Get Mystery Box with random crypto!

አፄ ኃይለ ሥላሴ ወደ ደብረ ዘይት መሄድ ፈልገው የአየር ንብረት ዘገባ በሬዲዮ ይሰማሉ፡፡ ቀኑ ፀሐ | ዮቶጵ ኢትዮጵያ

አፄ ኃይለ ሥላሴ ወደ ደብረ ዘይት መሄድ ፈልገው የአየር ንብረት ዘገባ በሬዲዮ ይሰማሉ፡፡ ቀኑ ፀሐይ ነው የሚል ነው ትንበያው፡፡ ንጉሡም ይህንን አምነው ወደ ደብረ ዘይት ያመራሉ፡፡ መንገድ ላይ ግን አንድ ገበሬ አህያውን እያስሮጠ ሲሄድ ያዩታል፡፡ ንጉሡም ‹ምነው አህያዋን ታስሮጣታለህ› ይሉታል፡፡ ገበሬውም ‹ዝናብ ሊመጣ ስለሆነ ነው› ይላቸዋል፡፡ ንጉሡም ‹እንዴት ዐወቅህ› ይሉታል፡፡ ገበሬውም ‹አህያዋ ጆሮዋን ጥላለች› ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ገርሟቸው ይሄዳሉ፡፡ እልፍ እንዳሉም የአየር ትንበያው የተናገረው ፀሐይ ቀርቶ ገበሬው የተናገረው ዝናብ መጣ ።

★★★★★★★★★★★★★★★★
የሃገራችን ገበሬ ኑሮን ከፈጣሪ በተሰጠው ጥበብ እንደሚመራ የሚያሰገነዝብ ታሪክ ነው:: የተፈጥሮ ጥበብ ከቴክኖሎጂ ጥበብ በብዙ እጥፍ የሚያስከዳ ነው።
★★★★★★★★★★★★★★★★

ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77