት ነው እኔም መጥቼ እስካይ ድረስ አላመንኩም ነበር እነሆ እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር ጥበብና ስራህ ከሰማሁት ዝና ይበልጣል በፊትህ ሁል ጊዜ የሚቆሙ ጥበብህንም የሚሰሙ ሰዎችህና ባሪያወችህ ምስጉን ናቸው " ።

ስለ እርሷ ከመፅሀፍ ቅዱስ ውጪ ክብረ ነገሰትን መሠረት በማድረግ የሚነገሩ ተረኮች አሉ ክብረ ነገስት ከ 400 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በምን አይነት ስርዓት ትተዳደር እንደነበር ፣ የቀደምት ነገስታቶቿ ታሪክ ምን እንደሚመስል የሚያትት ታሪካዊ መዝገብ (መፅሐፍ) ነው ።

በዚሁ መፅሐፍ ስለ ማክዳና ሰሎሞን በተመለከት ሌላው ዓለም ያልፃፈው ያላወቀው አንድ ታሪክ አለ ምን ይሆን ?

ማክዳ ጉብኝቷን ከጨረሰች በኋላ አሰናብተኝ ትለዋለች ሰሎሞን ግን መሽቷል አትሄጅም ብሎ ምንጣፍ አስነጥፎ ምኝታውን ሊያጋራት ወደደ ንግስቷ ምንም በትወደውም "ድንግል ነኝ ንግስናውን ያገኘሁት ከወንድና ከዘውድ ምረጪ ተብየ ነው ወንድ የተገኘበት ክፍል ማደር ክብሬ አይፈቅድልኝም " ትለዋለች እንደዚህ ያለችው ንግስተ ሳባ ዘሮች ውጪ የንግስናውን ዙፋን ሌላ ባዕድ ወገን እንዳይመጣበት ከመፍራት ነው የሚሉም አሉ እሱ ግን ሀሳቧን እንድትቀይር ለመናት እሷም በእምቢታዋ ፀናች እርሱም ያጠምዳት ዘንድ ፈተና አዘጋጀባት ።

ማክዳ ሰሎሞንን ቃል ታስገባዋለች እርሱም ይሰማማና ለማደር ትፈቅዳለች ነገር ግን እርሱም ከንብረቴ ምንም ነገር የማትነኪ የማትጠይቂ ከሆነ ሲል ቃል ያስገባታል ይስማማሉ ከዛም ጨው የበዛበት ምግብ ያበላታል ከዛም ይተኛሉ ነገርግን የበላችው ጨው የበዛበት ምግብ ውሀ ያስጠማታል ደንገጡሯንም ሶርሀን ጠርታ ውሀ አምጪልኝ ትላታለች ውሀውን ግን ደብቆት ነበር ሶርሀንም ውሀ ፍለጋ ስትሄድ ታገኘዋለች እርሱም ስላሰበበት ማክዳ መስላው ሶርሀ ጋር ፈቃደ ስጋውን ይፈፅማል ።

ድንግል ነኝ አላልሽኝም ነበር ሲል ይጠይቃታል እሷም እኔ አገልጋይዋ ነኝ ስትል ትመልስለታለች ሰሎሞንም በጣም ይደነግጣል ይህንም ነገር ሚስጢር እንዲሆን ያስጠነቅቃትና ወደ ስፍራዋ ትመለሳለች ለሳባም ሂዳ ከለከለኝ እራሷ መታ ትውሰድ ብሎኛል ስትል ትነግራታለች ንግስት ሳባም ልትጠይቀው ትሄዳለች ይህን ግዜ ቃልሽን አፈረሽ ከንብረቴ ወሰድሽ ይላታል ሳባም "እንዴ ውሀ እኮ ነው የጠጣሁት"ስትል ትመልሳለች ሰሎሞንም ውሀ እኮ ማለት "ምድረን በውሀ ላይ ነው ያፀናት" ውሀ ብዙ ምስጢር ያለው ነገር ነው ቃልሽን አፍርሰሻል ብሎ ተገናኛት ።

ማክዳም ፀነሰች ይሄንም ነገረችው ሰሎሞንም በጣም ተደሰተ መታሰቢያ ይሆናት ዘንድ በእየሩሳሌም ቦታ ሰጣት የከበሩ እንቁዎችንም አበረከተላት ስትሰናበተውም "ሴትም ሆነ ወንድ ብወልድልህ የምልክልህን ምልክት ስጠኝ" ትለዋለች እሱም የብርና የወርቅ ቀለበትን ሰጣት ሴት ከሆነች ብሩን ወንድ ከሆነ ወርቁን ላኪልኝ ይላታል ።

ንግስተ ሳባ አምልኮቷን ወደ እግዚአብሔር የመለሰችው በዚሁ ጊዜ ነው ወደ ሀገሯም ስትመለስ በሙሴ ህግጋት አምልኮቷን አፅንታ መከተል ጀመረች ይሁን እንጂ ከዚህም በፊት በአንድ እግዚአብሔር የምታምን እንደነበረች የሚናገሩ የታሪክ ምሁራን አሉ ።

እንግዲህ ከረጅሙ ባጭሩ ታሪኳን ለማሳወቅ ያክል እንዲህ በብዕር ሰፍሯል መፅሐፍ ቅዱስን ያክል ነገር ጥበበኛ እያለ ያወደሳትን ንግስተ አዜብን በሀገራችን ግን አብዘሀኞቻችን አናቃትም ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር ያላት ግኑኝነት የተመሠረተበት ዋናው አምድ ይህ የንግስተ ሳባ ጉብኝት ነው ብዙ ጥበቦችን መንግስታዊ መዋቅሮችን ይዛ በመምጣት ለሀገሯ አበርክታለች ግን በቢቂው መልኩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታሪኩ አልተላለፈም የሚመለከታቸው አካላት ታሪኩን ህዙቡ ያውቀው ይመረምረው ዘንድ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክቴ ነው ።


መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ ም ፲ (10)
የማክዳ ንውዘት (በደራሲ ገስጥ ተጫኔ )
እንዲሁም ክብረ ነገስት ቢያነቡ ሰፋ ያለ ሀሳብ ያገኛሉ ።


ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
60 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 ንግስተ ሳባ ማን ናት?

ረጅሙን ታሪክ ባጭሩ ለመከተብ ያክል

አንዳንዶች ኢትዮጵያዊት አንዳንዶች የመናዊት አንዳንዶች ናይጀሪያዊት ናት ይሏታል እነዚህ ሀገራት ስለርሷ ቅኔ ይቀኛሉ ተውኔት ይደርሳሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ያቀርባሉ ነገር ግን እውነታውና በታሪክ ሚዛን የደፋው ኢትዮጵያዊት መሆንዋ ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ አዜብ ይላታል ይህም ማለት ደቡብ ምዕራብ ማለት ነው በድሮ ዘመን አቅጣጫ የሚታወቀው ከእየሩሳሌም አንፃር ስለነበር ነው ከቅዱስ መፅሀፍ "በምድር መካከል መድሀኒትን አደረገ " ከሚለው በመነሳት እየሩሳሌም የምድር መካከል ናት ከሚለው አንፃር ሲታይ አዜብ ከእየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ ላይ ስለምትገኝ የደቡብ ምዕራብ ንግስት እንደማለት ነው ትክክለኛ የስሟ መጠሪያ ግን ማክዳ ይባላል።

የመኖች በልቂስ ይሏታል ብዙዎች የዓለም ሀገራት "Queen of Sheba" ይሏታል እኛም የሳባ ንግስት እንላታለን ንግስተ ሳባ ጥበብ አሳሽ ነች ባህረ ኤርትራን አቋርጣ ጥበብ ፍለጋ እስራኤል ድረስ ሄዳለች የቁንጂና ምሳሌ ናት የሚሏትም አሉ።

ማክዳ ትውልዷ አክሱም ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ957-982 ተወልዳለች ተብሎ ይታመናል የንግስና ዘመኗም 25 አመት ነበር።

ማክዳ የንጉስ ሰሎሞንን ዝና እየሩሳሌም ድረስ በሚመላለሱ ነጋዴዎች ትሰማ ነበር እሷም የማወቅ ጉጉት ያድርባትና ታምሪን የተባለውን ነጋድራስና የጠቢቡ ሰሎሞን የቅርብ ባለሟል አስጠርታ በደንብ ይገልፅላታል እሷም ንጉሱን ለመጎብኘት እንዳሰበች ትነግረዋለች መልዕክትም ትልካለች ንጉስ ሰሎሞንም ዝግጁ መሆኑን ገልፆ ስጦታ አብሮ ላከላት ማክዳም ወደ እየሩሳሌም ለመሄድ አጃቢዎቿን፣ደንገጡሮቿን ፣የቅርብ ባለሟሎቿን መለመለች ለጉዞም ተዘጋጀች ።

የቤተመንግስት የቅርብ ሰዎችንም ሰብስባ እንዲህ አለች "ነገሩን አድምጡኝ እኔ ጥበብን እሻለሁ ጥበብ ከሰማይ በታች ከማር ትጣፍጣለች ጥበብ ከወይን ታስደስታለች መንግሰትም ያለ ጥበብ አይቆምም ሀብትም ያለጥበብ አይጠበቅም እግርም ያለ ጥበብ በቆመበት አይፀናም ጥበብ ልዕልት ናት እንደ እናት እወዳታለሁ እሷም እንደ ህፃን ታፈቅረኛለች እኔ የጥበብን መንገድ ፍለጋ እከታተላለሁ እሷም እስከ ዘላለም ትጠብቀኛለች ለሁልጊዜ ትሆነኛለች ዱካዋን እከታተላለሁ ከእሷ አልጣላም እጠጋታለሁ እሷም የዲንጋይ ካብ ሀይልና ብርታት ትሆነኛለች የጥበብን ዱካ ልንከተል ይገባል ጥበብ ከንብረት ሁሉ ትሻላላች ወርቅና ብር የሰበሰበ ያለ ጥበብ አይጠቅመውም " ብላ ነገረቻቸው

ከዛም ማክዳ ስጦታዎቿን በግመል ጭና ጉዞ ወደ እየሩሳሌም ጀመረች ስጦታዎቿም ብዙ ሽቶ፣ዝባድ፣እንቁ ነበሩ ማክዳ በጠቢቡ ሰሎሞን ግዛት እንደደረሰች የደመቀ አቀባበል ተደረገላት ....
ከዚህ በኋላ ምን ሆነ ?
ይቀጥላል....



ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
88 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:30 #የዛሬ_ዘመን_ሰው

የዛሬ ዘመን ሰው ከድሮው ይቄላል
እራሱ እየዘራ - ራሱ ይነቅላል፡፡

የዛሬ ዘመን ሰው :-
የሰው ሰው ሳይፈልግ - ልክ እንደ ትላንቱ
ራሱ የወለደውን - አምጦ ካንጀቱ፣
በፌስታል ጠቅልሎ - ምንም ሳይፀየፍ
ከሔሮድስ ብሷል - ልጆች በመጨፍጨፍ፡፡

በሙሉቀን


ከ #አትሮኖስ

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
53 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:29 ታላቁ ንጉስ ነገስት ኢትዮጵስ 1ኛ

ኢትዮጵስ 1ኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ1856 እስከ 1800 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛ ታላቅ ንጉሥ ነበር። የራጉኤል (ዮቶር) ልጅ የሆነው አባብሄር በሲና ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ ከአይሁድ ነገድ የሆነችውን ሩት አሚን አግብቶ ታላቁን ኢትዮጵስን የወለዱ ሲሆን በታላቅ ስርዓትም በግዮን ወንዝ ዳርቻ ስመ መንግስቱ ሰንደቅ ዠን ተብሎ የነገሰ ነው።

በሱ የስልጣን ዘመን በመላ ኢትዮጵያ በረከት ሆኖ ነበር። ዛፎች ልምላሜና ፍሬ ይሰጡም ነበር። አህዛብ ሁሉ የጣኦት አማልክትን የሰባበሩበት የፈጣሪም መንፈስ በመላ ሀገሪቱ የነገሰበት የበረከት ዘመን ነበር።

ንጉስ ነገስት ኢትዮጵስ (ሰንደቅ ዠን) በብዙ የሀገሪቱ ቦታዎች ታላላቅ ከተሞችንና መንደሮችን የቆረቆረ ነው። በሰባተኛ ዘመነ መንግስቱም ወደ ተራራማው የቴሌጋቫ ምድር ሄደ። በዚህ ምድር ጉምዞች ፣ በአያ ፣ ሽናሻ ፣ አገዎች ፣ ትግሬዎች ፣ ኦማርና አረማዎች ይኖሩበት ነበር። በዛም ታላቂቱን ከተማ ሱቫን ሰራ። በላያ በመባልም ትታወቅ ነበር። አሁንም ቢሆን በላያ የተባሉ ህዝቦች ይኖሩበታል። በዘልማድ የበላያ አገዎች ይባላሉ።

ንጉሥ ኢትዮጲስ የአንድ ሃይማኖትን ስነ ምግባርና ተግባር የሰበከ ታላክ ንጉሥ ነበር። ህዝባዊነትን፣ ምልክናንና ክህነቱን በኢትዮጵያ ያፀና መንፈሳዊ ንጉሥም ነበር። በአስፈሪነቱ ፣ በመንፈሳዊነቱና ታማኝነቱ ለእግዚአብሔርና ለሰው ሁሉ የተመቸ ሰው ነበር።

ንጉሥ ኢትዮጲስ በሶስት አመት ውስጥ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በማሰራት 1200 ንፁሃን ሰወች ያገለግሉ ዘንድ አስገባ። የእግዚአብሔርን ስርዓት የሚጠብቁና የሚአስተምሩ 400 ነብያትንም አስገባ።
ንጉሱ ይህን ሁሉ ያረግ የነበረው እግዚአብሔር በሃገሩ በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ ፅንቶ እንዲኖር በማሰብ ነበር። እግዚአብሔርም አላሳፈረውም " ከእንግዲህ ሀገሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ተብላ ትጠራለች እስከ ዘመነ ምጽአትም ድረስ ኢትዮጵያ እግዚአብሔር የሚመለክባት ምድር ሆና እንደምቀጥል" ለንጉሱና ለካህናቱ ቃል ኪዳን ገባላቸው። በዚህ ንጉሥ መልካምነትና በአባቶቻችን ትጋት ከዛ ጊዜ ጀምሮ የወረደው ሀይለ መንፈስ ቅዲስ በኢትዮጵያ ላይ ስለማይነሳ የእግዚአብሔር ሀገር ልትባል ችላለች። ገናም ስትባል ትኖራለች።

ንጉሥ ኢትዮጵስ የኢትዮጵያን ስም ያከበረና ከፍ ከፍ ያደረገ ሀገሪቱንም ኢትዮጵያ ተብላ እንድትጠራ ያደረገ ታላቅ የሀገራችን ባለውለታ ንጉሥ ነበረ። በዘመኑም ምድሩ ከማለምለምና ከተማ ከመቆርቆር በስተቀር ምንም አይነት ጦርነት ችግር መከራ አልነበረም ነበር።

ታላላቅ ሰዎች ከራሳቸው በላይ ለቀጣዩ ትውልድ በማሰብ የሚተጉ ናቸው። የእነ ንጉስ ኢትዮጵስ ትጋትና ድካም ለኢትዮጵያ የዘላለም ቃልኪዳንና በረከት ያስገኝ ነው። ዛሬ ዓለም ከሃይማኖት ርቃ በተለያየ ፍልስፍና እና ትርምስ ውስጥ ባለችበት ከባድ ወቅት እንኳ ኢትዮጵያ ሳትፈራርስና ፈጣሪዋን ሳትተው ይሄው ብዙ ሺ ዓመታት ተሻግራ ቆማለች፤ ይህም መሆኑ ከታላቁ ኢትዮጵስ 1ኛ ጀምሮ የወረደው ሀይለ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ ላይ ስለማይነሳ ነው። ዛሬ በተለያየ አቋራጭ ከምናካብተው ጊዜአዊ ዝናና ሃብት ይልቅ በሃቅ ቁመን ለትውልድ መትጋትን ከታላቁ ንጉሳችን ኢትዮጵስ 1ኛ እንማር።


ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
56 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:29 የመላ-ምት የሕይወት ዘይቤ መዘዝ
(“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

ዘመኑ የአየር-በአየር መረጃ ዘመን ነው፡፡ በመገናኛ ብዙሃን ገጾችም ሆነ በሌሎች መስኮች በሰማናቸው፣ ባየንቸውና በመሰለን ነገር በመነዳት ብዙ ነገር እንገምታለን፤ ማስረጃ በሌለን ነገር ላይ ብዙ ርቀት እንሄዳለን፡፡ ይህ ሕይወት የመላ-ምት ሕይወት ይባላል፡፡

በሕይወትህ የምትገምታቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር ከራስህ፣ በዙሪያህ ካሉ ሰዎችና ከሁኔታዎች ጋር የምትጋጭበት ጊዜ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ እውነታውን ለማወቅ ጊዜን ወስደህና አስፈላጊውን መረጃ ሰብስበህ ከግምትና ከመላ-ምት ማምለጥ ስትችል፣ በተሰማህ፣ በሰማኸውና በተባለው ስትነዳ የመላ-ምት ዓለም ውስጥ ዘልቀህ ትገባለህ፡፡ ይህ የመላ-ምት አለም አንድ ኢላማ ለመምታት አንድ መቶ ጥይት የመተኮስ አይነት የግምት ሕይወት ውስጥ ይጨምርሃል፡፡

ሰዎች የአንተን ሁኔታ በሚገባ ሳይገነዘቡና ትክክለኛ መረጃ ሳይኖራቸው በግምት ሲፈርጁህ አለመግባባትና የመጎዳት ስሜት መፈጠሩ የማይቀር ነው፡፡ እኔና አንተም ብንሆን በእውነት ላይ ያልተመሰረቱ ሁኔታዎች እንዲሁ በመላ-ምት ማስተናገድ ስንጀምር የሚያስከትለውን መዘዝ መገመት አያስቸግርም፡፡

1. ማህበራዊ ቀውስ
በቂ ጊዜን ወስደውና ሙሉ መረጃ ሰብስበው እውነትን ለማግኘት ጥጉ ድረስ ሳይሄዱ በመላ-ምትና በግምት መኖር የአለማችን ታላላቅ ቀውሶች መንስኤ ነው፡፡ በመላ-ምት ምክንያት በአለማችን ላይ የብዙ ሰዎች ህይወት ያለፈባቸው ጦርነቶች ተጀምረዋል፡፡ እውነታን ባላማከለ የመላ-ምት ውሳኔ ምክንያት የብዙ ወዳጅነት ጉዞ ወደ ፍጻሜ ደርሷል፡፡ የመላ-ምት ውጤት በሆነው ስሜታዊነት ምክንያት ብዙ ቤተሰብ ፈራርሷል፡፡ በጥቅሉ የመላ-ምት ልማድ ማሕበራዊ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ በግላችንም ቢሆን “በይባላል” እና “በይወራል” ትርምስ ውስጥ ሆነን የሕብረተሰቡ ጤናማ አካል እንሆናለን ብለን ማሰብ አንችልም፡፡

2. ያልተረጋጋ ህይወት
በየቀኑ ሃሳባቸውን የሚለዋውጡ ሰዎች እነማን ናቸው? እንደሰሙት ወሬ ወዲህና ወዲያ የሚዋዥቁ ሰዎች አይመስሉህም? በየሳምንቱ አቋማቸውን የሚቀያይሩስ እነማን ናቸው? እንደሚሰሙት የአሉባልታ አይነት የሚለዋወጡ ሰዎች አይመስሉህም? በየጊዜው ከአንዱ የአመለካከት ጎራ ወደሌላኛው የሚገላበጡ እነማን ናቸው? ከአንዱ ሃሳብ ወደሌላኛው እንዲሁ በመላ-ምት የሚዘዋወሩ ሰዎች አይመስሉህም? በአጭሩ የመላ-ምት ሰዎች በየጊዜው እንደሰሙት፣ እንዳዩትና እንደገመቱት ሁኔታ ወዲህና ወዲያ ስለሚዋዥቁ የሕብረተሰቡ ያልተረጋጋ ክፍል አባሎች ናቸው፡፡

3. ተቀይባነት ማጣት
በአካባቢያችን በስሜታቸው በመነዳት ወደ ድምዳሜ ከሚቸኩሉት የመላ-ምት ሰዎች ባላነሰ ሁኔታ በተገቢው ሁኔታ አእምሮአቸውን ተጠቅመው ከእውነታ አንጻር የሚኖሩም ሰዎች እንዳሉ እሙን ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት አይነት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊና ግልጽ ነው፡፡ የእውነታ ሰዎች በሕብረተሰቡ መካከል ለቁም ነገር የሚፈለጉና የተከበሩ ናቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የመላ-ምት ሰዎች በማስረጃ ከሚያረጋግጧቸው ሁኔታዎች ይልቅ በግምት የሚሳሳቷቸው ሁኔታዎች ሰለሚበዙ ተፈላጊነታቸው እጅግ የወረደ ነው፡፡

ወደማንኛውም የሕብረተሰቡ ክፍል የአመራር መሰላል በመውጣት መልካምን ተጽእኖ የማምጣት ፍላጎት ያለው ሰው ከመላ-ምት የተርታ ሕይወት ዓለም ወደ አውነታው የከበረ ሕይወት ዓለም ለመዘዋወር ቁርጥ ውሳኔ ያስፈልገዋል፡፡

#Dr-Eyob-Mamo


ከ #ነገረጥበብ @zikiretibeb


@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
62 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:54:29 "እዚህ አዲስአባ ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንጀራ በቢላ ሲቆረስ እናያለን።

ይኼን በቢላ የመቁረስ ባህል የጀመረው ማን ነው?

ለምን ጀመሩ?

እንጀራን በቢላ መቁረስ እንጀራን ወደ ዳቦ ለማውረድ መጣር እንደሆነ አልተረዱትም?

የእኛ ትልቁ ችግራችን ዕውር ኮፒ አድራጊዎች መሆናችን ነው። ፈረንጅ ዳቦ ሲቆርስ አይተን ከዛ ያን በጭፍን ያለ ጥየቃ ያለትንታኔ ተበደርን። የዚህ ችግር መነሻው በራሳችን ማመን አለመቻላችን ነው። በራሱ የማያምን ሕዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው። (.......)

ለመሆኑ እንጀራ ለመቁረስ እጅ አነሳትና ነው ቢላ የመጣባት? በእንግሊዘኛ ኦቨርኪል (overkill) ይባላል። ዝንብ ለመግደል ታንክ ስታወጣ ማለት ነው።

እንጀራ ቢደርቅ እንኳን አይፈነክትም
እንጀራ ጥፊ እንኳን አይሆንም
ምኑ ሰይፍ ያስመዝዛል?
ግን እንጀራ አገር ያቆማል ...”


#እቴሜቴ_ሎሚ_ሽታ
#አዳም_ረታ


ከ #ነገረጥበብ @zikiretibeb


@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77
73 viewsDawit, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ