2022-02-12 01:51:40
ተወያዩበት፣ ሀሳብ ስጡበት፣ መረጃውን #ሼር_ፖስት አድርጉት። እንደኔ ህዝባችንን ለመታደግ መፍትሄው ለተደጋጋሚ ጥቃት ተጋላጭ ከሆኑ የኦሮሚያ ቀበሌዎች የሚኖረውን ዐማራ ወደሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ እና ማስፈር (population transfer) ብቻ ነው!
ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. ኮንፈረንስ ወዲህ ወያኔ "ኦሮሚያ" በሚል ባጠረው ክልል የሚፈፀመው (genocide) ሊቆም አይችልም። ምክንያቱም፦
1.በሸኔ ስም ጨለማን ተገን አድርጎ የኦሮሚያ መንግሥት የሚያካሂደው ጭፍጨፋ በመሆኑ መቼውንም ሊቆም አይችልም።
2. የኦሮሞ ፖለቲካ ተቦክቶ የተጋገረው በዐማራ ጥላቻ ላይ ነው። ፋኢዝ ሙሐመድ በቅርቡ "የታሪክ ንቅለ-ምልከታ" በሚል ባሳተመው መጽሐፉ፣ ገጽ.7 ላይ "የኦሮሞ ልሂቃን አንድ 'የጋራ ትውስታን' ለማታገያ ስልት በመጠቀሙ በኩል የተሳካላቸው ይመስላል። አርሲዎች 'ምኒልክ ወንዶቻችንን ገድሎ ሴቶቻችንን ጡታቸውን የቆራረጠው አኖሌ የምትባለው ቦታ ነው' በማለት ክስተቱን ለልጆቻቸው እያወጉ 'የጋራ ትውስታ' መፍጠራቸው የዓይን ምስክር ነኝ" በማለት ከአርሲ ሽማግሌዎች ከ20 አመታት በፊት የሰማውን ትርክት ጽፎታል። በዚህ መልኩ የኦሮሞ ሽማግሌዎች፣ ኢሊቶች፣ አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ህዝባቸውን ሞቢላይዝ እያደረጉት ያለው ከላይ እንደጠቀስነው በየአካባቢው የሚኖረውን ዐማራ በጠላትነት እንዲያዩት በመሆኑ እልቂቱ አይቆምም።
3. ዐማራ ስሁት ትርክት ፈጥረው በማንነቱ በታሪካዊ ጠላትነት ተፈርጇል። ነፍጠኛ”፣ “የምኒልክ ሰፋሪ”፣ "ትምህክተኛ"፣ "የድሮ ስርዓት ናፋቂ"፣ “ጨቋኝ” ወይንም “የጨቋኝ መደብ”፣ "አሐዳዊ"፣ "ደን ጨፍጫፊ"፣ "መጤ" የሚል ወካይ ስም (symbolization) ሰጥተውታል። ልክ ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱዎች በተዛባና በሐሰተኛ ስብከት ቱትሲዎችን ከሰው ደረጃ በማሳነስ "በረሮ" (cockroch) እና "እባቦች" (snakes) እያሉ እንደጨፈጨፏቸው። ስለዚህ ጥቃቱ ተጠንቶ፣ የስም ዝርዝር ተዘጋጅቶለት፣ በዕቅድ የሚመራ ስለሆነ ጥቃቱ ፈጽሞ ሊቆም አይችልም።
4. ኦሮሚያ ውስጥ ዐማራ አይደለሁም ብትል አንዴ በጠላትነት ተፈርጃሃል። ከአካባቢው ባህል ጋር መላመድ፣ በጋብቻ መዛመድ ሆነ ቋንቋውን መቻል ወይንም በፖለቲካው ፓሲቭ መሆን ለሩዋንዳ ቱትሲዎች፣ ለኩርዶች፣ ለጀርመን ጀውሾች ሆነ ለአዘር ባጃኖች አልሰራም። ናዚዎች በ50 እና በ100 ግድያዎች ተነስተው በሂደት ቀስ በቀስ 6 ሚሊዮን አይሁዳውያንን ገድለዋል። በተመሳሳይ ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ዐማራ ማንነቱን ቀይሮ "ገበሮ" ለመሆን ቢሞክርም፣ በፖለቲካው ፓሲቭ ቢሆንም ከመታረድ አልታደገውም።
5. ከዚህ በመነሳት የዐማራን ህዝብ ጨርሶ ከመጥፋት ለመታደግ በተለይም
ለተደጋጋሚ ጥቃት ተጋላጭ ከሆኑ የኦሮሚያ ቀበሌዎች የሚኖረውን ዐማራ ማንቀሳቀስ እና ማስፈር (population transfer) አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ህይወትንም መታደግ ነው፡፡
April 1, 2021 ሚኪ አማራ ያቀረበው ሀሳብም ይሄው ነበር። ሚኪ አማራ በወቅቱ የጻፈው የመፍትሔ ሀሳብ እኔም የምጋራው ነው። Population transfer በተለያዩ ሀገራት ጥቅም ላይ የዋለ እና የህዝቦችን ህይወት የታደገ ነው፡፡ ለምሳሌ፦
1. ኦሮሚያ ክልል ትልቁ ድክመቱ የነበረውን እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል የተወሰኑ ቦታዎች ላይ በማስወጣት ዛሬ ላይ የተሻለ ሰላም አላቸው፡፡ ቢያንስ የሚገደል ህዝብ የለም፡፡
2. የሶማሌ ክልልም ከ50 ሽህ በላይ የሚሆኑ ከኦሮሚያ ሁለት እና ሶስት አካባቢዎች በማስወጣቱ ከጭፍጨፋ አድኗቸዋል፡፡
3. በሰሜን ናይጀሪያ ኢቦዎች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ ሲካሄድ የሀገሪቱ መንግስት ከ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑትን በሰሜኑ ክፍል ይኖሩ የነበሩትን ወደ ሌላ አካባቢ አንቀሳቅሷል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ጭፍጨፋ አላጋጠማቸውም፡፡
4. የታሚል ዘር የሆኑ በሲሪላንካ ከተማ ኮሎምቦ አካባቢ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በየጊዜው ሲያጋጥማቸው በመቶሽዎች የሚቆጠሩት ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተዛውረዋል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ፍጅት አላጋጠማቸውም።
5. በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰርቦች ከስሎቬኒያ እና ክሮሽያ ክፍለ ግዛቶች በመውጣት ህይወታቸውን አትርፈዋል፡፡
6. እስከ ሁለት ሚሊየን የሚደርሱ ጀርመኖች ከኢስተርን ኢሮፕ ሀገሮች በመውጣት ከጭፍጨፋ ድነዋል፡፡
7. ከ 2 ሚሊየን በላይ ራሽያዎች በ1990'ዎቹ ከተገነጣጠሉት ሀገራት ወደ ራሽያ ግዛቶች ገብቶ በማስፈር ከጭፍጨፋ ተርፈዋል፡፡
8. 200 ሽህ ሃንጋሪዎች ከሰርቢያ አንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመስፈር ከጅምላ ግድያ ተርፈዋል፡፡
9. ቡልጋሪያ፤ ግሪክ፤ ቱርክ ውስጥ በየጊዜው ዘርን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎች አንዱን ወደ አንዱ በማስፈር ዘር ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋን አስወግደዋል፡፡
በመሆኑም በተደጋጋሚ እና ከፍተኛ ችግር የሚያጋጥምበትን አካባቢ በመለየት በተለየም በምእራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ በአርሲና በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ዐማራን ከአካባቢው የማስወጣት ስራ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ ከእነዚህ አካባቢዎች የሚወጡትን ለከተሞች ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ማስፈር፡፡
ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኑ እንደ ሰሜን ሽዋ አካባቢ ባሉት ዙሪያዎች ማስፈር፡፡ ወንዝ ያለበት አከባቢ ማስፈር፡፡ በተለይም መጠነኛ ግድቦች የሚሰሩባቸው እና በትንንሽ መሬት በአመት ሶስት እና አራት ጊዜ የሚያመርቱብት አካባቢ ማስፈር፡፡ ሰፋፊ ቦታዎች እና ከፍት የእርሻ መሬቶች ያሉበት አካባቢ ማስፈር ለምሳሌ ቋራ አካባቢ፤ ጃዊ፤ ምእራብ ጎንደር፤ ማእከላዊ ጎንደር (ዳንሻ ወልቃይት)፤ ሁመራ፣ ወልደያ አካባቢ እና የመሳሰሉት፡፡
ባለሃብቱ ተባብሮ በ10 ሽህ የሚቆጠሩ ቤቶችን በመስራት እንዲያግዝ ማድረግ አስፈላጊም ከሆነ ለዓመት እና ለሁለት ዓመት ብቻ የሚቆይ ልዩ የገቢ ግብር በመጣል ለዚሁ ተግባር ማዋል፡፡
እኛም ባናጓጉዛቸዉ አሁን ላይ በዱር በገደል እያሉ ግማሹ እየሞተ፤ ግማሹ እየቆሰለ፤ ንብረቱ ተበትኖ እየወጡ ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ ጥቃቱን ማስቆም ካልቻልን ለተደጋጋሚ ጭፍጨፋ ተጋላጭ የሆኑትን በመምረጥ ወደሌላ አካባቢ ከእነ ሃብት ንብረታቸው ከማጓጓዝ ውጭ ሌላ መፍትሄ የለውም፡፡ ከዚህ ውጭ ጨፍጫፊ መንግስት ላይ የቱም ያህል ጫና ብታደረግ ሊያቆም አይችልም፡፡
(ዮኒ ማኛ)
@yonimaga
@yonimaga
1.3K viewsUSA, 22:51